በ2009 የትምህርት ዘመን የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የመማር ማስተማር ሂደቱን ሰላማዊና ውጤታማ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል

በ2009 የትምህርት ዘመን የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የመማር ማስተማር ሂደቱን ሰላማዊና ውጤታማ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል

በ2009 የትምህርት ዘመን የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የመማር ማስተማር ሂደቱን ሰላማዊና ውጤታማ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ አስታወቁ፡፡

በቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ ስራው የ20007 ዓ.ም እና የ2008 ዓ.ም የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ እቅድ አፈፃፀም ከትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትሀዊነት፣ ጥራትና ተገቢነት አንፃር ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ለመገምገም እንዲያስችል የንቅናቄ ሰነድ በማዘጋጀት ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች፣ የዞንና ወረዳ አመራሮችንና የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ተገምግሞ ወደ ስራ መገባቱን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው የ2009 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማሩን ሂደት ስኬታማ ለማድረግ በባለቤትነት ለመንቀሳቀስ በሚያስችልበት ሁኔታ ላይ ስምምነት መደረሱን ተናግረዋል፡፡ 

በ2009 የትምህርት ዘመን በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ከተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መካከል ከመስከረም 4-22/2009 ዓ.ም ድረስ በተያዘው መርሃ ግብር መሰረት በሃገር አቀፍ ደረጃ መምህራን፣ በየደረጃው ያሉ የትምህርት አመራር አካላትና ባለሙያዎች፣ 36 የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች፣ ለትምህርት ስራ ድጋፍ የሚያደርጉ ሰራተኞች፣ ወላጆችና ከመጀመሪያ ደረጃ ሁለተኛ ሳይክል እስከ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ያሉ ተማሪዎች እያካሄዱት ያለው የውይይት መድረክ አንዱ ነው፡፡

የውይይቱ ዓላማ በተማሪዎች እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ላይ ለውጥ ለማምጣት የታለመ መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር ጥላዬ በዋናነት የውይይቱ ትኩረት የ25 አመታት የትምህርት ዘርፍ እንቅስቃሴን አስመልክቶ፣ በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና አንድ የጋራ ማህበረሰብ መገንባት እንዲሁም የስነ ዜጋና የስነ ምግባር ትምህርት አሰጣጥ ላይ የታዩ ጠንካራ አፈፃፀሞች፣ የተገኙ ውጤቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ እንዲወያዩ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም ግማሽ ሚሊዬን የሚጠጉ የአጠቃላይ ትምህርት መምህራንና የትምህርት አመራር አካላት የሙያ ፍቃድና እድሳት መመሪያ አተገባበር ላይ መወያየታቸውንና የውይይት መድረኩ በአብዛኛው ክልሎች የተጠናቀቀ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡ 

የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የመምህራን ሙያዊ ብቃት፣ ዝግጁነትና የትምህርት መሳሪያዎች አቅርቦት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታው በክረምት መርሃ ግብር ከሰርተፍኬት እስከ ሁለተኛ ዲግሪ ለ189 ሺህ 274 መምህራንና የትምህርት አመራር አካላት የደረጃ ማሻሻያ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን የሙያ ማሻሻያን ጨምሮ ለ212 ሺህ 422 መምህራንና የትምህርት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡

ከትምህርት መሳሪያዎች አቅርቦት አንፃርም ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በ745 ሚሊዬን ብር 66.7 ሚሊዬን መፅሀፍት በሰባት ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በትግርኛ፣ በሶማሌኛ፣ በሲዳማፎ፣ በወላይትኛና በሃዲይኛ በማሳተም የተሰራጨ ሲሆን በቀጣይም 59 ሚሊዬን ብር በሚፈጅ ወጪ የማስተማሪያና መማሪያ አጋዥ መፃህፍት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝና እንደሚሰራጭ አስታውቀዋል፡፡
ትምህርትን በቴክኖሎጂ ከመደገፍ አንፃርም እየተደረገ ባለው ጥረት አዲስ የተገነቡ ትምህርት ቤቶች የፕላዝማ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግና አጠቃቀሙ ላይ ስልጠና በመስጠት እንዲሁም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የኢንተርኔት አገልግሎት በአግባቡ እንዲጠቀሙ የማስቻል ስራ መከናወኑንም ዶክተር ጥላዬ ገልፀዋል፡፡

የ2009 የትምህርት ዘመን የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የመማር ማስተማር ሂደቱን ሰላማዊና ውጤታማ ለማድረግ መምህራንና የትምህርት አመራር አካላት የሚከሰቱ ችግሮችን በመለየት እንዲያስተካክሉ እንዲሁም ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት በመላክ ትምህርት እንዳያቋርጡ በማድረግ ረገድ ከመምህራን ጋር በጋራና በቅርበት የመስራት ኃላፊነት እንዳለባቸው ጨምረው ገልፀዋል፡፡

news


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡