በአጭር እድሜ አመርቂ ውጤት በአርሲ ዩኒቨርሲ፤

በአጭር እድሜ አመርቂ ውጤት በአርሲ ዩኒቨርሲ፤

የአርሲ ዩኒቨርሲቲ 2009. ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስር እራሱን ችሎ 3 ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች ተርታ በመሰለፍ በአጭር ዕድሜ ቆይታ ከቡድኑ ዩኒቨርሲቲዎች በተደጋጋሚ አመርቂ ውጤት አስመዝግቧል፡፡

በስርዓተ-ጾታ ጉዳዮች የተሸለ የዕቅድ አፈጻጸም እንዳለው የስርዓተ-ጾታ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ጽጌ ሃይሌ እንደገለጹት የተለያዩ የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው ሴት ተማሪዎችን ለመርዳት የተዘጋጁ ፑል ቤት፣ ፎቶ ኮፒ ቤት፣ የሴቶች የጸጉር ውበት ሳሎን፣ እንዲሁም ለመወያያ እና መማማሪያ የስንቄ አደራሽ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
እንደ ዳይሬክተሯ ገለጻ ከአገልግሎቱ ገቢ የሚገኘው ትርፍ ገንዘብ ለችግረኛ ሴት ተማሪዎች እርዳታ ይውላል፣ ለተማሪዎቹ ነጻ የወረቀት ፎቶ ኮፒ አገልግሎትም ይሰጣቸዋል፣ፑል እና ጸጉር ቤቱም በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በቅናሽ ዋጋ ከመገኘትም በላይ ይበልጥ ሴት ተማሪዎችን ለጾታ ትንኮሳ እንዳይጋለጡ ተከላክሏል ተብሏል፡፡
በስንቄ አደራሽ ሴት ተማሪዎች ይወያያሉ፣ ይመካከራሉ፣ ያነባሉ፣ እረፍት ያደርጋሉ፡፡ ተማሪዎቹ በፈለጉበት ሰዓት ስለ ስርዓተ-ጾታ ጉዳዮችና ስለ ጾታ ትንኮሳ፣ ስለ ትምህርታቸው ሁኔታ ጭምር በግልጽ የሚወያዩበት ክፍል ነው፡፡ ክፍሉ 24 ሰዓት ሙሉ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ እየተመካከሩ፣ የተሞክሮ ልምድ እየተለዋወጡ ከጾታዊ ወይም ውጫዊ ተጋላጭነት የሚገነባቡበት ቦታ ነው፡፡ ሰፊ ውይይት የሚደረግበት ሳምንታዊ ልዩ ፕሮግራምም አላቸው፡፡
በአደራሹ ውስጥ ሆነው ሲያነቡ ካገኘናቸው ሴት ተማሪዎች ውስጥ ተማሪ ጻድቁ አበበ አንዷ ስትሆን የመጣችው ከትግራይ ገጠራማ ክፍል አነስተኛ ገቢ ካላቸው ቤተስብ እና የስድስት ሰዓት መንገድ በመመላለስ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቷን እንደተማረች ገልጻልናለች፡፡ በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ትምህርቷን በተደጋጋሚ ልታቋርጥ እንደ ነበረና አርሲ ዩኒቨርሲቲ ከገባች ወዲህ እንኳ ከዩኒቨርሲቲው ትምህርቷን አቋርጣ ልትሄድ ስትል በስርዓተ-ጾታ ጉዳዮች በኩል እርዳታ አግኝታ ከትምህርት ክፍል ባለደረቦቿ ከፍተኛ ነጥብ (3.6 C.G.P.) እንዳስመዘገበች ትናገራለች፡፡ ተማሪ ጻድቁ ዘንድሮ /Horticulture/ በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርቷን ጨርሳ የሚትመረቅ ሲሆን / ጽጌን እና ዳይሬክቶሬቱ ስለ አደረጉላት እርዳታ አመስግናለች፡፡
ከተማሪ ጻድቁ ጋር የነበሩት ተማሪ አለምፀሃይ አየለና ተማሪ ጌጤ በበኩላቸው የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተለያዩ ችግሮችን በመቋቋም እዚህ የደረሱ እና በአርሲ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የስርዓተ-ጾታ ዳይሬክቶሬት እያደረገላቸው ያለውን የኢኮኖሚ እና የሞራል ድጋፍ በአድናቆት አብራርተዋል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡