የስርዓተ-ጾታ ጉዳዮች ምርጥ ተሞክሮ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ:

የስርዓተ-ጾታ ጉዳዮች ምርጥ ተሞክሮ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ:

በስርዓተ-ጾታ ጉዳዮች ከመጀመሪያ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የተሸለ ውጤት አስመዘገበ፡፡

 የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ለሴት ተማሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስልጠና፣ ለዩኒቨርሲቲው ሠራተኞችና መምህራን ደግሞ የህጻናት ማቆያ አገልግሎት በመስጠት፣ ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የተሸለ ውጤት አስመዝግቧል፡፡ ለሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም የጥሩ ተሞክሮ ልምዱን እያካፈለ መሆኑን የዩኒቨርሲው ስርዓተ-ጾታ ጉዳዮች ዳይሬክተር / አልማዝ ጊዜው ገለጹ፡፡

 / አልማዝ አክለውም ሴት ተማሪዎች ላይ የሚታዩና ከየዕለት ትምህርታቸው የሚያደናቅፉዋቸው አካላዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ስነልቦናዊ ጉዳዮችን ከመቅረፍ አኳያ 2009. 24 ሴት ተማሪዎች የተጀመረው የአካላዊ ብቃት እንቅስቃሴ ስልጠና አሁን ላይ 190 ተማሪዎችን ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ በተጨማሪ በተለያዩ ብሔራዊና አለም አቀፋዊ የቴኳንዶ ደረጃዎች አብቅቷል፣ ተማሪዎቹ ከጾታዊ ጥቃትና ትንኮሳ ራሳቸውን እንዲከላከሉ፣ ከድብርት፣ ከተግባቦት ውስንነት፣ ከትኩረት ማጣትና ስሜት አለመግለጽ ችግሮች እንዲላቀቁ አድርጓል ብለዋል፡፡

 ሴት መምህራን፣አመራርና ሠራኞች ልጆቻቸውን በህጻናት ማቆያ በመተው ሙሉ ጊዜያቸውን በአትኩሮት ዩኒቨርሲቲውን እንዲያገለግሉ፣ በምርምርና ጥናት እንዲሳተፉ፣ ልጆቻቸው ያለስጋት ደስተኛ አእምሮ ይዘው እንዲያድጉ እንደረዳቸው የህጻናት ማቆያ ማዕከል ኃላፊ / ኤደን አምሳሉ ገልጸዋል፡፡ እንደ / ኤደን ገለጻ የተመቻቸውን ዕድል በመጠቀም ሴት ሠራተኞች ለልጆቻቸው ሳይጨነቁ ዩኒቨርሲቲውን በትጋትና በባለቤትነት ስሜት እያገለገሉ የሚገኙ ሲሆን በዚህም ማቆያው ከራሳቸው አልፎ ዩኒቨርሲቲውንም እንደጠቀመ ተናግረዋል፡፡

 የስፖርት ትምህርት መምህርና አሠልጣኝ ወንድማገኝ ሸዋንግዛው በበኩላቸው የአካል ብቃት እንቅስቃሴው ለሴት ተማሪዎቹ እራስን ከመከላከል አልፎ የጤና፣ አእምሮና ስነ ልቦናዊ ችግሮችን በመቅረፍ ለትምህርታቸው ትኩረት እንዲሰጡ እንደሚረዳቸው ገልጸዋል፡፡

 ተማሪ ጽዮን እሸቱና ተማሪ እታፈራሁ ስንታየሁ የደይሬክተሯንና የመምህሩን ሀሳብ በመጋራት ስልጠናው የራስ መተማመን እና ከየትኛውም ጾታዊ ትንኮሳ ራስን ለመከላከል ዝግጁ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል፡፡

 አቶ እስክንዲር ላቀው በትምህርት ሚኒስቴር የስርዓተ-ጾታ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ ለሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ልምዱን በማካፈል ዩኒቨርሲቲዎቹ ምርጥ ተሞክሮውን እያስፋፉ እንደሆነ በአርዓያነትም የአርሲ ዩኒቨርሲቲንና የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተሞክሮን በመጥቀስ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ-ጾታ ጉዳዮችን አመስግነዋል፡፡ ለውጤቱም የዶክተር አልማዝ እና ባልደረቦቿን ጥንካሬና ተነሳሽነት አድንቀዋል፡፡

 ህዳር 2009. ስራ የጀመረ ፕሮጄክቱ በዚህን ሰዓት ከፔዳ ካምፓስ በተጨማሪ በፖሊ ቴክኒክ 2 ቅርንጫፍ ከፍቷል፣ 17 ለሚሆኑ ለሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ የልሆኑ ድርጅቶችም ልምዱን አካፍሏል፡፡ በመምህራን የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢም ለሴት መምህራን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስልጠና ለመስጠት እና በተቀሩት 5 ካምፓሶች የህጻናት ማቆያ ለማስፋፋት ዕቅድ እንደተያዘ ተገልጿል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡