የተቀናጀ የትምህርት ቤት የጤናና የምገባ ፕሮግራም የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የገዘፈ ሚና አለው

የተቀናጀ የትምህርት ቤት የጤናና የምገባ ፕሮግራም የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የገዘፈ ሚና አለው

የተቀናጀ የትምህርት ቤት የጤናና የምገባ ፕሮግራም ተማሪዎች በተለይም በመጀመሪያ ደረጃ የሚማሩ ህፃናት በምግብ እጥረትና በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ ከማድረጉም ባሻገር በክፍል ውስጥ ትምህርታቸውን በንቃትና በትኩረት እንዲከታተሉ በማድረግ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የገዘፈ ሚና አለው፡፡

በዚህም መነሻነት የኢፌዴሪ /ሚኒስቴር ፖርነትነርሽፕ ፎር ቻይልድ ዴቨሎፕመንት ከተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር የተቀናጀ የት/ቤት ጤናና ምገባ ፕሮግራም ማስተግበሪያ ሰነድ አዘጋጅቶ ስራ ላይ እንዲውል አድርጓል፡፡ የሰነዱ መዘጋጀት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትን የእርስ በእርስ ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር በማድረግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ያደርጋል፡፡school feeding

ሰነዱ ተዘጋጅቶ ስራ ላይ እንዲውል ከተደረገ 6 ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን በዚህ ወቅትም በየደረጃው ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ መፍጠር (Advocacy) እና የአቅም ግንባታ ተግባራት ሲከናወን ቆይቷል፡፡ ይህም የተሻለ መነቃቃትን በመፍጠር ቀደም ብለው በተለያዩ የሚመለከታቸው አካላት የተጀመሩት የተቀናጀ የት/ቤት ጤናና ምገባ ፕሮግራም ውጤት በማምጣት ላይ ይገኛል፡፡

ሚኒስቴር /ቤቱ ፕሮግራሙን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ከነሐሴ 24 - 25/2008 . "ጤናማ መሆን ለመማር ለመማር ጤናማ መሆን" በሚል መሪ ሀሳብ ከሚመለከታቸው አጋርና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅቶች ጋር በመተባበር የምክክር አውደ ጥናት አዘጋጅቷል፡፡ የምክክር አውደ ጥናቱ ይህንን የተቀናጀ የት/ቤት ጤናና ምገባ ፕሮግራም በሚተገበሩ አካላት ያለው የቅንጅት ስራ ምን እንደሚመስል፣ በአፈጻጸም የታዩ ክፍተቶችን ለመለየትና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በጋራ ለማስቀመጥ ያለመ ነው፡፡

በትምህርት ማኒስቴር የእቅድ ዝግጅትና ሀብት ማፈላለግ ዳይሬክቶሬት አቶ እሽቱ አስፋው የተቀናጀ የት/ቤት ምገባና የጤና ፕሮግራም ጤናማና አምራች ዜጋን ለመፍጠር ወሳኝ መሆኑን አውደ ጥናቱን በንግግር ሲከፍቱ ጠቅሰዋል ፡፡

ተማሪዎች ትምህርታቸው ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲማሩ ለመማር ማስተማሩ እንቅፋት ከሆኑ ችግሮች በተለይም ከተለያዩ በሽታዎች እንዲጠበቁ ማድረግና አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠት ተገቢ እንደሆነ የገለፁት አቶ እሽቱ ለዚህም ነው በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ የተቀናጀ የት/ቤት ጤናና ምገባ ማስተግበሪያ ሰነድ እንዲዘጋጅና ወደ ተግባር እንዲገባ የተደረገው ይላሉ፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የት/ቤት መሻሻል ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ያሳቡ ብርቅነህ በበኩላቸው ፕሮግራሙን ሊመራና ሊያስተባበር የሚችል ራሱን የቻለ አደረጃጀት ባለመኖሩ ይህ የተቀናጀ የት/ቤት ጤናና ምገባ ፕሮግራም ምን ያህል በት/ቤቶች ላይ በአግባቡ እየተተገበረ መሆኑን ክትትል ማድረግ አለመቻሉን ተናግረዋል፡፡

በሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እየተተገበረ ያለውን የተቀናጀ የት/ቤት ጤናና ምገባ ፕሮግራም ከመምራት፣ ከማስተባበርና ክትትል ከማድረግም በተጨማሪ ለፕሮግራሙ ስኬታማነትና ቀጣይነት አጠቃላይ ፕሮግራሙን የሚመራ አካል ሊኖር እንደሚገባም አቶ ያሳቡ አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

በቀጣይም የቅንጅት ስራዎችን ማጠናከር፣ በወርክሾፑ የተነሱ ክፍተቶችን ለመሙላት ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበትና የተጠናከረና ቀጣይነት ያለው የመረጃ ልውውጥ ማድረግ እንዲሁም በፕሮግራሙ ላይ ግንዛቤ የመፍጠር በተለይም በሚመለከታቸው የአመራር አካላት ትኩረት እንዲስጥ ግንዛቤ መፍጠር ተገቢ እንደሆነም አቶ ያሳቡ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

በአውደ ጥናቱ በት/ቤቶች አካባቢ የህፃናትን የመማር ማስተማር ሂደት የሚያደናቅፉ በሸታዎችን ለአብነት የብልሀርዝያና ሻስቶሶሚያሲስ እንዴት መከላከል እንደሚቻልና ስለሚሰጠው ህክምና፣ የእይታ ችግር ያለባቸውን ተማሪዎች የመለየትና መፍትሄ የመስጠት እንዲሁም ከኢልኒኖ ጋር ተያይዞ ድርቅ በተከሰተባቸው አንዳንድ አካባቢዎች ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ ስለተሰጠው የት/ቤት ምገባ ዙሪያ በተለያዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ቀርቦ ስላስገኘው ጠቀሜታና እንዴት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ውይይት ተደርጓል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡