አዲግራት ዩኒቨርሲቲ 16,000 ነባርና አዲስ ተማሪዎች ለመቀበል በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ

አዲግራት ዩኒቨርሲቲ 16,000 ነባርና አዲስ ተማሪዎች ለመቀበል በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ

ይህ የተገለጸው በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የአድግራት ዩኒቨርሲቲ የ2009 በጀት አመት የዘግጅት ምዕራፍ አስመልክቶ ለመምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች ለሰባት ተከታታይ ቀናት ስልጠና ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡

የስልጠናው ዋና አላማ ሀገራችን ከሃያ አምስት አመታት ከማሽቆልቆል ጉዞ ወጥታ ወደ ልማትና ዴሞክራሲ ጎዳና የገባችበትን ሂደት ለከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ማህብረሰብ ግንዛቤ ለማስጨበጥና የ2008 በጀት ዓመት አፈጻፀም በመገምገም ተግዳሮቶች ነቅሶ በማውጣት የመፍትሄ አቅጣጫ ለመጠቆም ታስቦ መሆኑን የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዛይድ ነጋሽ ተናግረዋል፡፡አድግራት ዩኒቨርሲቲ

በመድረኩ የትምህርት ልማት ሰራዊት ግንባታ በተመለከተ፣ ትምህርት ጥራት የማረጋገጥ፣ የትምህርት ስራን በአግባቡ ለማሳለጥ ግብዓትን የማሟላት ፣ መልካም አስተዳደር የማስፈን፣ ሰላማዊ የመማር ማሰተማር አካባቢ የመፍጠርና በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚታዩ የኪራይ ሰብሳቢነት ድርጊት የቁጥጥር ስርዓቱን ተከትሎ ተግባራዊ በማድረግ ምንጩን ማድረቅ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በሰፊው ውይይት ተካሄዷል፡፡
የዩንቨርሲቲው ፕሬዝዳንት የተማሪዎች ቅበላን በተመለከተ በሰጡት አስተያየት ተማሪዎች በክልላቸው በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የመመደብ እድላቸው 40 በመቶ ሲሆን ከክልላቸው ውጪ ደግሞ 60 በመቶ እንደሚመደቡ ጠቁመው ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ተማሪዎች ከክልላቸው ውጪ ወጥተው እንዳይሄዱ በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገጾች የሚናፈሱ መረጃዎች መሰረት ቢስና ፈጽሞ ከእውነት የራቀ መሆኑን ተገንዝበው ያለ ምንም ስጋት ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እንዲሄዱ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ከመስከረም 26-30ዓ.ም ለአምስት ተከታታይ ቀናት ለ11,000 ነባር ተማሪዎች እንዲሁም 5,600 ለሚሆኑ አዲስ ተማሪዎች ደግሞ በጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ ስልጠና እንደሚሰጥም ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አክለውም ለተማሪዎች የመኝታ ቤት፣ የምግብና ውኃ አገልግሎት እንዲሁም የመማሪያ ክፍሎችን ጨምሮ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውንም ተናግረዋል፡፡

ከመስከረም 5 እስከ 12/2009ዓ.ም በተካሄደው ስልጠና ከ3,000 በላይ የሚሆኑ የዩኒቨርሲቲው መምህራንና አሰተዳደር ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡