በእቅድ ዝግጅትና በለውጥ ስራዎች አተገባበር ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ

በእቅድ ዝግጅትና በለውጥ ስራዎች አተገባበር ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ድጋፍና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ልዩ ድጋፍ ለሚሹ አራቱ ክልሎች በእቅድ አዘገጃጀትና በለውጥ ስራዎች አተገባበር ዙሪያ ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ፡፡ 

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የልዩ ድጋፍና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሐመድ አቡበከር ዳይሬክቶሬቱ በአራቱ ክልሎች /ሶማሌ፣ አፋር፣ ጋምቤላና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ/ 2007 . ባካሄደው የዳሰሳ ጥናት በክልሎቹ የሚታቀዱ እቅዶች የክልሎቹን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ ሳይሆኑ በተለምዶ የሚታቀዱ መሆናቸው፣ ከአገራዊ እቅዱ ጋር የተሳሰረ ያለመሆኑና የለውጥ ስራዎችን በሠራዊት አግባብ አደራጅቶ ከመተግበር አኳያ ክፍተቶች መኖራቸውን ጠቁመው ሰልጠናው ጥናቱን መነሻ በማድረግ የተዘጋጀመሆኑና ሰልጣኞች በእቅድ ዝግጅትና በለውጥ ስራዎች አተገባበር ላይ ትኩረት አድርገው መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

27 - 2በእቅድ ዝግጅትና በለውጥ

የሚታቀዱ ተግባራትን መፈፀም የሚቻለው በየዘርፉ በለውጥ ሰራዊት መደራጀት ሲቻል ነው ያሉት አቶ መሀመድ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የክህሎት፣ የአመለካከትና የግብዓት ችግሮችን በመፍታት፣ ከክልል እስከ ወረዳና ትምህርት ቤት ድረስ አደረጃጀቶችን በመፍጠር፣ በጀትን በአግባቡ በመጠቀምና ለሚታዩ ክፍተቶች መፍትሔ በመስጠት የክልሎቹን የትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትሐዊነትና ጥራት ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባቸው ገልፀዋል፡፡

በቀጣይ ልዩ ድጋፍ በሚሹ ክልሎች በሚገኙ 34 ሞዴል ወረዳዎች የሚዘጋጁ እቅዶች ከክልሎቹ፣ ከሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እንዲሁም ከአምስተኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት መርሃ ግብር እቅድ ጋር ተሳስረው የታቀዱ መሆናቸውንና የለውጥ ስራዎች አተገባበር ያለበን ሁኔታ በልዩ ድጋፍ ባለሙዎች አማካኝነት የመስክ ምልከታ በማድረግ የመገምገምና አቅጣጫ የማስቀመጥ ስራዎች እንደሚሰሩ ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡

አንዳንድ የስልጠናው ተሳታፊዎች እንደገለፁት እቅድ አዘገጃጀት ላይ ውስንነት መኖሩንና ከስልጠናው ግንዛቤ ማግኘታቸውን ጠቁመው የለውጥ ሰራዊት አደረጃጀት ወጥ አለመሆን፣ የተደራጀ የህዝብ ክንፍ አለመኖርና የአመራሩ ቁርጠኛ አለመሆን ተግዳሮቶች በመኖራቸው መፍትሔ ሊሰጥ እንደሚገባ ጠይቀዋል፡፡ በስልጠናው ላይ የትምህርት ተቋማት እቅድ አዘገጃጀት፣ የለውጥ ሰራዊት አደረጃጀት፣ የትምህርትና ስልጠና ሴክተር የልማታዊ መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጓል፡፡

በአዳማ ከተማ ኮምፎርት ሆቴል ከሰኔ 7-14/2008 . በሁለት ዙር በሚካሄደው ሰልጠና ላይ ከሶማሌ፣ አፋር፣ ጋምቤላና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የተውጣጡ 200 የሚሆኑ የወረዳ ትምህርት /ቤት ኃላፊዎች፣ የእቅድና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡