የ2010 ዓ.ም በጀት ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የ6 ወር የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በሐዋሳ ከተማ ዛሬ ተጀመረ፡፡

የ2010 ዓ.ም በጀት ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የ6 ወር የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በሐዋሳ ከተማ ዛሬ ተጀመረ፡፡

የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሀዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ ኃላፊ / እሸቱ ከበደ መድረኩን ሲከፍቱ፣ ዕድሜው ለትምህርት የደረሰ ህፃን ሁሉ የትምህርት ዕድል እንዳገኘ ገልፀዋል፡፡
በመቀጠልም በአፈፃፀምና በስነ-ምግባር ጉድለት የተገኘባቸው 612 የትምህርት አመራሮች ላይ የማስተካከያና የእርምት እርምጃዎች በመውሰድ የማጥራት ስራ መሰራቱን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ገልፀዋል፡፡
የቢሮ ኃላፊው አያይዘውም ሴቶችን ወደ ትምህርት አመራርነት ለማምጣት በፈተና 50% በላይ ውጤት ካገኙ በዘርፉ አመራር እንዲሆኑ መመሪያ ፀድቆ እንደወረደ አሳውቀዋል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ መሐመድ አህመዲን እንደገለፁት፣ 27ኛው የትምህርትና ስልጠና ጉባዔ ላይ ተነስተው ሊሰራባቸው ይገባል በተባሉት ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግ ያሳወቁ ሲሆን በተለይም በትምህርት ዘርፉ በተከሰቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ፣ በትምህርት ቤት አመራሮች ልማት ዙሪያ በተለይ በሴቶች የአመራርነት ተሳትፎ ዙሪያ፣ በመምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና ዙሪያና የጎልማሶች የትምህርት ተሳትፎ ዙሪያ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ምን ያህል እንደተተገበሩ በመገምገም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ጠቁመዋል፡፡
የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማው መድረክ በቀጣይ ሁለት ቀናትም ቀጥሎ እንደሚውል የትምህርት ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዘግቧል፡፡


News

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡