ዩኒቨርሲቲዎች ከሀገራችን ተጨባጭ ችግሮች በመነሳት ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ ችግር ፈቺ ምርምሮች ማካሄድ አለባቸው

ዩኒቨርሲቲዎች ከሀገራችን ተጨባጭ ችግሮች በመነሳት ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ ችግር ፈቺ ምርምሮች ማካሄድ አለባቸው

12 - HE Meetings DebreBerehan Pic 1

ዩኒቨርሲቲዎች በተፈጥሮ ሃብት ልማት፣ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማስፋፋት ረገድ እያከናወኗቸው ያሉት የጥናትና ምርምር ስራዎች አበረታች ቢሆንም ህብረተሰቡን ባሰተፈ መልኩ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ  የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ካባ ኡርጌሳ አሳስበዋል፡፡ ከጥር28-29/2008 . የተካሄደው 31ኛው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቋማዊ ለውጥ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በመልካም አስተዳደር፣ በትምህርት ልማት ሰራዊት ግንባታ፣ በመማር ማስተማር፣ በማህበረሰብ ልማትና በጥናትና ምርምር ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት ላይ በስፋት መክሯል፡፡

የመልካም አስተዳደር ችግር እንደ ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሁሉ በዩኒቨርሲቲዎቻችንም የሚታይ ችግር መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታው በትምህርት ሚኒስቴርም የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍም ሆነ ዩኒቨርሲቲዎች የመልካም አስተዳደር ማስፈኛ ዕቅድ አቅደው ወደ ተግባር መግባታቸውን ጠቁመዋል፡፡ የሴቶችን ተሳትፎ በሁሉም ደረጃ ለማሳደግ የጀመርነውን ጥረት አጠናክረን በመቀጠል በመምህርነት፣ በተመራማሪነትና በመሪነት ቁጥራቸው እየጨመረ መሄድ ይኖርበታል ያሉት / ካባ ለዚህም የዩኒቨርሲቲዎች አመራርና መላው ማህበረሰብ የተለየ ትኩረት ሊያደርግ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

በጉባኤው ላይ የሀዋሳ፣ ወለጋ፣ ደብረብርሃን፣ ባህርዳር፣ አዲግራት፣ ሚዛንቴፒ እና መቱ ዩኒቨርሲቲዎች ባለፉት ስድስት ወራት በመማር ማስተማር፣ በምርምርና ጥናት እንዲሁም በማህበረሰብ ልማት ያከናወኗቸውን ተግባራትና የለውጥ ስራዎች ያሉበትን ደረጃ የሚያሳይ ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተካሂዷል፡፡  በተጨማሪም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባለፉት ስድስት ወራት በመማር ማስተማር ሂደት የታዩትን ጠንካራና ደካማ ጎኖች በዝርዝር ያካተተ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሱፐር ቪዥን ሪፖርት የቀረበ ሲሆን  ሪፖርቱ በመልካም አስተዳደር፣ በግዥ፣ በሠራተኛ ቅጥር፣ ዕድገትና ዝውውር የሚስተዋሉ ችግሮችን ጠቁሟል፡፡

ተሳታፊዎች በበኩላቸው በቀረበው ሪፖርት ላይ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን ያቀረቡ ሲሆን በተለይም በወረቀት፣ ላፕቶፕና ኮምፒዩተሮች ግዢ አፈጻጸም  የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በዝርዝር አቅርበዋል፡፡  ከግዢ ጋር በተያያዘ ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እንደተናገሩት የቁሳቁስ ግዢ ለሁሉም የፌዴራል ተቋማት በጋራና በአንድ ማዕከል መፈፀሙ ጥራት ያለው ዕቃ ወጪ በሚቀንስ መልኩ ለመግዛት የሚረዳ በመሆኑ አሰራሩ የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመው ይሁንና በግዢ ሂደት የሚያጋጥሙ የአሰራር ችግሮች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

የፌዴራል ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ተገቢውን አገልግሎት እያቀረበ አለመሆኑን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚቀርቡ ቅሬታዎች መኖራቸውን የጠቆሙት ሚኒስትሩ በቀጣይም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ችግሩን  ለመፍታት ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡ በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እንደተናገሩት ባለፉት ስድስት ወራት መልካም አስተዳደርን  ከማስፈን አንፃር በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከተማሪዎች ተሳትፎ፣ ምግብና መኝታ እንዲሁም ግዢ ጋር ተያይዞ ይነሱ የነበሩ ችግሮች መሻሻል እያሳዩ መሆኑን ገልጸው አሁንም ያልተፈቱ ችግሮች በመኖራቸው ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የመልካም አስተዳደር ፓኬጅን መሠረት በማድረግ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዕቅድ አዘጋጅተው ወደ ተግባር መግባታቸውን የገለፁት አቶ ሽፈራው  ውጤታማ ስራ መስራት የቻሉ ዩኒቨርሲቲዎች መኖራቸውንም ጠቁመዋል፡፡ በተማሪዎች፣ በመምህራን፣ በአስተዳደር ሠራተኞች እና በአካባቢው ማህበረሰብ ሲነሱ የነበሩና ቀደም ሲል በሰራተኛ ቅጥር፣ ዕድገትና ዝውውር፣ በተማሪዎች አገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ሲስተዋሉ የነበሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራትና የተገኘውን ውጤት የሚያሳይ የሱፐርቪዥን ሪፖርት ቀርቦም በጉባኤተኞቹ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

የመልካም አስተዳደር ማሻሻያ ፓኬጅን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ተጨባጭ የሆነ ለውጥ ለማምጣት የተደረጉ ጥረቶችን ለመመልከት መድረኩ መዘጋጀቱን አቶ ሽፈራው ጠቁመው የሱፐርቪዥኑ ሪፖርት ጉድለቶች ቢኖሩም አበረታች ለውጦች መኖራቸውን የሚያሳይ በመሆኑ ለውጦቹን አጠናክረን መቀጠል አለብን ብለዋል፡፡

እያንዳንዱ ዩኒቨርሲቲ ሁሉንም የሠራዊት አቅሞች በተደራጀ መንገድ እያንቀሳቀሰ መሆኑን መፈተሽ አለበት ያሉት ሚኒስትሩ ባለፉት ዓመታት የተገኙ የትምህርት ልማት ሠራዊት መልካም አፈፃፀሞች ላይ ጥናት በማካሄድ ሊሻሻሉና ሊጠናከሩ የሚገቡ ጉዳዮችን መለየት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር / ካባ ኡርጌሳ እያንዳንዱ ዩኒቨርሲቲ ከሚያከናውነው መደበኛ ተግባር በተጓዳኝ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ላይ ሊያተኩር እንደሚገባ  ተናግረዋል፡፡

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለጥናትና ምርምር ስራዎች ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ያሳሰቡት / ካባ ለዚህም የዩኒቨርሲቲ የምርምር ምክትል ፕሬዚዳንቶችን ያካተተ የምርምር ካውንስል መቋቋሙን አስታውቀዋል፡፡ እያንዳንዱ ዩኒቨርሲቲ ከፕሮፖዛል ጀምሮ እስከ ቴክኖሎጂ ሽግግር ድረስ የሚዘልቅ የምርምር ስራ ለመስራት ማቀድ እንዳለበት የተናገሩት / ካባ  በቀጣይ መልካም ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ የሚረዱ መድረኮች እንደሚዘጋጁም አስታውቀዋል፡፡ መልካም አስተዳደርን በተመከለተ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ለውጥ እየታየ ቢሆንም  ከዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ምላሽ የማይሰጡ አመራሮች መኖራቸውን ነው / ካባ የጠቆሙት፡፡  በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች ለሚነሱ ቅሬታዎች በቂ ምላሽ በመስጠት ለሌሎች ተቋማት አርአያ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው ቲቶሪያል ትምህርት ለሴቶች በሚፈለገው መጠን አየተሰጠ እንዳልሆነ የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታው በማንም በጎ ፈቃድ የሚሰጥ ሳይሆን ህገ መንግስታዊ መብት በመሆኑ የግድ መተግበር አለበት ብለዋል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡