ለትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞች በሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን (JEG) ምንነት እና የማስፈጸሚያ መመሪያ ላይ የግንዛቤ ማሰጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ

ለትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞች በሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን (JEG) ምንነት እና የማስፈጸሚያ መመሪያ ላይ የግንዛቤ ማሰጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ

ለኢ... ትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞች በሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን (JEG, Job Evaluation and Grading) እና የማስፈጸሚያ መመሪያ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና መጋቢት 01/2009 . በሚኒስቴር /ቤቱ የመሰብሰቢያ አደራሽ ተሰጠ፡፡

 

በትምህርት ሚኒስቴር የሰው ሀብት ልማት አስተዳደር ዳይሬክተር / አሰፋሽ ተካልኝ ሥልጠናውን ሲያስጀምሩ እንደተናገሩት  መድረኩ የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ሥርዓት በቅርብ ጊዜ ከጥቂት ወራት በኋላ በመሥሪያ ቤታችን ደረጃ የሚተገበር እንደመሆኑ መጠን ሠራተኞች ሥርዓቱንም ሆነ እሱን ለማስፈጸም የተዘጋጀውን መመሪያ ተገንዝበው በትግበራው ወቅት ግዴታቸውን ለመወጣትም ሆነ ማብታቸውን ለማስጠበቅ እንዲጠቀሙበት የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል። በትምህርት ሚኒስቴር የሰው ሀብት ልማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት የተዘጋጀው ስልጠና ከተቋሙ ህልውና ጋር የተቆራኘ ስለሆነ ሠራተኞች ሥልጠናውን በከፍተኛ ትኩረት ተከታትለው በሚፈለገው ደረጃ ዝርዝሮችን በመገንዘብ በትግበራው ላይ ጠቃሚ ሚና እንደሚኖራቸው ያላቸውን ተስፋ ዳይሬክተሯ ገልጸዋል።

 

ሥልጠናውን የሰጡት  የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ፕሮጀክት /ቤት ባለሙያ አቶ ከሳሁን ግደይ ሲሆኑ የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ሥርዓትን  ምንነት አሁን በትግባራ ላይ ካለው ሥርዓት ጋር በማወዳደር እንዲሁም ሥርዓቱን ለማስፈጸም የወጣውን መመሪያ አስመልክቶ ገለፃ አቅርበዋል። ከገከለጻው በኋላ በተሰጠው  እድል መሠረት ሠራተኞች በነሱት ጥያቄዎና ሀሳቦች ላይ አቶ ካሳሁንና / አሰፋሽ ምላሽና ማብራሪያ ሰተውባቸዋል።

 

ከተነሱት ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል የሚከተሉትን ለአብነት ለማንሳት ያክል፦ የሀገራችን የሥራ ምዘናና ደረጃ ምደባ ታሪካዊ አመጣጥና ተጨበጭ ሁኔታው፣ ከድሮ ጀምሮ እስከ አሁን በሥራ ላይ ያለው ሥርዓት “Positon Classification” በመባል የሚታወቅ መሆኑና የሥራ ምዘናው የትምህርት ዝግጅትና የሥራ ልምድን ብቻ መሠረት ያደረገና በሚገባ ሥራን የማይመዝንና ለእኩል ሥራ እኩል ክፍያ የሚለውን መሪህ ያልተከተለ ስለመሆኑ፣ አዲሱ የሥራ ምዘና Point Rating በመባል የሚታወቅ መሆኑና በርካታ ጉዳዮችን መሠረት የሚያደርግ መሆኑ፣ የመስፈጸሚያው መመሪያ (የመንግሥት ሠራተኞች የድልድል መመሪያ) ከያዛቸው ዋና ዋና ይዘቶች መካከል የሠረተኞችና የአመራሮች የማወዳደሪያ መስፈርቶች ያሉ ሲሆን ለአብነት ያክል የሠረተኞች፦ በውጤት ተኮር የአመዛዘን ዘዴ የአፈጻጸም ውጤት 70%፣በድልድሉ ወቅት አንድ ሰው በአንድ ጊዜ በሚመጥናቸው በሁለት የሥራ መደቦች ብቻ ላይ መወዳደር የሚችል ስለመሆኑ፣የመንግሥት ፖሊሲንና ስትራቴጂን ለመፈጸም ያለው ዝግጁነትና ተነሳሽነት 10%፣የማህደር ጥራት  10% ከፍ ባሉ ዳረጃዎች ላይ ለተሰጠ አገልግሎት 10% በድምሩ ከመቶ የሚመዘኑበት መሆኑ፣ የቅሬታ አቀራረብ ሥርዓትን በተመለከተ በውድድሩ መሠረት የሚደረገው የድልድል ውሳኔው ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ  ቅሬታ ለዚሁ ዓላማ  ለተቋቋመው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ማቅረብ የሚቻል ስለመሆኑ እና የመሳሰሉት ጉዳዮች ተናስተዋል።

 


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡