የአገራችንን ህዳሴ የሚፈታተኑ የትምክህተኝነት፣ የጠባብነት፣ የሃይማኖት አክራሪነትና ኪራይ ሰብሳቢነት አደጋዎችን ለመታገል ዝግጁ ነን

የአገራችንን ህዳሴ የሚፈታተኑ የትምክህተኝነት፣ የጠባብነት፣ የሃይማኖት አክራሪነትና ኪራይ ሰብሳቢነት አደጋዎችን ለመታገል ዝግጁ ነን

የአገራችንን ህዳሴ የሚፈታተኑ የትምክህተኝነት፣ የጠባብነት፣ የሃይማኖት አክራሪነትና ኪራይ ሰብሳቢነት አደጋዎችን ለመታገል ዝግጁ መሆናቸውን የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች አስታወቁ፡፡NEWS

ከመስከረም 5 እስከ 12/ 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የመምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች ግምገማዊ ስልጠና በትናንትናው ዕለት ሲጠናቀቅ የስልጠናው ተሳታፊዎች ባወጡት ባለ ሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ እንዳስታወቁት የዳበረ ኢኮኖሚና የበለፀገ ማህበረሰብ ለመገንባት እንደ አንድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በትምህርትና ቴክኖሎጂ ልማት ሠራዊት በመደራጀት ከፍተኛ ርብርብ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡

የሰራዊት ግንባታ ሥራችን ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፣ ለመልካም አስተዳደር መስፈንና ኪራይ ሰብሳቢነትን ለመዋጋት ያለውን ጠቀሜታ የበለጠ የተረዳንበት ስልጠና ነበረ ያሉት ተሳታፊዎቹ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በየደረጃው እየተሰራ ያለውን ሥራ በጥልቀት በመገምገም ያልተፈቱ ችግሮችን በተቀመጡ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ ተመሰርተው ከፍተኛ ርብርብ እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል፡፡

ብሄራዊ መግባባት ያለው ቀጣይ ትውልድ ለማፍራት የሚያስችልና ጠንካራ ፖለቲካዊና ማህበራዊ አንድነት የተፈጠረባት አገር ለመገንባት የድርሻቸውን የሚወጡ መሆናቸውንም ቃል የገቡት የስልጠናው ተሳታፊዎች የመንግስትና የህዝብ ሀብት እንዲሁም ሕግና ስርዓት በሚፈቅደው መጠን ለሃገራችን እድገትና ለዩኒቨርሲቲያችን ራእይ መሳካት የበኩላችንን አስተዋፅኦ ለማድረግ ቃል
እንገባለን ብለዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲውን ተቋማዊ ለውጥ እውን ለማድረግ እንዲሁም ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን አጠናክሮ በማስቀጠል የሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ እውን ለማድረግ እንደሚተጉም ነው ተሳታፊዎቹ በአቋም መግለጫቸው ያስታወቁት፡፡

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዛይድ ነጋሽ በበኩላቸው ሀገራችን የደረሰችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑ የዘንድሮውን ስልጠና ለየት እንደሚያደርገው ገልፀው ፖሊሲዎቻችንና ስትራቴጂዎቻችን እንዲሁም አፈፃፀማቸውን በተመለከተ ሀገራዊ ግንዛቤን በማስፋት ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደነበረው ተናግረዋል፡፡

newsየትምህርትና ቴክኖሎጂ ልማት ሠራዊት ለመማር ማስተማር ሰላማዊ ሂደት፣ለትምህርት ጥራት፣ለማህበረሰብ ልማት እንዲሁም መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር ዛይድ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በልማት ሠራዊት የታጀበ እንቅስቃሴ ወጥነት ባለው መልኩ እንዲካሄድ በቁርጠኝነት እየሰራ ቢሆንም አሁንም ክፍተቶች በመኖራቸው በተያዘው የትምህርት ዘመን ውጤታማ ስራ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱን ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የሚረዳ ግምገማ በማድረጉ ያልተቀረፉ ችግሮች መኖራቸውን መገንዘብ መቻላቸውን የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ በተያዘው የትምህርት ዘመን ችግሮቹን ለመቅረፍ ከወዲሁ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል፡፡ 

ከሀገራዊ ጉዳዮች በመነሳት የዩኒቨርሲቲውን የ2008 ዓ.ም እንቅስቃሴ በዝርዝር በመገምገም ውይይት መካሄዱን የገለፁት ዶ/ር ዛይድ በ2009 ዓ.ም እቅድ ላይ በጥልቀት በመወያየት ዕቅዱን በተሳካ ሁኔታ ለመፈፀም የሚያስችል

News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡