"ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል"

"ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል"

በ2009 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ፕሬዚዳንቱ አሳሰቡ፡፡

‹‹ወጣቱ ምሁር አዲስ የሀገራችን መፃኢ ዕድል ወሳኝ አካል ነው›› በሚል መርህ ለደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በተጠናቀቀበት ወቅት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አለማየሁ ከበደ እንደተናገሩት በዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር በማድረግ ረገድ የነበረውን መልካም ስም አስጠብቆ የ2009 ዓ.ም የትምህርት ዘመንን በስኬት ለማጠናቀቅ የዩኒቨርቲው ማህበረሰብ ሚና ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡news

ሀገራችን ሰላሟ ተጠብቆ እንድትኖር ማድረግ ተገቢ መሆኑን የገለፁት ፕሬዚዳንቱ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ኢንዲኖር ማድረግ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ሃላፊነት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ምህረት ጀምበር በበኩላቸው በ2008 ዓ.ም አፈፃፀም ላይ የነበሩ ክፍተቶችን በመለየት መፍትሄ ለማስቀመጥ እንዲሁም ጠንካራ ጎናችንን በማስቀጠል የትምህርት ጥራትን ማጎልበት የሚያስችለንን አቅም ለመፍጠር ስልጠናው ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የ2008 ዓ.ም አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት የተደረገበት መሆኑን የገለፁት አቶ ምህረት የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ አንፃር የነበሩ ችግሮች በተለይም በመምህራን፣በተማሪ ላይ የታዩ ችግሮች እንዲሁም የግብዓት አቅርቦት በተመለከተ በጥልቀት በመገምገም በ2009 የትምህርት ዘመን ውጤታማ ስራ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱን ተናግረዋል፡፡

ከስልጠናው ተሳታፊዎች መካከል በዩኒቨርሲቲው የቱሪዝምና ሆቴል ማኔጅመንት መምህር እንዳለማው ክፍሌ እና የሜካኒካል ኢንጅነሪንግ ዲፓርትመንት መምህርት ማርእሸት ሙላት አንደተናገሩት በስልጠናው ላይ የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ላይ በተለይም የትምህርት ጥራትን በተመለከተ ባሉት ጥንካሬና ጉድለቶች ላይ በስፋት መወያየታቸውን ገልፀው መድረኩ ግልፅና አሳታፊ በመሆኑ ለችግሮቻችን መፍትሄ በማስቀመጥ በ2009ዓ.ም የተሻለ አፈጻፀም ለማስመዝገብ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የጋራ መግባባት ላይ ደርሰናል ብለዋል፡፡

ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ በ2009 ዓ.ም የትምህርት ዘመን 2ሺህ815 አዲስ ተማሪዎችን ጨምሮ ከ10ሺህ በላይ ተማሪዎችን በመደበኛነት ተቀብሎ ለማስተማር ቅድመ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ መሆኑንም ከአቶ ምህረት ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡