የመማር ማስተማር ሂደቱ ሰላማዊና ውጤታማ እንዲሆን በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል

የመማር ማስተማር ሂደቱ ሰላማዊና ውጤታማ እንዲሆን በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል

የመማር ማስተማር ሂደቱ ሰላማዊና ውጤታማ እንዲሆን በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል

በበጀት አመቱ የመማር ማስተማር ሂደቱ ሰላማዊና ውጤታማ እንዲሆን በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

 

26ኛው የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ዓመታዊ ሀገር አቀፍ ጉባኤ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰመራ ከተማ  በተካሄደበት ወቅት የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ / ጥላዬ ጌቴ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍን ውጤታማ ለማድረግ በበጀት አመቱ በዝግጅት ምዕራፍ የአጠቃላይ ትምህርት የንቅናቄ መድረክ በማዘጋጀት፣ የመምህራን፣ ወላጆችና ተማሪዎች ስልጠና በማካሄድ እንዲሁም አምስተኛውን የትምህርት ልማት ዘርፍ መርሃ ግብር መሰረት በማድረግ ወደ ተግባር የተገባ መሆኑን ጠቁመው በበጀት አመቱ ሰላማዊና ውጤታማ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር የሚመለከታቸውና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

 

የቅድመ መደበኛ ትምህርት፣ የልዩ ፍላጎትና ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት፣ የመምህራንና የትምህርት አመራርን ማጠናከር እንደሚገባ፣ የመረጃ አያያዝ ስርዓትን ከክልል እስከ ፌዴራል ወጥ ማድረግ  ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታው የትምህርት አመራርና ባለሙያዎች በበጀት አመቱ ሊተገበሩ የተያዙ እቅዶችን በወቅቱ መፈፀም እንደሚገባቸው አስታውቀዋል፡፡

 

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ ኡዳ በበኩላቸው መንግስት ለትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠቱ  በተለይ ወጣቱ ትውልድ ከሃገራችን ነባራዊ ሁኔታ፣ ከህብረተሰቡ ማህበራዊና  ባህላዊ እሴቶች ጋር በማጣጣምና ጥራት ባለው ትምህርትና ስልጠና ራሱን በማነፅ ተወዳዳሪና ሥራ ፈጣሪ ዜጋ እንዲሆን ማስቻሉንና ሀገሪቱን መካከለኛ ገቢ ካላቸው የዓለም አገሮች ተርታ ለማሰለፍ በርካታ ተግባራት እያከናወነ እንደሚኝ ተናግረዋል፡፡

 

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትም የትምህርት ዕድል ተነፍጎት የቆየውን የአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር ህብረተሰብ የትምህርትና ስልጠና እድል እንዲያገኝ በማድረግ ረገድ ሰፊ ስራ መስራቱን የጠቆሙት ኃላፊው በዚህም ህብረተሰቡ የትምህርት ተጠቃሚ ከመሆን ባሻገር በሀገሪቱ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች ተሳታፊ መሆን ችሏል ብለዋል፡፡ 

 

ከጉባኤው ተሳታፊዎች መካከል አንዳንዶች የመማሪያ ማስተማሪያ ግብዓቶች በበቂ ሁኔታ አለመኖር፣  የስነ ዜጋና ስነ ምግባር የሚያስተምሩ መምህራን ስነ ምግባር ላይ ትኩረት ተደርጎ ቢሰራ፣ የትምህርት ቤት አደረጃጀት ማስተካከል እንደሚገባ፣ የልዩ ፍላጎት ትምህርት እንቅስቃሴ ቢኖርም በሚፈለገው ደረጃ ስላልተሰራ ትኩረት ቢደረግበት በሀገሪቱ ትምህርት በፕላዝማ በአግባቡ እየተሰጠ መሆኑ ቢፈተሸ የሚሉና ሌሎች አስተያየቶችን አንስተው ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የዝግጅት ምዕራፍ የቁልፍና አበይት ተግባራት እቅዶች አፈፀፃም ሪፖርት፣ የሱፐርቪዥን የመስክ ምልከታ ሪፖርት፣ የትምህርት ልማት አጋር አካላት ሪፖርትና ሌሎች ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተካሂዷል፡፡

 

ከህዳር 3 እስከ 4/2009 .  በተዘጋጀው የዘርፉ ዓመታዊ ጉባዔ ላይ የክልልና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ኃላፊዎች፣ የትምህርት ሚኒስቴር የስራ ሂደት መሪዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የትምህርት ልማት አጋር አካላት ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡