በልዩ የኮምፒውተር ክህሎት (ጃቫ) የሰለጠኑ ዓይነስውር መምህራንን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመረቁ

በልዩ የኮምፒውተር ክህሎት (ጃቫ) የሰለጠኑ ዓይነስውር መምህራንን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመረቁ

ትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ /ቤት ጋር በመተባበር በአጭር ጊዜ መርሀ ግብር በልዩ የኮምፒውተር ክህሎት (ጃቫ) የሰለጠኑ 120 ዓይነስውር መምህራንን ነሐሴ 27/2008 . በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማንዴላ አዳራሽ አስመረቀ፡፡በልዩ የኮምፒውተር ክህሎት (ጃቫ) የሰለጠኑ ዓይነስውር መምህራንን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመረቁ

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ድጋፍና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሐመድ አቡበከር በምረቃ ስነ ስረዓቱ ላይ በመገኘት ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር መንግስት የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የወጡ ዓለም ዓቀፍ ኮንቬንሽኖችን፤ ድንጋጌዎችንና ስምምነቶችን መሰረት በማድረግ ልዩ ፍላጎት ላላቸውና ለአካል ጉዳተኛ ዜጎች ጥራት ያለው ትምህርትን በፍትሃዊነት ተደራሽና ተጠቃሚ ለማድረግ በቁርጠኝነት በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

ለትምህርት ስራው ዋነኛ ባለቤት የሆነው ትምህርት ሚኒስቴርም በህገ መንግስቱና በትምህርትና ስልጠና ፖሊሲው መሰረት ለልዩ ፍላጎት ትምህርት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በተለይም በመደበኛ /ቤቶች ልዩ ፍላጎት ያላቸውና አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በአካቶ ትምህርት የሚታገዙበትን ስርዓት በመዘርጋት፣ ወደ መምህርነት ሙያ መግባት ለሚፈልጉ አካል ጉዳተኞች በመመልመያ መስፈርቱ መሰረት በልዩ ሁኔታ የሚታዩበትና የሚበረታቱበትን መንገድ በመፍጠርና ከቅጥር በኋላ ለስራ አመች የሆኑ አካባቢዎች እንዲፈጡ በማድረግ ረገድ ትኩረት ተጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

በሀገራችን ከሚገኙ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን መካከል በርካታ ዐይነ-ስውር መምህራን እንደሚገኙ የጠቆሙት አቶ መሐመድ እነዚህ መምህራን እንደ ማንኛውም ዜጋ ዘመኑ ባፈራው ቴክኖሎጂ የመጠቀም መብታቸውን ለማረጋገጥ እንዲሁም በሥራ ላይ ሥልጠና ፍትሐዊና ተደራሽ ከማድረግ ባሻገር የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እገዛው የላቀ በመሆኑ ለመጀመሪያ ጊዜ 2007 . በክረምቱ መርሃ ግብር ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 150 ዓይነስውር መምህራን 45 ቀናት ልዩ የመሰረታዊ ኮምፒውተር (Jaws) ስልጠና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መሰልጠናቸውን ዳይሬክተሩ አስታውሰዋል፡፡

በዛሬው እለትም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የልዩ ፍላጎትና ድጋፍ ሰጭ /ቤት ጋር በመተባበር ከአዲስ አበባና ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች፣ ከኦሮሚያ፣ ከአማራ፣ ከትግራይና ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልሎች ከአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 120 ዓይነስውር መምህራንን በልዩ የኮምፒውተር ክህሎት (Jaws) በማሰልጠን ለምርቃት ማብቃቱን አቶ መሐመድ ተናግረዋል፡፡

ተመራቂ መምህራንም ከስልጠናው ያገኙትን የኮምፒዊተር ክህሎታቸውን በማሳደግ የመማር ማስተማር ሂደቱን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ በማድረግ በኩል ሃገራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ዳይሬክተሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የልዩ ፍላጎት ድጋፍ ሰጭ /ቤት ኃላፊ / ሰውዓለም ፀጋ በበኩላቸው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን መጠቀም ወሳኝ መሆኑን ተናግረው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም ከመደበኛ የመማር ማስተማር መርሀ ግብር በተጨማሪ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት በአጭር ጊዜ መርሀ ግብር ዓይነ ስውር መምህራንን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር ለማስተዋወቅ ካለፈው በጀት ዓመት ጀምሮ በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይም /ቤታቸው እድሉን ያላገኙ አካል ጉዳተኛ ዜጎች የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከአካል ጉዳተኞችና 

ከሚመለከታቸው ሌሎች ማህበራት ጋር በጋራ እንደሚሰራ / ሰውዓለም አስታውቀዋል፡፡

በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የሚሊኒየም መሰናዶ ትምህርት ቤት መምህርት የሆነችው / ይሳለሙሽ ጫኔ ስልጠናው ዘመናዊ 

ቴክኖሎጂን ተጠቅመን መረጃን በቀላሉ እንድናገኝ ከማድረግ በተጨማሪ ኮምፒውተርን በመጠቀም ፈተና ለማዘጋጀት፣ ለማረም በአጠቃላይ የመማር ማስተማር ሂደቱን ቀልጣፋ እንደሚያደርገው ገልፃ ስልጠናውን ያዘጋጁ አካላትን በማመስገን በቀጣይ ተግባራዊ ልምምድ በአግባቡ ለማድረግ እንዲቻልም ትምህርት ሚኒስቴር የላፕቶፕ እገዛ የምናገኝበትን ሁኔታ ቢያመቻች የሚል አስተያየቷን ሰጥታለች፡፡

በደቡብ ክልል ቃጫ ቢራ ወረዳ የሸንሸቾ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት አቶ አረጋ አበባው በበኩላቸው ስልጠናው እንደማንኛውም ዜጋ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስቻላቸው መሆኑን ጠቁመው እድሉን ያላገኙ ዓይነ ስውር መምህራንም የስልጠናው ተከፋይ እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡