ከመስከረም 8 - 15/2010 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የትምህርትና ስልጠና ሣምንት የንቅናቄ መድረክ ማስፈፀሚያ ዕቅድ ዙሪያ ውይይት ተደረገ፡፡

ከመስከረም 8 - 15/2010 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የትምህርትና ስልጠና ሣምንት የንቅናቄ መድረክ ማስፈፀሚያ ዕቅድ ዙሪያ ውይይት ተደረገ፡፡


የንቅናቄ መድረኩ አምስት ዋና ዋና ዓላማዎች እንዳሏቸው የገለፁት ሚኒስትሩ፣ በእያንዳንዱ ዓላማ ዙሪያ ለተሰብሳቢዎች ገለፃ ሰጥተዋል፡፡
ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ድረስ ኃላፊነታቸውንና ተልዕኮአቸውን በሚገባ ተረድተው 2010 . ዕቅድን በላቀ ሁኔታ በመፈፀም የትምህርት አግባብነትና ጥራትን ማጎልበት ዋነኛ ዓላማ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
2009 . የጥልቅ ተሃድሶ ግምገማ በኋላ በመጡ ለውጦች ላይ በመወያየት ቀሪ ተግባራትን በተሃድሶ መንፈስ በመተግበር የትምህርት ፍትሃዊነትንና ጥራትን ማስጠበቅ ሌላው ዓላማ እንደሆነ ያስገነዘቡ ሲሆን መምህራን የትምህርትና ስልጠና ጥራትና ብቃት በማረጋገጥ ብቁ ዜጋን ለማፍራት በሚደረገው ጥረት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የወላጅነትና የባለአደራነት ሚናቸውንና ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የሚያስችላቸውን ግንዛቤ በመፍጠር ተግባራዊ እንዲያደርጉ ማስቻል የንቅናቄ መድረኩ ዓላማ እንደሆነ አሳውቀዋል፡፡
በስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር ትምህርት አሰጣጥ ላይ የተለያዩ ጥናቶች የተደርጉ ሲሆን በዚሁም መሰረት ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ማህበረሰብ ለመገንባትና ተልዕኮ ለመወጣት በሚያስችል መልኩ ማሻሻያ ተደርጎበት በትምህርት ሴክተሩ ላይ ያለውን ትልቅ ድርሻ የማሳካት ዓላማ መድረኩ እንዳነገበ ሚኒስትሩ አስጨብጠዋል፡፡
በመጨረሻም ከአምስት ዓመቱ የትምህርት ሴክተር ልማት መርሃ-ግብር እንዲሁም 2ኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የተቀዳውን 2010 . ዕቅድ በአግባቡ ተገንዝቦ የተደራጀ የልማት ሠራዊት ውጤታማነትን ለማስፈፀም ታሳቢ ያደረገ ዓላማ እንደሆነ ገልፀው ሁሉም ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ለውጤታማነቱ መትጋት እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል፡፡


News

ትምህርት ሚኒስቴር ተፈናቅለው ለነበሩ ተማሪዎች የአልባሳትና የመማሪያ መሳሪያዎች ድጋፍ አደረገ።

ትምህርት ሚኒስቴር በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን እና በደ/ብ/ብ/ህ/ክልል በምዕራብ ጌዲዮ ዞን አዋሳኝ አካባቢ በተፈጠረው ግጭት ተፈናቅለው ለነበሩ ተማሪዎች የአልባሳትና የትምህርት መማሪያ መሳሪያዎች ድጋፍ አደረገ።

የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ-ካርታ ፎረም ተጀመረ፤

ከትምህርትና ስልጠና ዘርፉ የሚመነጩ ችግሮችን ከመሠረቱ በመፍታት ሥራ የሚወድ ፣ ሌብነትን የሚጠየፍና ለህዝብና ለአገር የሚሰራ ባለሙያና አመራር በመፍጠር የተሻለች ኢትዮጵያን መገንባት እንደሚገባ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ አስገነዘቡ፡፡

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።