የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፍቃድ ምዘና

የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፍቃድ ምዘና

 በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራን የትምህርት ቤት አመራርና የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር / ካሳነሽ አለሙ እንደገለጹት ከግንቦት 11 ጀምሮ የሚካሄደው ምዘና የመምህራንን ብቃት ደረጃ በማሻሻል ጥራቱ የተጠበቀ የትምህርት ሥርዓት በመፍጠር የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል እየተካሄደ ያለው የማሻሻያ ተግባር አካል ነው፡፡

 በመላ አገሪቱ በሚካሄደው የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ምዘና 90 የሚሆኑ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የጹሑፍ ምዘና እንዲወስዱ ተገቢው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡

 እስካሁን በተካሄደው ምዘናም 251 መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የተመዘኑ መሆናቸውን ጠቁመው ከተመዛኞቹ መካከል ብዙዎቹ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ተመርቀው አዲስ የተመደቡ መምህራን መሆናቸውን ጠቁመዋል ፡፡

 ከተመዘኑ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች መካከል 38 ሺህ የሚሆኑ ነባር መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ወደ ማህደረ-ተግባር የተሸጋገሩ መሆናቸውንም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

 የመምህራንና የትምህርት አመራር ብቃት ለማረጋገጥ የሚካሄደው የምዘና ሥራ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲው አካል መሆኑንና በተለይም‛‛ Certification of teachers‛‛በሚል በተዘጋጀ መመሪያ ወደ ሥራ እንዲገባ የተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

 ምዘናው ካለፈው የካቲት ወር ጀምሮ መሰጠት የነበረበት ቢሆንም የቅድም ዝግጅት ሥራዎች ባለመጠናቀቃቸው ወደ ግንቦት ወር ሊሸጋገር መቻሉን ጠቁመው ተመዛኞች በድጋሚ ይራዘማል በማለት እንዳይዘናጉም ዳይሬክተሯ በመግለጫቸው አስገንዝበዋል፡፡

 ከግንቦት 11 ጀምሮ በሚካሄደው ምዘና የሚሳተፉ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ሁለት በሁለት የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ በመያዝ በምዘና ማዕከልት መገኘት እንዳለባቸው / ካሳነሽ ጨምረው መግለጻቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዘገባ ያስረዳል፡፡


News

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡