የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሀገራዊ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ በአዳማ ከተማ አባገዳ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጀመረ

የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሀገራዊ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ በአዳማ ከተማ አባገዳ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጀመረ

ለአራት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው ሀገራዊ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ከሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች፣ ከተለያዩ የህዝብ ክንፍ አካላት እንዲሁም ሌሎች አጋርና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡33 - 2የንቅናቄ መድረክ ተጀመረ

የንቅናቄ መድረኩን መጀመር አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ / ጥላዬ ጌቴ የሃገራችንን ልማትና ዴሞክራሲ የሚያስቀጥል ትውልድ ለመፍጠር በትምህርትና ስልጠና ዘርፉ ትኩረት ተሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱንና አበረታች ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሽፋንን ለማሳደግና የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ባለፉት ዓመታት በተደረገው ጥረት በገጠርና በከተማ በሴቶችና በወንዶች መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ ከመቻሉም በላይ ልዩ ፍላጎት ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የትምህርት ፍትሐዊነት መረጋገጡን / ጥላዬ ጠቅሰው በተለይም የትምህርት ተደራሽ ከሆኑት የሀገራችን ዜጎች አንድ አራተኛ የሚሆኑት በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ውስጥ የሚገኙ ናቸው ብለዋል፡፡

የትምህርት ጥራትን ለማሻሻልም ምርጥ ተሞክሮዎችን ቀምሮ የማስፋትና የአጠቃላይ ትምህርት የጥራት ማረጋገጫ መርሀ ግብር ተነድፎ ስራ ላይ እንዲውል ከመደረጉም በላይ ለደረጃው ብቁ የሆኑ መምህራንን የመመደብ፣ የማሰልጠንና በየጊዜው ብቃታቸውን የማሻሻል ስራ እየተሰራ እንደሆነም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የትምህርትና ስልጠና ፕሮግራሙ ብቃት ባላቸው የትምህርት አመራር አካላት እንዲመራ ማድረግ ወሳኝ በመሆኑ 6 ለሚሆኑ መምህራን የአመራርነት ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ትምህርት በቴክኖሎጂ እንዲደገፍ የማድረግ ጥረት መኖሩንም / ጥላዬ ተናግረዋል፡፡ ከመጠነ ማቋረጥ ጋር ተያይዞ በቅርቡ በሀገራችን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የነበረውን የመጠነ ማቋረጥ ችግር ለመቅረፍ 6 መቶ ሚሊዮን ብር በመመደብ 2.8 ሚሊዮን ተማሪዎችን መመገብ በመቻሉ ትርጉም ያለው የመጠነ ማቋረጥ ችግርን መፍታት ተችሏል፡፡ 

እንዲሁም እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ የመጠነ ማቋረጥ ችግሮችን የመለየትና መፍትሔ የመስጠት ስራ መሰራቱን ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመው በአሁኑ ወቅትም በመጠነ ማቋረጥ ዙሪያ ሀገር አቀፍ ጥናት እንደተጠናና ጥናቱን መሰረት በማድረግም በአዲስ መልክ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡  የትምህርት ቤቶች የውስጥ አደረጃጀትና ግብዓት በማሟላት የኢንስፔክሽን ስታንዳርዶችን በማጠናከር ረገድ የመምህራን ብቃትና ዝግጅት ወሳኝ እንደሆነና ለዚህም ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን / ጥላዬ ጠቅሰዋል፡፡

ትምህርት ቤቶች የሰላም ማበልፀጊያ እንዲሆኑ ከነበሩት 11 ዕሴቶች በተጨማሪ ተማሪዎችን በመልካም ስነ ምግባር ለማነፅና የጋራ ማህበረሰብ ለመገንባት 12ኛነት የሰላም እሴት ተዘጋጅቶ በቅርቡ ተግባር ላይ እንደሚውል ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመዋል፡፡ በቀጣይም በሀገራችን የአንድ ዓመት ቅድመ መደበኛ ትምህርት ለማዳረስ ጅምር ስራዎች እንዳሉ የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው በአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎች ሙሉ በሙሉ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑና እንዳያቋርጡ እንዲሁም ሴት ተማሪዎች ከወንዶች እኩል በሁሉም የትምህርት እርከኖች ውጤታማ እንዲሆኑ በማስቻል የመፃኢዋን ኢትዮጵያ የሚወስኑ ዜጎች ለመፍጠር ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራና ለዚህም ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች <<በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ 2009 . የህዝብ ንቅናቄ ማቀጣጠያ ሰነድ፣ በመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት አፈፃፀም መመሪያ፣ በአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን የትምህርት ቤቶች ትንተና ሪፖርት እንዲሁም የማሽቆልቆል ምዕራፍ ተዘግቶ የእድገት ምዕራፍ በተከፈተበት 25 ዓመታት ጉዞ ውስጥ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚናና ለቀጣይ ተልዕኮ ሊኖረው የሚገባው ቁመና፣ በፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ አንድ የጋራ ማህበረሰብ የመገንባት አስፈላጊነትና በስነ ዜጋና ስነ ምግባር አተገባበር ሰነድ>> ላይ እየተወያዩ ይገኛሉ፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡