የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ-ካርታ ፎረም ተጀመረ፤

የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ-ካርታ ፎረም ተጀመረ፤

ከትምህርትና ስልጠና ዘርፉ የሚመነጩ ችግሮችን ከመሠረቱ በመፍታት ሥራ የሚወድ ፣ ሌብነትን የሚጠየፍና ለህዝብና ለአገር የሚሰራ ባለሙያና አመራር በመፍጠር የተሻለች ኢትዮጵያን መገንባት እንደሚገባ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ አስገነዘቡ፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ዝግጅት የመጀመሪያ የህዝብ ውይይት መድረክን በንግግር በከፈቱበት ወቅት እንዳስገነዘቡት የዴሞክራሲ ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ብልጽግና መሠረት የሆነው ትምህርትና ስልጠና የሁሉንም አካል ትኩረት ይሻል፡፡
የኢትዮጵያ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ለትምህርት ሽፋንና ተደራሽነት የሰጠውን ትኩረት ያህል ለፍትሀዊነትና ለትምህርት ጥራት በሚዛናዊነት ትኩረት ባለማድረጉ ዘርፉ የሚጠበቅበትን ያህል መራመድና የሚፈለግበትን ውጤት ማስመዝገብ እንዳልቻለ አስገንዝበዋል፡፡
ለዚህም ዛሬ በአገሪቱ በምህድስናና በኮንስትራክሽን ዘርፉ ፣ በፍትህ ሥርዓቱ ፣ በህክምና፣ በቴክኖሎጂ ፣በሀብት ቁጥጥር ፣ በአገልጋይነት መጓደልና በሌሎችም ዘርፎች የሚስተዋሉ ችግሮች ከትምህርትና ስልጠና ዘርፉ የሚመነጩ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ 
በመሆኑም የመድረኩ ተሳታፊዎች በፍኖተ-ካርታው የረቂቅ ጥናት የሥርዐተ ትምህርቱን ጉድለቶች በአግባቡ በመፈተሽና ነቅሶ ማውጣትና በዘርፉ የተገኙ ውጤቶት ሳይንጠባጠብ ችግሩን ከሥር መሠረቱ እንዲፈታ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የድርሻቸውን ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡ 
ችግሩን ከመሠረቱ መፍታት የሚቻለውም የውጪ ተሞክሮን ሙሉ በሙሉ በመተግበር ሳይሆን ከራሳችን ሀገር በቀል በቀል እውቀት እና ቴክኖሎጂ ጋር በመጠቀም ጭምር ሊሆን እንደሚገባም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡
የኢፌደሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲው አንድም ዘመኑ ከሚጠይቀው ሂደት ጋር አጣጥሞ ያለመምራት ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በአግባቡ የመተግበር ችግር ያለበት በመሆኑ ችግሩን በአግባቡ ፈትሾ ከስር መሰረቱ መፍታት እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ በበኩላቸው የሚዘጋጀው የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ በአገራችን የመጪው 15 ዓመታት አጠቃላይ ዕድገትና ብልጽግና ላይ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመው በፍኖተካርታው የመጀመሪያ የህዝብ ውይይት ተሳታፊዎች ፍኖተካርታው ችግር ፈቺ የዘመነ ትውልድ መፍጠር በሚያስችል መልኩ እንዲበለፅግ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡
የትምህርትና ስልጠና ፍኖተካርታው ጥናት ዛሬ ለደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አመራሮች፣ ተቋማት፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻዎች ምስጋና አቅርበው በውይይት መድረኩም የሁለቱ ምክር ቤት አፈጉባዔዎች ፣ ሚኒስትሮች፣ የክልል መስተዳድሮች ፣ የዴሞክራሲ ተቋማት፣ ትምህርት ሚኒስቴርን ባለፉት 24 ኣመታት የመሩ አመራሮች፣ የኃይማኖት አባቶች ፣ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ ኢንደስትሪዎች፣ ባንኮች፣ አምባሳደሮችና ሌሎችም ባለድረሻዎች ተሳታፊዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

News

ትምህርት ሚኒስቴር ተፈናቅለው ለነበሩ ተማሪዎች የአልባሳትና የመማሪያ መሳሪያዎች ድጋፍ አደረገ።

ትምህርት ሚኒስቴር በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን እና በደ/ብ/ብ/ህ/ክልል በምዕራብ ጌዲዮ ዞን አዋሳኝ አካባቢ በተፈጠረው ግጭት ተፈናቅለው ለነበሩ ተማሪዎች የአልባሳትና የትምህርት መማሪያ መሳሪያዎች ድጋፍ አደረገ።

የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ-ካርታ ፎረም ተጀመረ፤

ከትምህርትና ስልጠና ዘርፉ የሚመነጩ ችግሮችን ከመሠረቱ በመፍታት ሥራ የሚወድ ፣ ሌብነትን የሚጠየፍና ለህዝብና ለአገር የሚሰራ ባለሙያና አመራር በመፍጠር የተሻለች ኢትዮጵያን መገንባት እንደሚገባ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ አስገነዘቡ፡፡

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።