በታዳጊ ክልሎች የሴቶች የትምህርት ተሳትፎ እያደገ መጥቷል

በታዳጊ ክልሎች የሴቶች የትምህርት ተሳትፎ እያደገ መጥቷል

ባለፉት ስምንት ዓመታት በልዩ ድጋፍ መርሀ ግብር ለአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የመጀመሪያ ትምህርት ማስፋፊያ ስትራቴጂ ተቀርጾ ተግባራዊ በመደረጉ የሴቶችን የትምህርት ተሳትፎ ማሳደግ መቻሉን የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በሚኒስቴር /ቤቱ የስርዓተ ጾታ ዳይሬክቶሬት በአራቱ ታዳጊ ክልሎች የሴቶች ትምህርት ተሳትፎና ውጤታማነት ላይ ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ ዳይሬክቶሬቱን ወክለው ንግግር ያደረጉት አቶ መሀመድ አቡበክር በሴቶች የትምህርት ተሳትፎ ውጤት የተመዘገበ ሲሆን ጥራቱን በሚፈለገው ደረጃ በማምጣት ረገድ አሁንም ክፍተቶች ያሉ በመሆኑ ክልሎች ከመቸውም በበለጠ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ በስርዓተ ጾታ ዳይሬክቶሬት የስርዓተ ጾታ የክትትልና ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ እስክንድር ላቀው በበኩላቸው በእነዚህ ታዲጊ ክልሎች ያለውን የስርዓተ ጾታ ክፍተት ለማጥበብ በቀጣዩ አምስት ዓመት የእድገትና ትንስፎርሜሽን እቅድ እና በአምስተኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት መርሀ ግብር የተጠናከረ የክትትልና ድጋፍ ስራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

9 - Access in developing regions increased Pic 1

በምክክር መድረኩ አራቱ ታዳጊ ክልሎች ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ጋምቤላና ሶማሌ ክልሎች 2008 . 6 ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን ለሴቶች ትምህርት ተሳትፎ የተሰሩ ስራዎች፣ ውጤታማነትና ባጋጠሙ ችግሮች እንዲሁም በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ በጋራ መክረዋል፡፡ የአፋር ክልል የሴት ተማሪዎችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትምህርት ንቅናቄ ሳምንት ሴት ልጆች ወደ /ቤት እንዲመጡ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ከመስራት በተጨማሪ ከረጂ ድርጅቶች በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በሶስት 2 ደረጃ ትምህርት ቤት ገቢ ማስገኛ ፕሮጀክት በማቋቋም ለሴት ተማሪዎች የገንዘብ፣ የቁሳቁስና የዩኒፎርም ድጋፍ በማድረግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡

ሴት እጩ መምህራን ቅድመ ስራ ስልጠና እንዲያገኙ፣ ወደ አመራርነት ለሚመጡ ሴት መምህራን የትምህርት አመራር ስልጠና እንዲሰለጥኑ መደረጉ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡ የአማራጭ መሰረታዊ ትምህርት እና በአንደኛ ደረጃ በስራ ላይ ያሉ መምህራን የሴቶች ተሳትፎ 21.5% የደረሰ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ /ቤቶች የሴቶች ተሳትፎ ደግሞ 12.8% ደርሷል፡፡ እንዲሁም በአንደኛ ደረጃ (1-8) /ቤቶች የሴት አመራር ተሳትፎ 9.4% እና በሱፐርቫይዘርነት የሴቶች ተሳትፎ 12.2% መድረሱ በመድረኩ ተገልጿል፡፡

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል /ቤቶች ለሴት ተማሪዎች ብቻ የሚያገለግሉ ቤተ መጽሀፍትና የመጸዳጃ ቤቶች እንዲስፋፉ የማድረግ፣ በህይወት ክህሎትና በሴት ልጆች የራስ መተማመን ዙሪያ ተከታታይ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና የመስጠት፣ ከሴቶች አዳሪ /ቤት ትምህርቱን አጠናቀው የሚወጡ ሴቶችን በየኮሌጆችና በዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ የማድረግ፣ በክልል ደረጃ የሴቶች ማጠናከሪያ ትምህርት አሰጣጥ ወጥና ስልታዊ እንዲሆን የሚያስችል መመሪያ የማዘጋጀት፣ ከረጂ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለሴት ተማሪዎች ለትምህርት ድጋፍ የሚውል ፕሮጀክት እንዲቀረጽ የማድረግና ተጠቃሚ እንዲሆን የማድረግ ስራ መሰራቱ በሪፖርታቸው አመልክተዋል፡፡

በተጨማሪም በት/ቤቶች የሚፈጸመውን ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል የሚያስችል 13 መመሪያና እያወቃችሁ እደጉ በሚል ርእስ 400 መጽሀፍት ህትመት ተከናውኖ ለትምህርት ተቋማት የማሰራጨት እንዲሁም በጀንደር ሪስፖንሲቭ ፔዳጎጂ ላይ 100 መምህራንና 50 የትምህርት ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በመከናወኑ የሴት ተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎና ዉጤታማነት እየተሻሻለ መምጣቱን በውይይት መድረኩ የቀረበው ሪፖርት አሳይቷል፡፡

በሶማሌ ክልል ትምህርት አቋርጠው የነበሩ 600 ሴት ተማሪዎችን ኢንተር አፍሪካ ግሩፕ ኢትዮጵያ ከተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ የዩኒፎርም፣ የትምህርት ቁሳቁሶችና የንፅህና መጠበቂያ እቃዎች ድጋፍ የማድረግ፣ በክልሉ በተመረጡና መደገፍ አለባቸው ተብለው በተለዩ ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ 3000 ሴት ተማሪዎች የኪስ ገንዘብ፣ የዩኒፎርምና የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ የማድረግ፣ ሴት ተማሪዎች ጾታዊ ትንኮሳ ሳይደርስባቸው ትምህርታቸውን ተረጋግተው እንዲከታተሉ በተለያዩ ጊዜያት ለትምህርት ቤት ማህበረሰቡ ስልጠና የመስጠት፣ ለሴት ተማሪዎች የተጠናከረ የማጠናከሪያ ትምህርት የመስጠትና በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ሴት ተማሪዎች በመሸለም ለከፍተኛ ውጤት የማነሳሳት ስራ በመሰራቱ የሴት ተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎ መጨመሩን ሪፖርታቸው አሳይቷል፡፡

ይሁን እንጂ የሴቶችን ትምህርት ከመደገፍ አንፃር የአመራሩ ሚና የሚጠበቀውን ያህል አለመሆን፣ ወደ አመራርነት የሚመጡ ሴቶች ዝቅተኛ መሆንና ወደ አመራርነት ቢመጡም በትምህርት ዘርፉ አለመቆየት እንዲሁም የበጀት እጥረት መኖሩ የሴቶችን እኩል ተሳታፊነትና ጠተቃሚነት በሚጠበቀው ደረጃ ማረጋገጥ አለመቻሉን ሪፖርቱ በዝርዝር አመልክቷል፡፡

በጋምቤላ ክልል የሴቶችን የትምህርት ተሳትፎ እንዲሁም ሴቶችን ወደ አመራርነት ለማምጣት በተደረገው ጥረት ለውጥ የመጣ ቢሆንም በአንደኛ ደረጃ 5-8 ክፍል እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎ ላይ ለሴቶች ትኩረት አድርጎ መስራት፣ የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት ተግባራዊ በማድረግ 20 ሴት ጎልማሶችን ተጠቃሚ ማድረግ፣ የቅድመ መደበኛ እና የልዩ ፍላጎት ትምህርት የሚያስፈልጋቸውን ሴት ህፃናት በአካቶ ትምህርት ተጠቃሚ ማድረግ፣ የሴቶች የመጠነ ማቋረጥ ችግሮችን በመለየት ችግሮቹ ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት መጠነ ማቋረጥ 2007. ከነበረበት በአንደኛ ደረጃ 8 በመቶ እና 2 ደረጃ 5በመቶ ወደ 2 በመቶ ማድረስ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫቸው እንደሆነ ሪፖርታቸው ጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የትምህርት ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ እና ህብረሰተሰቡ ትምህርት ቤቶችን ሴቶች እንዲመራቸው በማድረግ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ፣ 2 ደረጃ ሴት ተማሪዎችን የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ትምህርት ተጠቃሚ ማድረግ፣ የሴት መምህራንን የመልካም አስተደዳር ችግር መቅረፍ፣ ጥቅማጥቅማቸውን በማስከበር መምህራን በትምህርት ጥራት ላይ እንዲሰሩ ማድረግና ሴቶች በትምህርት ቤቶች አደረጃጀት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ አቅማቸውን ማሳደግ የሚሉም ይገኙበታል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡