ወሎ ዩኒቨርሲቲ፡ የ2010ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ በዓል፡

ወሎ ዩኒቨርሲቲ፡ የ2010ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ በዓል፡

ተመራቂ ተማሪዎች በተጀመረው የመደመር፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የይቅርታ ዘመን በንቃት በመሳተፍ ለሀገራቸው ሁለንተናዊ ለውጥ የዲርሻቸውን እንዲወጡ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አስገነዘቡ፡፡

የወሎ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 4362 ተማሪዎችን 2ኛና በመጀመሪያ ዲግሪ ለአስረኛ ጊዜ ባስመረቀበት ወቅት የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ክቡር / አባተ ጌታሁን እንደገለፁት ሊከፋፍሉን ለሚፈልጉ አካላት ጀርባችንን በመስጠት አሁን የተጀመረው የመደወር፣የመደመር እና የለውጥ ምህዋር ጋር በጋራ ከተባበርን መሻገር የማይቻል ችግር እንደለለ ገልፀው ተመራቂ ተማሪዎችም በፍቅር እና በአንድነት በህብር በመኖር ለሀገራቸው ሁለንተናዊ ልማት የጎላ አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

የእለቱ የክብር እንግዳ የልብ መርጃ ማዕከል መስራችና ዋና ዳይሬክተር / በላይ አበጋዝ በበኩላቸው ተመራቂ ተማሪዎች በንድፈ-ሃሳብና በተግባር የቀሰሙትን እውቀት ተግባር ላይ በማዋል ሀገራቸውን በታታሪነትና በቅንነት ማገልገል እንደሚገባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በዕለቱ በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂዎች ከዕለቱ የክብር እንገዳ ከዶ/ በላይና ከዩኒቨርሲቲው የስራ ሃላፊዎች የሜዳሊያና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ዩኒቨርስቲው በዋናው ግቢና በኮምቦልቻ ካምፓስ ካስመረቃቸው 4382 ተመራቂ ተማሪዎች መካከል 34.45% የሚሆኑት ሴቶች ናቸው፡፡

1999 . 760 ተማሪዎችን በመቀበል ስራ የጀመረው የወሎ ዩኒቨርስቲ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በግብርና ሳይንስ፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ በህክምናና ጤና ሳይንስ፣ በተፈጥሮ ሳይንስ፣ በማህበራዊ ሳይንስና ሰብአዊ በመምህራን ትምህርትና ስነ-ባህሪ ኮሌጆች እንዲሁም በህግና በእንስሳት ህክምና /ቤቶች በመደበኛና በተለያዩ ፕሮግራሞች 25 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡


News

ትምህርት ሚኒስቴር ተፈናቅለው ለነበሩ ተማሪዎች የአልባሳትና የመማሪያ መሳሪያዎች ድጋፍ አደረገ።

ትምህርት ሚኒስቴር በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን እና በደ/ብ/ብ/ህ/ክልል በምዕራብ ጌዲዮ ዞን አዋሳኝ አካባቢ በተፈጠረው ግጭት ተፈናቅለው ለነበሩ ተማሪዎች የአልባሳትና የትምህርት መማሪያ መሳሪያዎች ድጋፍ አደረገ።

የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ-ካርታ ፎረም ተጀመረ፤

ከትምህርትና ስልጠና ዘርፉ የሚመነጩ ችግሮችን ከመሠረቱ በመፍታት ሥራ የሚወድ ፣ ሌብነትን የሚጠየፍና ለህዝብና ለአገር የሚሰራ ባለሙያና አመራር በመፍጠር የተሻለች ኢትዮጵያን መገንባት እንደሚገባ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ አስገነዘቡ፡፡

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።