በአገራችን በአሁኑ ወቅት 28 ሚሊዬን ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው

በአገራችን በአሁኑ ወቅት 28 ሚሊዬን ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው

ባለፉት 25 ዓመታት ለሃገራችን ዜጎች ትምህርትን በፍትሐዊነት ለማዳረስ በተደረገው ጥረት በአሁኑ ወቅት 28 ሚሊዬን ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አስታወቁ፡፡

ሚኒስትሩ የትምህርትን ተገቢነት፣ ፍትሐዊነትና ጥራትን ለማምጣት በአዳማ ከተማ በተዘጋጀው የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ዜጎች ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ድረስ ፍትሐዊ ትምህርት እንዲያገኙ ከአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በሚመጥን መልኩ ቢያንስ በየ 2.5 ኪሎ ሜትር ርቀት አንድ ትምህርት ቤት በመሰራቱ በሴቶችና በወንዶች፣ በገጠርና በከተማ፣ ልዩ ፍላጎት ባላቸው ዜጎች የትምህርት ፍትሐዊነትን በማረጋገጥ ረገድ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡ Image

በትምህርትና ስልጠና ዘርፉ ባለፉት ጊዜያት የተመዘገቡ ውጤቶች አመርቂ መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ ሽፈራው በቀጣይም የዘርፉን አፈፃፀም የተሻለ ለማድረግ የትምህርት ጥራት ማስጠበቅ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት፣በግብዓትና አቅርቦት በተገቢ ሁኔታ ማሟላት እንዲሁም የመማር ማስተማር ሂደቱን ሰላማዊ በሆነ መልኩ ለማስቀጠል ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ አስገንዝበዋል፡፡ 

በመጪው የትምህርት ዘመን በሰላማዊ የመማር ማስተማር ላይ፣ በትምህርት ቤቶች ደረጃ፣ በመጠነ ማቋረጥና መጠነ መድገም፣ በልዩ ፍላጎት እንዲሁም ብቃት ያላቸው መምህራንን በማፍራት ተወዳዳሪና ብቁ እንዲሁም ምክንያታዊ ትውልድ ለመፍጠር ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባም አቶ ሽፈራው አስገንዝበዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ መርጊያ ፈይሳ በአሁኑ ወቅት ያደጉ ሀገሮች ሚስጥር ለትምህርት በሰጡት ትኩረት መሆኑን ጠቅሰው የክልሉ መንግስትም አሳታፊና ጥራት ያለው የትምህርት ዕድል ለዜጎች ለማድረስ በተደረገው ጥረት 8.7 ሚሊዬን ዜጎች ትምህርት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ ወደፊትም በክልሉ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት የተረጋጋና የተቃና እንዲሆን ከማድረግ ባሻገር የመጠነ ማቋረጥ ችግርን ለማስወገድ ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ በመሆን የዕለት ተዕለት ስራ ለማድረግ ጥረት እንደሚደረግ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡


News

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡