በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የመምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ውይይትና ሥልጠና እየተካሄደ ነው

በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የመምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ውይይትና ሥልጠና እየተካሄደ ነው

ውይይቱና ሥልጠናው በዩኒቨርስቲው መማር ማስተማር ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየትና የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ ምቹ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲፈጠር የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር ደጀኔ አየለ በስልጠናና በውይይቱ መምህራኑና የአስተዳደር ሠራተኞቹ በዩኒቨርስቲው የውስጥ ጉዳይና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ አስተማሪና ገንቢ የሆኑ ውይይቶችን እንዳደረጉ ተናግረዋል፡፡ፕሮፌሰር ደጀኔ አየለ

የዩኒቨርስቲው የአመራር አካላት፣ የመምህራኑና የአስተዳደር ሠራተኛው ለዩኒቨርስቲው መማር ማስተማር መቃናት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት የሚያሳይ ውይይትና ሥልጠና መሆኑን øሮፌሰር ደጀኔ ጠቁመው ይህም የ2ዐዐ9 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ዕቅድ ትግበራ ላይ ግብዓት ከመሆኑም በላይ የጋራ መግባባት እንዲፈጠር በማድረግ በመማር ማስተማሩ ሂደት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ያግዛል ብለዋል፡፡

ውይይቱ በመምህራንና አስተዳደር ሠራተኞች ላይ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተገለፀ ያለውን ብዥታ የቀረፈና ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን ከዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ምን ይጠብቃል የሚለውን ጥያቄ በተገቢው ሁኔታ በመመለስ የጋራ አስተሳሰብና አንድነት እንዲኖርና በተግባርም እንዲገለጽ የሚረዳና አቅም የሚሆን እንደሆነም ፕሮፌሰሩ አክለው ተናግረዋል፡፡ 

መምህር ሻሎም አሊ እና ሜሮን ተስፋዬ የተባሉት ተሳታፊዎች በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርስቲው ያለበትን ደረጃ በመገምገም በዋናነት የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ከእያንዳንዱ ምን እንደሚጠበቅና የባለፈው ስህተታችንን ሳንደግም ወደፊት እንዴት የተሻለ ውጤት ማምጣት እንዳለብን የሚያነቃቃ ውይይትና ሥልጠና ነው ብለዋል፡፡

አቶ ኢብዱራህማን ሙሳ እና ውብሸት ወርቅነህ የተባሉት የአስተዳደር ሠራተኞች በበኩላቸው ውይይቱና ሥልጠናው ግልጽነት የተሞላበት በመሆኑም በሁሉም የዩኒቨርስቲው ማሕበረሰብ የጋራ መግባባት በመፍጠር ምቹ የመማር ማስተማር ሂደትን ለመፍጠር ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ወልቂጤ ዩኒቨርስቲበመጨረሻም ውይይቱ ለዩኒቨርስቲው ግብዓት በሚሆን መልኩ ተካሂዶ የሚጠናቀቅ መሆኑንና በ2ዐዐ9 የትምህር ዘመን የነባርና የአዲስ ተማሪዎችን ቅበላ ዝግጅታቸውን እንዳጠናቀቁ ገልፀዋል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡