ብቃት ያላቸው ሴት የትምህርት ቤት አመራሮችን ለመፍጠር የሚያስችል የማሰልጠኛ ሰነድ የተዘጋጀ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታወቀ

ብቃት ያላቸው ሴት የትምህርት ቤት አመራሮችን ለመፍጠር የሚያስችል የማሰልጠኛ ሰነድ የተዘጋጀ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታወቀ

በትምህርት ቤቶች የሴት አመራሮችን ቁጥር ከማሳደግ ባሻገር ብቃት ያላቸው ሴት መምህራንን በመመልመል አሰልጥኖ መመደብ የሚያስችል የስልጠና ሰነድ በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ተዘጋጅቶ በሚመለከታቸው የትምህርት ባለድርሻ አካላት ሶስት ቀናት በአዳማ ከተማ እየተገመገመ ነው፡፡

 

ይህ የስልጠና ሰነድ ከአስራ አንድ ዩኒቨርሲቲዎች ከዘጠኝ የመምህራን ትምህርት ማሰልጠኛ ኮሌጆችና ከትምህርት ሚኒስቴር የተለያዩ የስራ ክፍሎች በተወጣጡ አመራሮችና ባለሙያዎች የተዘጋጀ ነው፡፡ 

 

የስልጠና ሰነዱን አስፈላጊነት የገለፁት በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር / አበበች ነጋሽ፤ የስልጠና ሰነዱ ሶስት ፓኬጆችን የያዘ ሲሆን በትምህርት አመራርነት ኢንስትራክሽናል ሊደርሺፕፖሊሲ እና በዘርፈ ብዙ ጉዳዮች የተካተተ ሲሆን በተጨማሪም መሰረታዊ የኮምፒውተር ክህሎት፣የትምህርት መረጃ አያያዝ እና የተማሪ ወላጅ ተሳትፎ ላይ ያነጣጠረ ነው ብለዋል፡፡

 

ዳይሬክተሯ አያይዘውም ከመጪው ጥር  ወር 2009 . ጀምሮ ለተከታታይ 3 ወራት ከሁሉም የሃገሪቱ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 1020 በብቃታቸው የተመረጡ ሴት መምህራን በአቅራቢያቸው በሚገኙ የመምህራን ኮሌጆች በመግባት በዚሁ ሰነድ ዙሪያ በቂ ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጎ ከሚያዚያ ወር  2009 . ጀምሮ በአገሪቱ በሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተጓደሉ የር/መምህራንና /ርዕሰ መምህራን ቦታዎች እንዲመደቡ ይደረጋል ብለዋል፡፡ እነዚህም ሴት ወደ ርዕሰ መምህርነት የሚመጡ መምህራን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ስታንዳርድን መሰረት ባደረገ መልኩ ሁሉም የዲግሪ ምሩቃን መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

 

ከዚህ በፊት ወደ አመራርነት የሚመደቡ መምህራን የሚሰጣቸው ስልጠና በትምህርት ቤት አመራር እና post graduate diploma for school leadership (PGDSL) ሲሆን የአሁኑ የአሰለጣጠን ሂደት ከዚህ  በፊት የሚሰጠውን ስልጠና የሚያስቀር ሳይሆን በተጨማሪነት የሚሰጥ ሆኖ ለየት ባለ መልኩ  ሴት መምህራንን  ረዘም ላለ ጊዜ በትምህርት አመራር፣ በትምህርት ፖሊሲ እና ተዛማጅ ጉዳዪች ላይ ስልጠና እንዲያገኙ መደረጉ ብቃት ያላቸው ሴት የትምህርት ቤት አመራሮችን ለመፍጠር ያስችላል፡፡ በመሆኑም ይህንን የስልጠና ሰነድ ከኢትዮጵያ መምህራን ማህበር፣ ከክልል የትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊዎች ፣የተለያዩ የትምህርት ባለድርሻ አካላትን ጨምሮ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተውጣጡ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ዳይሬክተሮች በጋራ በሰነዱ ግምገማ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡