የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የ2009 በጀት አመት የ6 ወራት እቅድ አፈጻፀም ግምገማ በኮምቦልቻ ከተማ ተካሄደ

የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የ2009 በጀት አመት የ6 ወራት እቅድ አፈጻፀም ግምገማ በኮምቦልቻ ከተማ ተካሄደ

የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ መደበኛና መደበኛ ባልሆነ የትምህርት አሰጣጥ የሚካሄድ ሲሆን ቅድመ መደበኛ ትምህርትን የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን እንዲሁም የጎልማሶች ትምህርትን ያጠቃልላል፡፡

በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ እንደገለጹት የግምገማ መድረኩ 2008 በጀት አመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማን መሠረት በመድረግ በተካሄደው 26ኛው የትምህርትና ስልጠና ጉባኤና በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ላይ የተነሱ የውይይት  ነጥቦችና ውሳኔዎችን መነሻ በማድረግ በተያዘው የመጀመሪያ ግማሽ አመት በዘርፉ የተከናወኑ ስራዎችን ለመገምገምና በእቅድ አፈጻፀም ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት ቅድሚያ ትኩረት ለሚሹ ጉዳዮች የመፍትሄ አቅጣጫ ለመጠቆም ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡     

ክቡር / ጥላዬ አክለውም የአጠቃላይ ትምህርት ስራዎችን በአግባቡ ለማሳለጥና የሚጠበቀውን ውጤት ለማስመዝገብ  በሁሉም ክልሎች ለናሙናነት በተመረጡ ዞኖች፣ ወረዳና ትምህርት ቤቶች በሶስት ቡድን  የመስክ ጉብኝት ስራ የተከናወነ መሆኑን   ጠቁመዋል፡፡

በመስክ ሱፔርቪዥን ሂደት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ከህዝብ ክንፍ አካላት የተውጣጡ ባለሙያዎችና ኃላፊች  ተሳታፊ ሲሆኑ 10 የተለያዩ ዞኖች፣በ28 ወረዳዎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና በወረዳ  ትምህርት / ቤት የጎልማሶች ትምህርት አመቻች በመጎበኘት ለስራው ግብዓት የሚሆኑ መረጃን መሰባሰብ መቻሉን ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አስገነዝበዋል፡፡

የቅድመ መደበኛ ትምህርት ተሳትፎ ጋር ተያይዘው የታቀደው 80 በመቶ ለማድረስ ቢሆንም አሁን ያለበት ደረጃ 52 በመቶ ነው፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ጥቅል ተሳትፎ 82 በመቶ መሆኑን በመግለፅ የተማሪ መጽሀፍ ጥምርታ 11 መዳረስ መቻሉን ከሴት አመራር ጋር ተያይዞ በቀጣይ 1020 ሴት አመራሮች ወደ ስልጠና እንደሚገቡ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡

በቀሪው የእቅድ አፈጻፀም ወራት  የትምህርት ፍትሃዊነት፣ ተገቢነትና  ጥራት  በሚፈለገው ደረጃ ለማሳደግ በተቀናጀ ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት፣ በታዳጊ ክልሎች የሚታዩ የመጠነ ማቋረጥና መድገም በልዩ ፍላጎት ትምህርት፣  በመረጃ ልውውጥ ጥራትና ወቅታዊነት፣   በሰላማዊ የመማር ማስተማር ላይ የሚታዩ ክፍተቶች  እንዲሁም በቂና ብቃት ያላቸው መምህርን ለማፍራት  ሁሉም ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባም ዶክተር ጥላዬ አስገንዝበዋል፡፡

 የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ይልቃል ከፍአለ የእንኳን ደህና መጣችው መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት እንደተናገሩት መንግስት የትምህርት ዕድል ለዜጎች ለማዳረስ  መጠነ ሰፊ ስራ እየሰራ መሆኑን በመግለፅ አማራ ትምህርት ቢሮም የተቀመጡ ትምህርት ግቦች ለማሳካት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ የሚገኙ 9 በላይ ትምህርት ቤቶች 150 መምህራን እና 5 ሚሊዮን የሚጠጉ የአጠቃላይ ትምህርት ተማሪዎችን በመያዝ እንዲሁም ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም  አቶ ይልቃል ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ተሳታፊዎች በበኩላቸው በተያዘው  በጀት አመት 6 ወራት እቅድ አፈጻፀም ሂደት በተላይም በትምህርት ቤቶች ደረጃ ምደባ፣ በመረጃ ልውውጥ ጥራትና ወቅታዊነት፣   በተቀናጀ ተግባር ተኮር  የጎለማሶች ትምህርት፣ ከትምህርት ግብዓት አኳያ እንዲሁም በልዩ ፍላጎት ትምህርት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ለመፍታት መስራት እንደሚገባችው ተናግረዋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግት ኮምቦልቻ  ከተማ ከጥር 23-24 /2009 . በተካሄደው የግምገማ መድረክ የትምህርት ሚኒስቴር፣ የሁሉም ክልሎችና ሁለቱ ከተማ  አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የተውጣጡ ኃላፊዎችና ባሙያዎች እንዲሁም የህዝብ ክንፍ  አካላት ተሳታፊ ሆኖዋል፡፡

በመድረኩ 2009. 6 ወራት እቅድ አፈጻፀም የቁልፍና የዓበይት  ተግባራት አፈጻፀም፣ የመስክ ሱፐርቪዥን ሪፖርት ቀርቦ በጥልቀት የተገመገመ ሲሆን በግምገማው ሂደት የተለዩ ክፍተቶችን በቀሪው ጊዜያት ለማጥበብ ብሎም ለማስወገድ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡


News

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡