ትምህርት ሚኒስቴር ጠንካራ ሥነ-ልቦና፣ ባህሪ፣ እና አመለካከትን ለመፍጠር የሚረዳ ትምህርትን "Mind Education" ለማስፋፋት ከዓለም አቀፍ የወጣቶች ህብረት ጋር የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ

ትምህርት ሚኒስቴር ጠንካራ ሥነ-ልቦና፣ ባህሪ፣ እና አመለካከትን ለመፍጠር የሚረዳ ትምህርትን "Mind Education" ለማስፋፋት ከዓለም አቀፍ የወጣቶች ህብረት ጋር የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ

የኢ.... ትምህርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ ውስጥ በሥልጠና መልክም ሆነ በመደበኛ ትምህርት ሥርዓተ-ትምህርት ውስጥ አካቶ ጠንካራ ሥነ-ልቦና፣ ባህሪ፣ እና አመለካከትን ለመፍጠር የሚረዳ ትምህርትን "Mind Education" በዘርፉ ውስጥ በስፋትና ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ለመስጠት የሚረዳ የስምምነት ሰነድ  መቀመጫውን በደቡብ ኮሪያ ባደረገው የዓለም አቀፍ የወጣቶች ህብረት ጋር በትምህርት ሚኒስቴር መጋቢት 05 ቀን 2009 . ተፈራረመ።

 

በትምህርት ሚኒስቴር በኩል የስምምነት ሰነዱን የፈረሙት የትምህርት ሚኒስትር ክቡር / ሽፈራው ክለማሪያም ሲሆኑ በዓለም አቀፍ ወጣቶች ህብረት በኩል የህብረቱ መሥራችና መሪ የሆኑት የደቡብ ኮሪያ ተወላጅ / ኦክሱ ፓርክ ናቸው። ክቡር ሚኒስትሩ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ይህ በደቡብ ኮሪያ የተጀመረውና በዓለም አቀፍ የወጣቶች ህብረት እየተስፋፋ ያለው ጠንካራ ሥነ-ልቦና፣ ባህሪ፣ እና አመለካከትን ለመፍጠር የሚረዳ ትምህርትን በተመለከተ አጫጭር ገለፃዎች ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሠራተኞችና ለተወሰኑ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሠራተኞች ተሰጥቶ ጥሩ ግብረ-መልስ የተገኘበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ክቡር ሚኒስተሩ ይህንን ጅማሬ በውጤታማ መልኩ አደራጀቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ለሆኑ መምህራኖቻችንን በአሰልጣኞች ሥልጠና (TOT) መልክማድረስ ይህ ስምምነት እገዛ እንደሚያደርግ አስገንዝበዋል፡፡ በቀጣይም ከታችኛው የትምህርትና ሥልጠና እርከን ጀምሮ እስከ ከፍተኛው ድረስ ትምህርቱን በመደበኛነት በአገሪቱ ሥርዓተ-ትምህርት ውስጥ አካቶ ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመስጠት የሚስችል አሰራር ለመዘርጋት የስምምነት ሰነዱ ዋነኛ መሠረት መሆኑን ዶክተር ሽፈራው ገልጸዋል። ይህ ትምህርት በትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ የሀገርን አደራ የሚረከቡ ሁለንተናዊ ብቃትንና ሥነ-ምግባርን የተላበሱ ምክንያታዊ አስተሳሰብ ያላቸውን ዜጎችን ለመፍጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ እንዲሆን ከፍተኛ ፋይዳ ያለው መሆኑን ገልጸዋል። ዶክተር ሽፈራው ለዚህ ሥራ መሳካት ከሁሉም በላይ የመላው ህዛበችን ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው  ህብረቱም ሆነ የደቡብ ኮሪያ መንግሥት እገዛ እንደ ከዚህ በፊቱ እንደማይለየን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

 

የዓለም አቀፍ የወጠቶች ህብረት መሥራችና መሪ የሆኑት የደቡብ ኮሪያው ተወላጅ የሆኑት / ኦክሱ ፓርክ ከፍርማ ሥነ-ሥርዓቱ በኃላ ኢትዮጵያ የዚህን ትምህርት ፋይዳ ተገንዝባ ለነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶቿ ለመስጠት ወስና በይፋ ወደ ሥራ መግባቷን አስመልክቶ ባደረጉት የእንኳን ደስ አላችሁ ንግግራቸው ውስጥ ትምህርቱ 10 ዓመታት ውስጥ በሀገሪቷ ሁለንተናዊ ልማት ላይ በግልጽ የሚታይ ተጽዕኖ እንደሚያሳይ ያለውን እምነት ጠቅሰው ትምህርቱ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ የሚጠበቅባቸውን ትብብርና ድጋፍ  እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። ማህበሩ በተወሰኑ የአፍሪካ ሀገራት ዋና ከተሞች ላይ ቢሮዎችን ከፍቶ ሀለ-ገብ አገልግሎት የሚሰጥ የወጣቶች ማዕከል ለመገንባት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ጠቅሰው በቅርቡ በአዲስ አበባ ቢሮዎችን ለመክፈት እየተንቀሳቀሳ መሆኑንና የአዲስ አበባን የአፍሪካ መዲናነት ከግንዛቤ ባስገባ ሁኔታ በሌሎች አፍሪካ ሀገራት ከሚገነቡት ይበልጥ ጉዙፍ የሆነ ሀለ-ገብ የወጣቶች ማዕከል ለመገንበት ለኢትዮጵያ መንግሥት የመሬት ጥያቄ ማቅረቡንም ተናግረዋል። እንደሚያበረክት ተናግረዋል። / ኦክሱ  በማከል ትምህርቱ ከእድገት ጋር ተያይዞ በደቡብ ኮሪያ የመጠውን ማህበራዊ ችግር ማለትም የግለሰቦች ራስን ወይም ፍላጎትን ያለመግዘት (ያለመቆጣጠር) ችግር እንዲሁም በተስፋና በራዕይ መኖር ያለመቻልን፤በሌላ አገለለጽ  የዳካማ አእምሮ ባለቤት የሆኑ ዜጎች መበራከትን፤ይህ ችግር ኮሪያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ዜጎች በብዛት ራሳቸውን የሚያጠፉባት ዋነኛ ሀገር እንዲትሆን ያደረጋት ስለመሆኑ፣ለዚህም ችግር በደቡብ ኮሪያም ሆነ በአሁኑ ወቅት ለሌሎች ሀገራት እንደ መፍትሔ ሆኖ እያገለገለ ያለው  ይህ ”Mind Education” ወይም ”Mind seting Education” (ራስን ወይም ፍላጎትን ወይም ምኞትን በራስ" በቤተሰብና በሀገር አቅም ልክ የመግዛት ወይም የመቆጣጠር ትምህርት እና  ጠንካራ ሥነ-ልቦናና አእምሮን የመፍጠር) ትምህርት እንደሆነ ገልጸዋል።


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡