የሰላም ትምህርት ከስነ ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት ጋር አዋህዶ ለመስጠት አውደጥናት ተካሄደ

የሰላም ትምህርት ከስነ ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት ጋር አዋህዶ ለመስጠት አውደጥናት ተካሄደ

ትምህርት ሚኒስቴር ከብራድፎርድ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የሰላም ትምህርት ከስነ ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት ጋር አዋህዶ ለመስጠት አውደጥናት አካሄደ፡፡ ሀገራችን ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ሽግግር በተደረገ ማግስት በሀገሪቱ የተጀመረውን የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባት ይበልጥ ለማሳለጥና መልካም አስተዳደርን በመገንባት እንዲሁም የሀገሪቱን ልማት በማፋጠን ረገድ የራሱን ሚና እንደሚጫወት የታመነበት የስነ ዜጋ ስነ ምግባር ትምህርት ስራ ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡

moe

ከሁሉም የትምህርት ደረጃ ውስጥ ያሉት ወጣት ተማሪዎችን በመልካም ስነ ምግባር ታንፀው እንዲወጡና በሀገር አቀፍ ብሎም በአለም አቀፍ ደረጃ ብቁ፣ ተወዳዳሪ፣ ችግር ፈቺና በዴሞክራሳዊ አስተሳሰብ የበለጸገ እንዲሁም በምክንያት የሚያምን ዜጋ በሚፈለገው ደረጃ ለማፍራት የስነ ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት የጎላ ሚና አለው፡፡

ይህንኑ ለማረጋገጥ ትምህርት ሚኒስቴር በብርትሽ ካውንስል ድጋፍና ከብራድ ፎርድ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ‘ሰላም ትምህርት ለብሄራዊ ዕድገትና የረጅም ጊዜ ሰላም መረጋጋት‘ በሚል ለአንድ አመት የሚቆይ ፕሮጀክት በስነ ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት ጋር አዋህዶ ለመስጠት ታስቦ አውደ ጥናት ከመስከረም 4-6/2009ዓ.ም አካሄዷል፡፡

በትምህርት ማኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ አማካሪ አቶ ብርሃኑ ሞረዳ አውደ ጥናቱን በንግግር በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት የአውደ ጥናቱ አላማ ሰላም ትምህርት በተለያዩ ትምህርት እርከን ያሉ ወጣት ተማሪዎችን በሚገባ ለማስተማር በስነ ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት ጋር አዋህዶ ለመስጠት ለሚደረገው ጉዞ እውን ለማድረግ ከመምህራን፣ ባለሙያዎችና ከዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር ውይይት ለማድረግ ታስቦ መሆኑን ተናግረዋል፡፡Ato Berehanu

አማካሪው ትምህርት በሀገራችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ውሰጥ የበኩሉን አስታዋጾ በማበርከት ረገድ አምራች ዜጋን ለመፍጠር ወሳኝ መሆኑን አውደ ጥናቱን በንግግር ሲከፍቱ ጠቅሰዋል፡፡

አቶ ብርሃኑ የሰላም ትምህርት አቀራረብ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና መልካም እሰተዳደር በሚፈለገው ደረጃ ለማጠናከር እንዲሁም የጋራ የሆኑ መልካም እሴቶች ተከትለው በወጣት ተማሪወች መካከል ሰላማዊ የግጭት አፈታት ባህል ለማዳበርት እንደሚረዳም አማካሪው ገልጸዋል፡፡ 
የትምህርት ፍትሐዊነት፣ ተገቢነትና ጥራት ለማረጋገጥና ብቁ ዜጋ ለማፍራት እንዲሁም በሀገር ደረጃ የተያዘውን የአምስተኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት መርሃ ግብር ለማሳካት የሰላም ትምህርት በሁሉም የትምህርት እርኮኖች መሰጠቱ ጠቃሚ መሆኑን አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ የሰላም ትምህርት ከስነ ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት ጋር ተዋህዶ መሰጠቱን አስመልክቶ አስተያየት በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት የሀገራችን የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ተቻችለውና ተከባብረው የሚኖሩበት ከመሆኑ የተነሳ የቋንቋና የሃይማኖት ልዩነት ያገናዘበ መልካምና የጋራ የሆኑ እሴቶች በመቀመር እንዲሁም አለም አቀፍ ተሞክሮ በመቀንጨብ በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ እንዲካተት መደረጉን ገልጸዋል፡፡

ይህ |የሰላም ትምህርት ፕሮጄክት በሀገራችን አንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭት ምክንያት ያደረገ ሳይሆን ከአራትና አምስት አመታት በፊት ተጀምሮ በስራ መደራረብ ምክንያት የዘገየ መሆኑን ዶ/ር ጥላዬ አስገንዝበዋል፡፡

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል አበበ በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ የስነ ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት ዳራ አሁን ከሚሰጠው ትምህርት ጋር በማነጻጸር ሲያቀርቡ እንደተናገሩት አሁን እየተሰጠ ያለው የስነ ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት በተማሪው ላይ መልካም ስነ ምግባርን ከማስረፅ አንፃር በሚፈለገው ደረጃ ለውጥ ለማምጣትና በተለያዩ የሃይማኖት ተከታዮች መካከል መቻቻልና አብሮ የመኖር ባህልን ለማጠናከር ጉልህ ድርሻ እንዳው ተናግረዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም የሰላም ትምህርት ከመጀመሪያ እስከ ሁለተኛ የትምህርት ደረጃ ከስነ ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት ጋር ተዋህዶ መሰጠቱ ወጣት ተማሪዎች መልካም ስነ ምግባር ተላብሰው፣ ምክንያታዊና ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ይዘው እንዲያድጉ ከማድረጉም ባሻገር ዜጎች ለዘላቂ ልማትና ሰላም ያላቸውን ድርሻ በሚፈለገው መጠን እንዲወጡ ይረዳል ብለዋል፡፡

ከብራድፎርድ ዩኒቨርሲቲ በብሪትሽ ካውንስል ድጋፍ ፕሮፌሰር ኬነት ኦሜጀ የሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተሞክሮ በማቅረብ የሰላም ትምህርት ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ስርዓተ ትምህርት ለማዋሃድ ከተጀመሩ ቅድመ ዝግጅቶች መካከል የወላጅ፣ተማሪ፣መምህሩና የትምህርት ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ለተግባር ምርምር የሚሆን መረጃ ወደ ማሰባሰብ ስራ እንደሚገባም ጠቅሰዋል፡፡

Curriculum Directorአንዳንድ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት አውደጥናቱ በቂ ግንዛቤ እንዳስጨበጣቸው ገልጸው የሰላም ትምህርት የሚፈጠሩ አለመግባባቶችና ግጭቶች በሰላማዊ፣ በውይይትና በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት በስነ ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት ውስጥ መዋሀዱ ለአንድ ሀገር አንድነትና ልማት የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ጊዮን ሆቴል ከመስከረም 4-6 / 2009 ዓ.ም በተካሄደው አውደ ጥናት ከዘጠኙም ክልሎችና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ እንዲሁም ከስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት የተውጣጡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን፣ ባለሙያዎችና መምህራን ተሳትፈዋል።


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡