ትምህርት ለመጀመር ዘግጅት የምናደርግበት ግዜ ነው

ትምህርት ለመጀመር ዘግጅት የምናደርግበት ግዜ ነው

የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ 2009. የተማሪዎች ምዝገባ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከነሐሴ 23 እስከ ጳጉሜ 03/2008 . ይካሄዳል፡፡

2008 . ክረምቱን አገባደን 2009. አዲስ የትምህርት ዘመን ለመጀመር ጥቂት ቀናት ይቀራሉ፡፡ በነዚህ በቀሩት ቀናት ውስጥ ተማሪዎች ለትምህርት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች የሚያዘጋጁበት ጊዜ ይሆናል፡፡ትምህርት ለመጀመር ዘግጅት የምናደርግበት ግዜ ነው

ከመስከረም 18/ 2009 . ጀምሮ የእውቀት ማዕድ የሆነው ትምህርት ቤት ለሁሉም ተማሪዎች ክፍት ይሆናል፡፡

የትምህርት ፍትሐዊነት፣ ተገቢነትና ጥራት ለማረጋገጥ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀመጠውን ራዕይ ማለትም ሀገራችንን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ የተደራጀ የትምህርት ልማት ሰራዊትና የህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ የማይተካ ሚና አለው፡፡

መምህራን፣ የትምህርት አመራሮችና የትምህርት ማህበረሰብ በሙሉ የትምህርት ጥራት በሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ በሀገር ደረጃ የተያዘውን የአምስተኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት መርሃ ግብር ለማሳካት የጎላ ሚና ይጫወታሉ ተብሎ ይታመናል፡፡

ወደ ትምህርት ገበታ የመጡ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሳያቋርጡ በአግባቡ ተከታትለው እንዲያጠናቅቁ የወላጅ ተማሪ መምህር ህብረት፣ የመምህራን ክትትልና ድጋፍ፣ የትምህርት ባለድርሻ አካላት እንዲሁም መላው ህብረተሰቡ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

እድሜው ለትምህርት የደረሰ አንድም ህጻን ከትምህርት ገበታ ውጪ አይሆንም!


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡