ለትምህርት ጥራት መጠበቅ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ ነው ተባለ፤

ለትምህርት ጥራት መጠበቅ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ ነው ተባለ፤

ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት 27 ዓመታት በቁጥር 2 የነበሩትን ዩኒቨርሲቲዎች የግልን ጨምሮ 150 በላይ በምታሳድግበት ወቅት ተደራሽነቱ ላይ በትኩራት በመስራት በተለያዩ ምክንያቶች የትምህርት ጥራት ክፍተት መፈጠሩን የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ ክቡር / ሣሙኤል ክፍሌ ገለጹ፡፡

ትምህርትና ስልጣኔ ለኢትዮጵያ ህዝብ አዲስ ባይሆንም ዘመናዊ ትምህርት ከተጀመረበት 19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ በይበልጥ በአጼ ኃይለስላሴ እና በደርግ ስርዓቶች ትምህርት ለተወሰኑት ዜጎች ብቻ የሚሰጥ የነበረና አሁንም የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት ካለው የህዝብ ብዛት ጋር ባለመጣጣሙ አስፈላጊውን የኢኮኖሚ ዕድገት በማምጣት እያገዘ እንዳልሆነ / ሣሙኤል ገልጸዋል፡፡በዚህ ምክንያት መንግስት ተደራሽነት ላይ በሚረባረብበት ወቅት ጥራቱ ክፍተት አሳይቷል ብለዋል፡፡

ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የሚተገበረው የተከለሰ የትምህርት ፍኖተ-ካርታ እንዳለ ሆኖ ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ አንጻር የሰው ኃይልና ሌሎች ግብዓቶች ላይ እየሰራ መሆኑን የመምህራንን አቅም ማጎልበት፣ የተማረ ህብረተሰብ በማፍራት ተማሪዎችን ከቤተሰብ ጀምሮ ማስተማር፣ ትምህርት ቤት አከባቢ ያሉ አዋኪ ጉዳዮችን ማስወገድ ተመራቂ ተማሪዎችን የኢንዱስትሪ ገበያ በሚፈልገው መልኩ መዝነው ማውጣት ላይ ትኩረት ሰጥተው እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሆኖም ግን ሁሉንም የትምህርት ጉዳዮች በየዕለቱ ተከታትሎ ማስተካከል ስለማይቻል ሌሎች አስፈጻሚ መስርያቤቶችን ጨምሮ የትምህርት ባለድርሻ አካላት መረባረብ እንደሚጠበቅባቸው / ሣሙኤል ተናግረዋል፡፡


News

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡