የ2009 የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ይፋ ሆነ

የ2009 የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ይፋ ሆነ

በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ በመደበኛና በማታው የትምህርት መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ለተከታተሉ ተማሪዎች ለወንዶች 354 እና በላይ፤ ለሴቶች 340 እና በላይ፣ ሁሉም የግል ተፈታኝ ወንዶች 360 እና በላይ፤ ለሴቶች 355 እና በላይ፣ በአወንታዊ ድጋፍ መሰረት ለታዳጊና የአርብቶ አደር ተማሪዎች ለወንዶች 340 እና በላይ፤ ለሴቶች 335 እና በላይ፣ ሁሉም መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች ወንዶችም ሴቶችም 297 እና በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ይመደባሉ፡፡

በማህራዊ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ ሁሉም መደበኛና የማታው የትምህርት መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ለተከታተሉ ተማሪዎች ለወንዶች 330 እና በላይ፤ ለሴቶች 320 እና በላይ፣ ሁሉን የግል ተፈታኝ ወንዶች 360 እና በላይ፤ ሴቶች 355 እና በላይ፣ በአወንታዊ ድጋፍ መሰረት ለታዳጊና አርብቶ አደር ተማሪዎች ለወንዶች 320 እና በላይ፤ ለሴቶች 315 እና በላይ፣ ሁሉም መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች ወንዶችም ሴቶችም 275 እና በላይ፣ ሁሉም ዓይነስውራን ተማሪዎች ወንዶችም ሴቶችም 200 እና በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ይመደባሉ፡፡

በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በቀን፤ በመንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማታ እንዲሁም በርቀት ትምህርት ትምህርታቸውን መከታተል የሚችሉት 295 እና በላይ ውጤት ያስመዘገቡ  ይሆናሉ፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡