ሁለንተናዊ ስኬት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

ሁለንተናዊ ስኬት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

ዩኒቨርሲቲዎች ከመማር ማስተማር ስራ ጎን ለጎን በጥናትና ምርምር እንዲሁም ለአከባቢው ማህበረሰብ የቴክኖሎጂ ሽግግር በማስፋፋት ጉሊህ ድርሻ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡
በትምህርት ስራ አፈጸጸም የላቃ ውጤት በማስመዝገብ በዩኒቨርሲቲዎች መካከል በሚደረገው ውድድር ባለፉት አራት ዓመታት ከመጀመሪያ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች 1 እስከ 3 ደረጃ ውጪ ሆኖ የማያውቀው የሀዋሳ ዩኑቨርሲቲ ከመሠረቱ የተረጋጋና ቀጣይነት ያለው አሰራርና አፈጻጸም መኖሩን ያሳያል ያሉት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕረዝደንት ዶክተር ኢንጂነር ፍስሃ ጌታቸው ናቸው፡፡
2009. 2 ደረጃ ቢያገኝም በቅርብ ቀን ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ልቆ እንደሚሄድ በዩኒቨርሲቲው በሂደት ላይ ያሉ መጠነ ሰፊ የትምህርት ልማትና የልህቀት ማዕከላት እንዲሁም የማስፋፈያ ስራዎች ያረጋግጣሉ፡፡ ከላይ በተጠቀሰው ዓመት የምርምር ዩኒቨርሲቲ እንዲሆን የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ 81 የቅድመ ምረቃና 125 የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ተቀርጸው በፕሮግራሞቹ ዙሪያ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት ጋር በጥምረት እየተሰራ መሆኑን ዶክተሩ አብራርተዋል፡፡
በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በመማር ማስተማር ሂደ በትምህርት ጥራት ላይ ከማተኮር በተጨማሪ የማህበረሰብ ችግሮችን በመለየት በችግሮቹ ዙሪያ ጥናት ይደረጋል፣ በጥናቱ ውጤት ዙሪያ ሰፊ ውይይትና ግንዛቤ በመፍጠር ችግሩ ከመሠረቱ እንዲቀረፍ የተግባር ስራ ይሰራል፡፡ ከተለምዶው ሼልፍ ማስዋቢያ አልፈው የጥናትና ምርምር ውጤቶቻችን በተገኘው ውጤት ዙሪያ ክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ ይደረግባቸዋል በማለት የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝደንት ዶክተር ተስፋዬ አበባ ይገልጻሉ፡፡
የማህበረሰብ አገልግሎት፣ የዩኒቨርሲቲ እንዱስትሪ ትስስርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ትኩረት ተሰጥቶት በምክትል ፕሬዝደንት ደረጃ መመራቱ ዩኒቨርሲቲው ለማህበረሰቡ ተደራሽ ከመሆኑም በላይ ስራውን በጥራት በመስራት ደረጃ እንዲያገኝ ረድተውታል ይላሉ የዩኒቨርሲቲው የምርምር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አለማየሁ ረጋሳ፡፡
ዩኒቨርሲቲው በአየር ንብረት ለውጥ፣ በከርበንና ታዳሽ የሃይል ምንጭ ማፈላለግ ዙሪያ በወንዶ ገነት ደን ልማት ኮሌጅ፣ የካንሰር ህክምና ማእከል ግንባታና በግምት 20 ሚሊዮን የኦሮሚያ፣ የሶማሌ፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ኢትዮጵያውያን ተደራሽ የሆነው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እንዲሁም ESTEM ማዕከል 1 እና 2 ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን “INSIDE EVERY CHILD IS A SCIENTIST” በሚል መፈክር በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በኢንጂነሪንግና በህሳብ ትምህርቶች ተማሪዎችን ከመሰረቱ ኮትኩቶ ለማውጣት እያደረገ ያለው ጥረት ዩኒቨርሲቲውን ልዩ ያደርገዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ካምፓስ ጨምሮ በአምስት ካምፓሶች እና ሰባት ኮሌጆች በሁሉም መስክ 48,000 ተማሪዎችን እስያተማረ ይገኛል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡