ለትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ውጤታማነት ጠንካራ የልማት ሰራዊት ግንባታ አስፈላጊ ነው

ለትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ውጤታማነት ጠንካራ የልማት ሰራዊት ግንባታ አስፈላጊ ነው

የትምህርትና ስልጠና ዘርፉን ስኬታማና የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ ለማስቻል ጠንካራ ቁመና ያለው የትምህርት ልማት ሰራዊት ግንባታ ላይ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አንዳንድ ክልሎች አስታወቁ፡፡

ክልሎች የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሀገራዊ የህዝብ ንቅናቄ መድረኩን አስመልክቶ በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ 2009 . የህዝብ ንቅናቄ ማቀጣጠያ ሰነድ እና በመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት አፈፃፀም መመሪያ፣ በስነ ዜጋና ስነ ምግባር አተገባበር ሰነድ እንዲሁም በሌሎች ሰነዶች ላይ ውይይት ባካሄዱበት ወቅት ክልሎች ያሉበትን የአፈፃፀም ደረጃ ለማወቅና 2009 . ምን ላይ ማተኮር እንደሚገባቸውና የመማር ማስተማር ሂደቱን የተቃናና ውጤታማ ለማድረግ የሚያግዝ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡34 - 2የትምህርትና ስልጠና

በተለይም ክልሎቹ በሰነዶቹ ላይ ሰፊ ውይይት ማካሄዳቸው ከተቀመጠው ሀገራዊ ግብ አኳያ ያለባቸውን ክፍተቶች ለይተው እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ የትምህርት ፍትሐዊነትን፣ ተገቢነትንና ጥራትን በማስጠበቅ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ያለው፣ በመልካም ሥነ ምግባር የታናፀ ዜጋ፣ ቴክኖሎጂን መፍጠርና ማስፋፋት የሚችል ዜጋ ለመፍጠር አቅም እንደሚሆንላቸው ገልፀዋል፡፡ 

ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ተግዳሮት የሆኑት ለደረጃው ብቁ የሆኑ መምህራንና የትምህርት አመራሮችን በሚፈለገው ደረጃ ለማፍራት የመምህራን ሙያ ብቃት እየተፈተሸ ያለመሄድ እንዲሁም የልማት ሰራዊት ላይ አደረጃጀት የተፈጠረ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ከጠባቂነት የፀዳ የትምህርት ልማት ሰራዊት ያልተፈጠረ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ የትምህርትና ሰልጠናውን የተሳካ ለማድረግ የህዝብ፣ የመንግስትና የድርጅት ክንፍ አካላት ትርጉም ያለው አደረጃጀት ሊፈጥሩ እንደሚገባ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ክልሎቹ ገልፀዋል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡