ሀገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ

ሀገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ

ይህ የተገለጸው በሀገራችን ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ በተከበረው የትምህርት ቤት ምገባ ቀን በዓል ላይ ነው፡፡

የኢ.... ትምህርት ሚኒስቴር ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ጋር በመተባበር በአፍሪካ ለሶስተኛ ጊዜ በሀገራችን ደረጃ ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን በዓልን ‘’ውጤታማ ሀገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራምን ተግባራዊ በማድረግ የኢትዮጵያ ህጻናትን እምቅ አቅም እናሳድግ!’’ በሚል መሪ ቃል የካቲት 22/2010 . በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሲዳማ ዞን ቦረቻ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት አከብሯል፡፡

የትምህርት ጥራትን በተጨባጭ ዕውን ለማድረግ ትምህርት ቤቶች መሰረት እንደመሆናቸው መጠን ለተማሪዎች ምቹ የትምህርት ሁኔታና አካባቢ እንዲኖር፥ ለትምህርት ያላቸውን ፍላጐትና ተነሳሽነት እንዲጨምርና የትምህርት አቀባበላቸውም እንዲሻሻል የትምህርት ቤት ምገባ አስፈላጊ ነው።

በኢ... ትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን ዓሉን አስመልክቶ ንግግር ባደረጉበት ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀመጠውን የትምህርት ልማት ግቦች ለማሳካት በአካልና በአዕምሮ የተስተካከለ ዜጋ ማፍራት ሲቻል ነው ብለዋል፡፡ ሚኒስትሩ አክለው በአንደኛ ደረጃ የትምህርት ተሳትፎና ጥራት በሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ መጠነ መጠናቀቅ መጠነ መዝለቅ ፣መጠነ ማቋረጥና መጠነ መድገም ላይ የሚታዩትን ክፍተቶችን በማጥበብ የትምህርት ውጤታማነት ማሳደግ ላይ ትኩረት መሰጠት እንደሚገባ አስገነዝበዋል፡፡

እንደ ክቡር አቶ መሀመድ ገለጻ ፌዴራል መንግስት በተያዘው ዓመት የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ተግባራዊ ለማድርግ 289 ሚሊየን ብር በመመደብ ከአንድ ሚሊየን በላይ ተማሪዎች የምገባው ተጠቃሚ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስቴር /ቤቱ የምገባ ፕሮግራሙን በስፋት ለማስቀጠል ብሔራዊ የትምህርት ቤት ምገባ ስትራቴጂ በማዘጋጅት ላይ ነው ያሉት ክቡር አቶ መሀመድ በቅርቡ ተጠናቆ በቁጥራቸው ውስን ለሆኑ ተማሪዎች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ ያቀደ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ኃላፊ / እሸቱ ከበደ እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት የትምህርት ቤት ምገባ በትምህርት ዘርፉ በመማር ማስተማር ሂደት ከሚያበረክተው፥ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ከማድረጉ ባሻገር አነስተኛ አርሶ አደሮች ለገበያ የሚያቀርቡት የምግብ እህል ምርት ብሎም የግብርና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ መኖሩን ተናግረዋል፡፡

የምገባ ፕሮግራሙ በተመረጡ አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ሳይለዩ ትኩስና የተመጣጤኔ ምግብ እንዲመገቡ ከማድረግ በተጨማሪ ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተኩ እንዲሁም ዕድሜው ለትምህርት የደረሰ ህፃን ጥራት ያለው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል አቅም ለክልሉ እየፈጠረ መሆኑን / እሸቱ ተናግረዋል፡፡

በባዓሉም የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም በተመረጡ አካባቢዎች ተግባራዊ በማድረግ በአንዳንድ ክልሎች የተገኙ መልካም ተሞክሮዎች ቀርበዋል፡፡

በዕለቱ ከትምህርት ሚኒስቴር ከዘጠኝ ክልልና ሁለት ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች እንዲሁም ከሀገር በቀል የግል ድርጅቶችና ከዓለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች የተውጣጡ ባለሙያዎችና ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

ባለፈው ዓመት በሀገራችን ደረካ ለመጀመሪያ ጊዜ የሀገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ በአዲስ አበባ ከተማ ኮከበ ጽባህ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤትሀገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ፤ ለመጪው ትውልድ ስኬት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ዛሬ እንቨስት እናደርግ!” በሚል መሪ ቃል መከበሩ የሚታወስ ነው፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡