በሀገራችን ለ8ኛ ጊዜ በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመናገር ቀን በዓል ተከበረ

በሀገራችን ለ8ኛ ጊዜ በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመናገር ቀን በዓል ተከበረ

የኢ.... ትምህርት ሚኒስቴር ከባህልና ቱርዝም ሚኒስቴርና ከሐረሪ ሕዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል፣ቅርስ ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር በዓለም አቀፍ ደረጃ 19 በሀገራችን ደግሞ 8 ጊዜ የሚከበረውን በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመናገር ቀን በዓልቋንቋዎቻችን በመጠበቅና ልሳነ-ብዙነትን (Multilingual) በማበረታት ለዘላቂ የልማት ስኬት እንትጋ!’’ በሚል መሪ ቃል በሐረሪ ሕዝቦች ክልል በታሪካዊቷ ሐረር ከተማ ከየካቲት 14 እስከ 15/2010 . በዓሉን በድምቀት አከብV ፡፡

በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ረመዳን አሸናፊ በዓሉን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀውን ሲምፖዝየም በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት ዘንድሮ በሀገራችን ደረጃ 8 ጊዜ የሚከበረውን በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመናገር ቀን በዓልን በሐረሪ ሕዝቦች ክልል እንዲከበር የተመረጠበት ዓላማ ከተማዋ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት /UNESCO/ እውቅና የሰጣት ታሪካዊ ከተማ በውስጧ ልሳነ-ብዙ ቋንቋ የሚነገርባት ከተማ በመሆኗ ነው ያሉት ሲሆን ሚኒስትሩ አክለውም የክልሉ መንግስት የሐረሪኛ ቋንቋ የፊደል ገበታ ቀርጾ የአካባቢው ተወላጅ ሕፃናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ ሁኔታዎችን በማመቻቸ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ መደበኛ ትምህርታቸውን መማር እንዲችሉ በማድረጉና ለቋንቋ ልማት እያደረገ ያለው ጥረትና እየታዩ ያሉ ለውጦች አበረታች በመሆናቸው ነው ብለዋል፡፡

እንደ ክቡር አቶ ረመዳን ገለፃ እስካሁን በተደረጉ ሀገራዊ የቋንቋ ልማት መስክ እንቅስቃሴዎች በሀገራችን 56 ቋንቋዎች የጽሁፍና የትምህርት ቋንቋ እንዲሆኑ ተደርጓል ፡፡ ከነዚህም መካከል 12 ቋንቋዎች በሳባና 44 በላቲን ፊደል ስክሪፕት የሚጠቀሙ መሆናቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ ሕዝቦች ትምህርት የሚሰጥባቸው የቋንቋዎች ብዛት ሦስት ሲሆኑ በቋንቋው የሚጠቀሙበት ስክሪፕት ሁለት ሳባ እና አንድ ላቲን እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡

በክልሉ መንግስት ባህል፣ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ የቋንቋ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ አብዱልቃድር የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት እንዳሉት የበኣሉ መከበር የህዝብ ለህዝብ ትስስርና በባህል መካከል የሚኖሮውን መስተጋብርን እንደሚያጠናክር አብራርተዋል፡፡

በኢ.... ትምህርት ሚኒስቴር የአፍ መፍቻና እንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ / እመቤት አበራ ጋር በተደረገ ቃለ ምልልስ እንደገለጹት ሕፃናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መማር የትምህርት ተሳትፎን ከማሳደግና ጥራቱንም በሚፈለገው ደራጃ በማድረስ ረገድ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እንደ / እመቤት ገለፃ ተማሪዎች አፋቸውን በፈቱበት ቋንቋ ሲማሩ፣ ሲሰሩ ሲከራከሩ ፣ሲመራመሩና የአካባቢያቸውን ችግር መፍታት ሲችሉት ይበልጥ በትምህርታቸው ውጤታማ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

በአፍ መፍቻ ቋንቋ መናገር የማሰብ ነፃነትንና ሰብዓዊ ፍጥረትን ይበልጥ የሚያጎላና ቋንቋን ጨምሮ በሶስት ነገሮች ማለትም ማንነት ቋንቋና ባህልን አሁን ካለበት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ሕጋዊ ከለላ እንደሚያስፈልጋቸው ለመረዳት ተችሏል፡፡

በበዓሉም የማስተማር ቋንቋ ተግዳሮቶች፣ የትርጉም ስራ አስፈላጊነት የአስተርÒሚነት ሙያ እና የብቃት አሰጣጥ በኢትዮጵያ እንዲሁም የአፍ መፍቻ ቋንቋ ልማት ስራ በሀገራችን ያለበትን ደረጃና የወደፊት ሁኔታ በሚሉት ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ሕፃናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ተጠቅመው የአካባቢያቸውን ሳይንሳዊ ፅንስ ሃሳብ ተምረው በቀላሉ መረዳት እንዲችሉና የሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦች የአንደኛ ደረጃ ትምህርትን በቋንቋቸው እንዲማሩ መብት በመደንገግ ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል፡፡

በሲምፖዚየሙም ላይ ከትምህርት ሚኒስቴር ፣ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና ከክልል ባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

ባለፈው ዓመት 7ኛው በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመናገር ቀን በኣል በጋምቤላ ሕዝቦች ክልል መከበሩ የሚታወስ ነው፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡