በኢንስፔክሽን ስራ ብዙ የትምህርት ጥራት ውጤቶች መታየት እንደጀመሩ ተገለጸ

በኢንስፔክሽን ስራ ብዙ የትምህርት ጥራት ውጤቶች መታየት እንደጀመሩ ተገለጸ

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን በዳይሬክቶሬት ደረጃ ከተቋቋመበት ከ2004ዓ.ም ጀምሮ የትምህርት ጥራት ላይ አትኩሮ በመስራቱ ሰፊ ለውጥ እያመጣ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ አስፋው መኮንን የ2010 ትምህርት ዘመን የ9 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የተሻለ ተሞክሮ ካለው የአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት ጥራትና አግባብነት ሬጉላቶሪ ኤጀንሲ ከክልሎችና የድሬ ዳዋ ከተማ ትምህርት ኢንስፔክሽን ጋር ከ15-19/2010ዓ.ም በተካሄደው የልምድ ልውውጥ መድረክ ላይ እንደተናገሩት ባለፉት 5 ዓመታት ዳረክቶሬቱ በሰራቸውና በወሰዳቸው የተለያዩ እርምጃዎች ትምህርት ጥራት ከማስጠበቅ አንጻር እምርታ ውጤቶች እየታዩ መምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡

በትምህርት ኢንስፔክሽን በተካሄደው የትምህርት ቤቶች ደረጃ ፍረጃ ባሉበት ደረጃ የሚቆዩትን እና ከደረጃቸው የሚያፈገፍጉ ትምህርት ቤቶች ላይ በመስራት፣ በህብረተሰቡ ዘንድ ግንዛቤ መፍጠር እና የባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት መሙላት ንቅናቄዎች ላይ በመስራት ለበለጠ ውጤታማነት ወደ ስራ የተገባ መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡በዚህም የግምገማ ግብረመልስ ተቀብለው ጥሩ ውጤት ዳይሬክቶሬቱ ከክልሎች ጋር በቅርበት መስራት የግንዛቤ ክፍተቶችን እንደሞላላቸው፣ የሁሉም ትምህርት ቤቶች ኮድ መዘጋጀት እንደ ሀገሪቱ የትኛው ትምህርት ቤት በኢንስፔክሽን ክፍተት እንደሚያሳይ ይገልጻል፣ አሁንም ለበለጠ ውጤታማነት የአዲስ አበባ የትምህርት ጥራት እና አግባብነት ሬጉሌቶሪ ኤጀንሲ ተሞክሮ ከትምህርት ሚኒስቴር ጀምሮ በሁሉም ክልሎች ቢስፋፋ፣ ለአመራሮችም ተመሳሳይ የግንዛቤ መድረክ ቢዘጋጅ፣ የኢንስፔክሽን ግብረመልስ ተቀብለው የማይተገብሩት ትምህርት ቤቶችና ባለድርሻዎች ወደ ስራ የሚስያገባ የተጠያቂነት አሠራር ቢጠብቅ በማለት ተሳታፊዎቹ መድረኩን በአድናቆት ገልጸዋል፡፡

35 ሺ አከባቢ ትምህርት ቤቶችን ይዘን የወጣለት ስራ ሠርተናል ማለት አይቻልም፣ ሆኖም ግን ወደ ፊት የሚያራምዱን ሰፊ ሁኔታዎች በብዙ ጥረት እንደተዘጋጁ በመግለጽ ባሉበት ደረጃ የሚቆዩ ብቻ ሳይሆን የሚያፈገፍጉ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን፣ ለአሰራር ግልጽ ያልሆኑ መረጃዎች ከክልሎች አልፎ አልፎ እንደሚታዩ በዳይሬክቶሬቱ ባለሙያዎች በአቶ አላምረው እና በወ/ሮ ገነት የተጠቆመ ሲሆን እነዚህን በምክንያታዊ መረጃ ማቅረብ እንደሚገባ ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡

ከክልሎቹ በቀረበው ሪፖርት መሠረት በተለያዩ ደረጃዎች ያሉ ትምህርት ቤቶች ከነተማሪዎቻቸው ዳታ በቀረበው የኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ሪፖርት ምን ያህል ተማሪዎች እንዳላቸው ጭምር መግለጹ ለአመራሮች በቀላሉ ግንዛቤ ማስያዝ እንደሚቻል አድንቀውታል፡፡ የትምህርት ጥራት እና አግባብነት በኢንስፔክሽን እንዴት ውጤታማ መሆን ይችላል በሚለው ዙሪያ በዳየይሬክቶሬቱ ባለሙያ በአቶ ሲሳይ የቀረበውን የጥናት ዕቅድ በመተቸት መድረኩ ተጠናቋል፡፡            

News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡