ብቃት ያላቸው መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮችን የማፍራቱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ

ብቃት ያላቸው መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮችን የማፍራቱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ

7 - Developing Teachers - Pic 2

በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት በመምህራንና በትምህርት ቤት አመራሮች የአሰለጣጠን ሂደት መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ግብዓት ለማሰባሰብ በአዲስ አበባ አራራት ሆቴል አውደ ጥናት አካሂዷል፡፡ የኢ... ትምህርት ሚኒስትሩ ክቡርበትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት በመምህራንና በትምህርት ቤት አመራሮች የአሰለጣጠን ሂደት መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ግብዓት ለማሰባሰብ በአዲስ አበባ አራራት ሆቴል አውደ ጥናት አካሂዷል፡፡ የኢ... ትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አውደ ጥናቱን በንግግር ሲከፍቱ በትምህርት ዘርፉ እስካሁን የተገኙ ውጤቶችን ወደ ላቀ ደረጃ በማድረስ ዜጎች በተሟላ መልኩ የትምህርት ተቋዳሽ እንዲሆኑ ከማድረግ በተጨማሪ የትምህርት ጥራቱን ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀው በሃገሪቱ ብቃት ያላቸው መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮችን ለማፍራት በተጠናከረ መልኩ ይሰራል ብለዋል፡፡

የመምህራንና የትምህር ቤት አመራሮች በየደረጃው አቅማቸውን የማጎልበት ስራ እየተሰራ ቢገኝም የምልመላና የአሰለጣጠን ስርዓቱን በመፈተሽ መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮችን በማስተካከል ለተልኳቸው የበለጠ ብቁ ሆነው እንዲገኙ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡የትምህርት ጥራት ችግርን ለመፍታትም ከቅድመ መደበኛ እስከ ዩኒቨርሲቲዎች ድረስ በአግባቡ መፈተሸ እንደሚገባ የጠቆሙት አቶ ሽፈራው መምህራንና የትምህርት አመራሮችም በየደረጃው ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የመመዘን ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡ ለሰው ሃብት ልማታችን ወሳኝ የሆኑት መምህራን የኑሮ ሁኔታቸውን ለማሻሻል፣ መብቶቻቸውንና ጥቅሞቻቸውን ለማስከበር ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትሩ በተለይ ከመኖሪያ ቤት እና ከደመወዝ ጋር ተያይዞ ላሉ ችግሮች የማሻሻያ ስርዓት ተዘርግቶ ጥናት መካሄዱንና በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ በበኩላቸው በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የትምህርት ጥራትን የማስጠበቅ ተግባር ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራ መሆኑን በመግለፅ ከአውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች በሚገኝ ግብአት 1999 . የወጣው የመምህራን ልማት ገዢ መመሪያ እንደሚሻሻል፣ ከቅድመ መደበኛ እስከ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ መምህራን አሰለጣጠን፣ የመምህራን ምልመላ፣ ስምሪት፣ ማትጊያና የሙያ ፍቃድ አስመልክቶ እንዲሁም የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ስልጠና በተከታታይ የሚመዘንበትና ሌሎችም ተካተው አገራዊ የአፈፃፀም ስርዓት ይዘረጋል ብለዋል፡፡

የአውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የመምህራን ጥቅማ ጥቅም ትኩረት ቢሰጠው፣ የመምህራን ልማት ፈንድ ቢቋቋም፣ በትምህርት አመራር ስልጠና የልዩ ፍላጎት ትምህርት ቢካተት፣ ለመምህራን ነፃ የጤና መድህን ቢኖር፣ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ሙያተኞች የምልክትና የብሬል ቋንቋ ላይ ክፍተት ስላለባቸው ችሎታቸውን የሚያመለክት ገዢ መመሪያ ቢኖርና የመምህራን ትምህርት ተቋማት አሰራርና አደረጃጀት ቢፈተሸ የሚሉትን አንስተዋል፡፡

እንዲሁም የትምህርት ቤት አመራሮች የመምህርነት ክህሎት ቢኖራቸው፣ የኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን የሚመዘኑበት ስርዓት ቢፈጠር፣ የመምህራን ልማት ገዢ መመሪያውና የአሰለጣጠን ሂደት ላይ ሊሻሻሉ የሚገባቸው ጉዳዮች በስፋት አቅርበው ውይይት ተደርጓል፡፡

በአውደ ጥናቱ ላይ በሃገሪቱ የመምህርነት ስልጠና የሚሰጡ 22 ዩኒቨርሲቲዎችና 37 የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች የተወከሉ መምህራንና የትምህርት አመራሮች፣ ከመምህራን ማህበር፣ ከህዝብ ክንፍ አካላት ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ትምህርት ቢሮዎችና ከትምህርት ሚኒስቴር የተውጣጡ 300 በላይ የሚሆኑ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አውደ ጥናቱን በንግግር ሲከፍቱ በትምህርት ዘርፉ እስካሁን የተገኙ ውጤቶችን ወደ ላቀ ደረጃ በማድረስ ዜጎች በተሟላ መልኩ የትምህርት ተቋዳሽ እንዲሆኑ ከማድረግ በተጨማሪ የትምህርት ጥራቱን ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀው በሃገሪቱ ብቃት ያላቸው መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮችን ለማፍራት በተጠናከረ መልኩ ይሰራል ብለዋል፡፡

የመምህራንና የትምህር ቤት አመራሮች በየደረጃው አቅማቸውን የማጎልበት ስራ እየተሰራ ቢገኝም የምልመላና የአሰለጣጠን ስርዓቱን በመፈተሽ መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮችን በማስተካከል ለተልኳቸው የበለጠ ብቁ ሆነው እንዲገኙ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡የትምህርት ጥራት ችግርን ለመፍታትም ከቅድመ መደበኛ እስከ ዩኒቨርሲቲዎች ድረስ በአግባቡ መፈተሸ እንደሚገባ የጠቆሙት አቶ ሽፈራው መምህራንና የትምህርት አመራሮችም በየደረጃው ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የመመዘን ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡ ለሰው ሃብት ልማታችን ወሳኝ የሆኑት መምህራን የኑሮ ሁኔታቸውን ለማሻሻል፣ መብቶቻቸውንና ጥቅሞቻቸውን ለማስከበር ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትሩ በተለይ ከመኖሪያ ቤት እና ከደመወዝ ጋር ተያይዞ ላሉ ችግሮች የማሻሻያ ስርዓት ተዘርግቶ ጥናት መካሄዱንና በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ በበኩላቸው በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የትምህርት ጥራትን የማስጠበቅ ተግባር ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራ መሆኑን በመግለፅ ከአውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች በሚገኝ ግብአት 1999 . የወጣው የመምህራን ልማት ገዢ መመሪያ እንደሚሻሻል፣ ከቅድመ መደበኛ እስከ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ መምህራን አሰለጣጠን፣ የመምህራን ምልመላ፣ ስምሪት፣ ማትጊያና የሙያ ፍቃድ አስመልክቶ እንዲሁም የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ስልጠና በተከታታይ የሚመዘንበትና ሌሎችም ተካተው አገራዊ የአፈፃፀም ስርዓት ይዘረጋል ብለዋል፡፡

የአውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የመምህራን ጥቅማ ጥቅም ትኩረት ቢሰጠው፣ የመምህራን ልማት ፈንድ ቢቋቋም፣ በትምህርት አመራር ስልጠና የልዩ ፍላጎት ትምህርት ቢካተት፣ ለመምህራን ነፃ የጤና መድህን ቢኖር፣ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ሙያተኞች የምልክትና የብሬል ቋንቋ ላይ ክፍተት ስላለባቸው ችሎታቸውን የሚያመለክት ገዢ መመሪያ ቢኖርና የመምህራን ትምህርት ተቋማት አሰራርና አደረጃጀት ቢፈተሸ የሚሉትን አንስተዋል፡፡

እንዲሁም የትምህርት ቤት አመራሮች የመምህርነት ክህሎት ቢኖራቸው፣ የኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን የሚመዘኑበት ስርዓት ቢፈጠር፣ የመምህራን ልማት ገዢ መመሪያውና የአሰለጣጠን ሂደት ላይ ሊሻሻሉ የሚገባቸው ጉዳዮች በስፋት አቅርበው ውይይት ተደርጓል፡፡

በአውደ ጥናቱ ላይ በሃገሪቱ የመምህርነት ስልጠና የሚሰጡ 22 ዩኒቨርሲቲዎችና 37 የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች የተወከሉ መምህራንና የትምህርት አመራሮች፣ ከመምህራን ማህበር፣ ከህዝብ ክንፍ አካላት ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ትምህርት ቢሮዎችና ከትምህርት ሚኒስቴር የተውጣጡ 300 በላይ የሚሆኑ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡

News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡