የ2010 ትምህርት ዘመን ሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

የ2010 ትምህርት ዘመን ሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ 2010 . ትምህርት ዘመን ሀገር አቀፍ 10 እና 12 ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና አሰጣጥ ሂደት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቢሾፍቱ ከተማ ውይይት አካሄደ፡፡ በእለቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ /እግዚኣብሄር የፈተናውን ጥራትና ደህንነት ማስጠበቅ እንዲሁም በአግባቡ ፈተናውን ሰጥቶ ውጤቱን ለተማሪዎች መግለጽ ከፈተና ጋር የተያያዙ ሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች መሆናቸውን እና እነዚህኑ ጉዳዮች መሠረት በማድረግ የዘንድሮ ፈተናዎች ከሌላው ጊዜ በተለየ የፈተና አይተም ባንክን በመጠቀም በጥንቃቄ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡ በቀሪ ጊዜያት የፈተናዎቹን ደህንነት ጠብቆ አጓጉዞ በአግባቡ ፈተፈናውን ሰጥቶ የተማሪዎችን ውጤት እስከ መመለስ ድረስ ያሉ ፈታኝ ሥራዎች የግድ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሠራት ያለባቸው ሥራዎች በመሆናቸው ይህ የምክክር መድረክ ማስፈለጉን ገልጸዋል፡፡
የእለቱ የክብር እንግዳና የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አቶ መሀመድ አህመዲን በበኩላቸው የዚህ የምክክር መድረክ ዋና ዓላማ የትምህርት ዘመኑ ማጠቃላያ የሆኑትን ሁለቱን ብሔራዊ ፈተናዎች በውጤታማነት ለማጠናቀቅ የጋራ አቅጣጫ የምንይዝበት መሆኑን ገልፀው የተማሪዎችን ፈተና የመውሰድ መብት ፍፁም ሰላመዊና ከኩረጃ በፀዳ መልኩ ለማስከበር ሁሉም ባለድርሻ አካላት በባለቤትነት ስሜት ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚገባቸው አሳስበዋል ፡፡
በመድረኩ ለውይይት መነሻ የሚሆን ሰነድ በአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አረጋ ማማሩ ያቀረቡ ሲሆን ከተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያያቶች ተነስተው በሚመለከታቸው ኃላፊዎችና በክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ ከሁሉም ክልሎችና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደር የተውጣቱ የትምህርት አመራሮች ፣የፈተና ክፍል ሃላፊዎች፣ፖሊስ ኮሚሽነሮች፣የፋይናንስ ኃላፊዎች፣የመምህራን ማህበር ተወካዮች፣የአስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊዎች ናቸው፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡