Back

የ2010 አዲስ ዓመት አቀባበል አስመልክቶ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች የብሔራዊ ሙዚየም ጉብኝት አደረጉ

የ2010 አዲስ ዓመት አቀባበል አስመልክቶ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች የብሔራዊ ሙዚየም ጉብኝት አደረጉ


ጉብኝቱ ለሠራተኞቹ እንዲያመች ተብሎ በሁለት ፈረቃ የተከፈለ ሲሆን ከፍል ሠራተኞች ከጠዋት 300 እስከ 500 ሰዓት የተቀሩት ከሰዓት በኃላ 830 እስከ 1030 ተከፋፍለው ጉብኝቱን አካሂደዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት ስለ ጉብኝቱ የጠየቅናቸው አንዳንድ ሠራተኞች በሁኔታው በጣም እንደተደሰቱና እንደተደነቁ ገልጸው አስያየታቸውን እንደሚከተለው አብራርተዋል፡፡እኛ ኢትዮጵያውያን የራሳችን የሆነውን ቅርስ የመንከባከብና የመጎብኘት ልምድ የለንም፤ በተዘዋዋሪ ከሌሎች አካላት በብዛት ከአገር ውጭ ዜጎች ጎብኝዎች አድናቆታቸውን ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሲያወሩ ወይም ሲገልጹ እንሰማለን እንጂ በቦታው ላይ ተገኝተን እንደ ዛሬው ጉብኝት ትኩረት በመስጠት የባለቤትነት ስሜት ተሰምቶን የመጎብኘት ልምድ የለንም ይላሉ፡፡ ሆኖም ግን እንደዚህ ዓይነቱ የቸልተኝነት ባህል ተቀርፎ የሰው ዘር መገኛና የብዙ ሺህ ዘመናት ቅርስና ታሪክ ባለቤት የሆነች አገራችን ኢትዮጵያን እራሳችን አውቀን ሌሎችን የማሳወቅ ሀላፊነት አለብንበማለት አብራርተዋል፡፡
በመጨረሻም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ 2010 አዲስ ዓመት አቀባበል ያቀዳቸውን በርካታ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች እስከ ጳጉሜ 5/2009. ድረስ በአርአያነት እንደሚያከናውንና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ቀጣይነት እንዲኖራቸው ለማስቻል አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡


Communication and Media Communication and Media

Communication Address:

Tel: +251-11-156-14-94

Fax: