የ2010 ዓ.ም የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ከግንቦት 22 - 30 /2010 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ተገለፀ፡፡

የ2010 ዓ.ም የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ከግንቦት 22 - 30 /2010 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ተገለፀ፡፡

የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርዓያ ገብረእግዚአብሄር እንደገለፁት፣ 10 ክፍል የሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 22-24/2010 . የሚሰጥ ሲሆን 12 ክፍል(የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ) ፈተና ደግሞ ከግንቦት 27 - 30 /2010 . ድረስ ይሰጣል ብለዋል፡፡ 

ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም የፈተናዎች የህትመት ስራ ተጠናቆ በአጠቃላይ 131 የፈተና ስርጭት የጉዞ መስመሮች እና 10 የአውሮፕላን የጉዞ መስመር ተገቢው የፖሊስ ጥበቃና አጀባ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
2709 10 እና 993 12 በድምሩ 3602 የፈተና ጣብያዎች የሚገኙ ሲሆን በዘንድሮው ፈተና በጠቅላላው 1,222 ,956 10 ክፍል ተፈታኞች፣ 284,558 12 ክፍል ተፈታኞች 3,467 የፈተና ጣቢያዎች እንደሚፈተኑ ታውቋል፡፡ 
የፈተና ስራው በታቀደለት ሁኔታ ፍፁም ሰላማዊ እንዲሆንና ከፈተና ስነ-ምግባር ውጪ እንዳይሆን 77,222 በላይ የሰው ሃይል በቅንጅት እንደሚሰራና ድሬዳዋን ጨምሮ በአራቱ ዋና ዋና ክልሎች ክላስተር ማዕከላት ተቋቁመው የፈተናው ስራ ክትትል እንደሚደረግበት ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

የፈተና አሰጣጡ በተረጋጋና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማከናወን እንዲቻል በፈተና አስፈጻሚነት ለሚሰማራው የሰው ሃይል እና ለተፈታኞች ተከታታይ ገለጻና ኦሬንቴሽን በየደረጃው የተሰጠ ሲሆን ማህበረሰቡ ልጆቹን የተሳሳተ የፈተና መልስ አባዝተው ከሚበትኑና የተፈታኞችን ስነ-ልቦና ከሚረብሸ ማንኛውም ድርጊት እንዲከላከል እንዲሁም ኩረጃ የአገር ፀር እንደሆነ መምከር እንዳለበት አቶ አርዓያ ማስገንዘባቸውን የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዘግቧል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡