የዩንቨርሲቲው መምህራንና አጠቃላይ ሰራተኞች ውይይት ለማስተማር፣ ለምርምር ስራዎችና ለአስተዳደራዊ ተግባራት አቅጣጫ ያሲዛል

የዩንቨርሲቲው መምህራንና አጠቃላይ ሰራተኞች ውይይት ለማስተማር፣ ለምርምር ስራዎችና ለአስተዳደራዊ ተግባራት አቅጣጫ ያሲዛል

 የጅማ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ፍቅሬ ለሜሳ መምህራንና አጠቃላይ የዩኒቨርስቲው ሰራተኞች በሀገሪቱ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ማድረጋቸው ሲያስተምሩም ሆነ፣ የምርምር ስራ ሲሰሩ እንዲሁም አስተዳደራዊ ተግባራት ሲያከናውኑ ትክክለኛውን አቅጣጫ ተከትለው እንዲሄዱ ያደርጋቸዋል ብለዋል፡፡

ስልጠናና ውይይቱ ከተጀመረበት እለት ጀምሮ ተሳታፊዎቹ ያለገደብ ሀሳባቸውን በመግለጽና ጥያቄዎችን በማንሳት በንቃት መሳተፋቸውን ፕሮፌሰሩ ጠቅሰው በተለይም በውይይቱ ግልጽነት በሚሹ ጥያቄዎች ዙሪያ በውይይት እንዲፈቱና የጋራ ግንዛቤ እንዲፈጠር በማድረግ የትምህርት ልማት ሰራዊት እንዲገነባ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም አክለው ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም ዩኒቨርስቲው በ2009ዓ.ም የትምህርት ዘመን ነባርና አዲስ የሚገቡ ተማሪዎች ለመቀበልም ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑንም ፕሮፌሰር ፍቅሬ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

የዩኒቨርስቲው መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች በበኩላቸው ስልጠናና ውይይቱ ሀገራዊና ተቋማዊ ችግሮችን በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ የላቀ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

በዋናነት ችግሮች ተለይተው የመፍትሄ አቅጣጫ ሲሰጣቸው አገልግሎት አሰጣጡ ጥራት ይኖረዋል ያሉት መምህራንና ሰራተኞች በአገልግሎት አሰጣጡ ረገድ ጥራትን ማረጋገጥ ሲቻል ጥራት ያለው ትምህርትን ለዜጎች በማዳረስ ሁለንተናዊ የሆነውን የሀገሪቱን ልማት ለማፋጠን ያስችላል ብለዋል፡፡

የውስጥና የማህበረሰብ ችግሮች ምንድናቸው የሚለውን ከመለየትና ከመወያየት ባለፈ የእያንዳንዱ የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ኃላፊነት ምንድነው በሚለው ዙሪያ ሰፊ ውይይት ማድረጉ በዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ውስጥ ግልጽነትን በመፍጠር ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዳይደናቀፍ እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡

Jimma


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡