የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የመምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ውይይት አደረጉ

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የመምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ውይይት አደረጉ

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሀብታሙ ከቡ በዩኒቨርስቲው የተሰጠው ስልጠና ለዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር የ2009 ዓ.ም የመማር ማስተማር ሂደት፣ የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን ለማሰለጥ አቅም እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በበኩላቸው ተማሪዎች ትምህርት ከመጀመራቸው በፊት እንዲህ አይነት የውይይት መደረክ መፈጠሩ ሁሉም የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ትውልድን ለመቅረጽ በሚደረው ጥረት ድርሻ አለኝ ብሎ እንዲያምንና አስተዋጽኦ እንዲያደርግ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡

የውይይት ተሳታፊዎቹ ከቀረቡት ሰነዶች ጋር የተገኛኙ ለመልካም አስተዳደር እንቅፋት የሆኑ የጋራ ማህበረሰብን ከመፍጠር አንጻር ችግር ናቸው የሚሏቸውን እንዲሁም ከትምህርት ጥራት ጋር ከተያያዙ በርካታ ጥያቄዎች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን የጠቀሱት ፕሮፌሰር አፈወርቅ ይህም ሀገሪቱ ያለፈችበትን፣ ያለችበትን እንዲሁም ወደፊት መድረስ ወዳሰበችበት ለቀጣይ ተልእኮ ስኬታማነት እንዴት መሄድ እንዳለባት እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

አንዳንድ የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ውይይቱ አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመፍጠር እንቅፋት የሆኑት መልካም አስተዳደርና ኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮች በማያዳግም ሁኔታ ካልተፈቱ ሀገሪቱ ልትደርስበት ያለመችውን የልማት ግብ ማሳካት እንደማትችል ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ውይይቱ ከተማሪ አቀባባል ጀምሮ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው እንዴት መስተናገድና ደህንነታቸው መጠበቅ እንዳለበት ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ የአዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ውይይት በማካሄድ ላይ ናቸው፡፡፡ አዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምክትል ዲን አቶ ጣሰወ ጉተማ ውይይቱ ፍትሀዊ አሰራርን ለማስፈን፣ የተገልጋይ እርካታን ለማምጣትና ሰላማዊ የስልጠና ዘዴ እንዲኖር ለማድረግ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

ውይይቱ የትምህርት ስትራቴጂውንም ሆነ የሀገሪቱን የፖለቲካ ስርዓት ተከትሎ በሀገሪቱ ወደፊት ሊሻሻሉ የሚገባቸው ጉዳዮች እንዲሻሻሉ በማድረግ ረገድ ሚናው የላቀ እንደሆነም አቶ ጣሰው ጨምረው ገልጸዋል፡፡


News

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡