የኢትዮጵያና የሀንጋሪ መንግስት በትምህርቱ ዘርፍ የነበራቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ስምምነት ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ተስማሙ፡፡

የኢትዮጵያና የሀንጋሪ መንግስት በትምህርቱ ዘርፍ የነበራቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ስምምነት ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ተስማሙ፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌና የሀንጋሪ የውጭ ጉዳዮችና ንግድ ሚኒስቴር ክቡር Dr. Csaba Baloch የሀንጋሪ መንግስት በሁለተኛና 3 ዲግሪ የሚሰጠውን የትምህርት ለማሳደግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመዋል፡፡
በስምምነቱ መሰረት 2014 30 የነበረው ነፃ የትምህርት እድል በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ወደ 50 ለማሳደግ ከስምምነት ደርሰዋል፡፡
ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በስምምነቱ ወቅት እንዳሉት ይህ እድል ለኢትዮጵያ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ገልፀው የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ያጠናክረዋል፡፡
የሀንጋሪ አምባሳደር የሆኑት ክቡር አምባሳደር Dr. Csaba Baloch በበኩላቸው መንግስታቸው ይህን ተግባ ለኢትዮጵያ የተደረገ መልካም ውለታ አድርጎ አይቆጥረውም፡፡ ይልቁንም የሁለቱን ሀገራት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ግንኙነት ለማጠናከር የተደረገ ነው ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያና በሀንጋሪ መንግስት መካከል የትምህርት ዘርፍ ትብብር ግንኙነት የተጀመረው ... 1980 ሲሆን ብዛት ያላቸው ተማሪዎች ወደ ሀንጋሪ እየተላኩ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል፡፡
ቢሆንም 1980 ጀምሮ እስከ 1990ዎቹ መጨረሻ ድረስ በምስራቅ አውሮፓ በተፈጠረው የፖለቲካ ለውጥ ምክንያት የትብብር ግንኙነቱ ሊዳከም ችሏል፡፡
ሆኖም አልፎ አልፎ የሀንጋሪ መንግስት ለኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ስልጠናዎችን በመስጠት ድጋፉን ሲያሳይ ቆይቷል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወድህ ደግሞ የሀገራቱን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ዳግም .. 2014 ለሶስት ዓመታት የሚቆይ የትምህርት ትብብር የተፈራረሙ ሲሆን ቁጥራቸው 40 በላይ የሚሆኑ የከፍተኛ ትምህርት መምህራን ለትምህርት ወደ ሀንጋሪ ተልከው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡
የሁለትዮሽ ግንኙነቱ በሳይነሳዊ ምርምር፣በልምድ ለውውጥና በሌሎችም ጉዳዮች የበለጠ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡