ከተባበሩ እጆች በስተጀርባ ሁል ጊዜ ስኬት አለ

ከተባበሩ እጆች በስተጀርባ ሁል ጊዜ ስኬት አለ

የአርቦዬ 1 ደረጃ ትምህርት ቤት በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአርሲ ዞን ጀጁ ወረዳ አርቦዬ ከተማ ውስጥ ይገኛል፡፡ ትምህርት ቤቱ 2009. በትምህርት ስራ አፈጻጸም እንደ ሀገር ተሸላሚ ሆኗል፡፡
አካባቢው የወይናደጋ አየር ጠባይ ያለውና ለኑሮ ተስማሚ የሆነው ጀጁ ወረዳ ከዞኑ ርዕሠ መስተዳድር ከአሰላ ከተማ በስተ ሰሜን ምስራቅ 120 / ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በከተማው የተለያዩ ብሔርና ብሔረሰብ በይበልጥ አማራና ኦሮሞ ለዘመናት ተቻችለውና ተከባብረው እየኖሩባት ይገኛሉ፡፡
የአርቦዬ 1 ደረጃ ትምህርት ቤት 2008. በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ውስጥ ከሚገኙት 1 ደረጃ ትምህርት ቤቶች በትምህርት ስራ አፈጻጸም ተወዳድሮ 1 ደረጃ በመውጣት እንደ ክልል ብሎም እንደ ሀገሪቱ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ትምህርት ቤቱ ደረጃውን በማስጠበቅ 2009 የትምህርት ዘመን ዳግም 1 ወጥቷል፡፡
የትምህርት ቤቱ ርዕሠ መምህር አቶ ሙሳ ፌኮ ትምህርት ቤቱ 1 ደረጃ የሚወጣበትን ሚስጥር ሲገልጹ የሁሉም የትምህርት ባለ ድርሻ አካላት ያልተገደበ ጥረት ታክሎበት ትምህርትቤታችን ለዚህ ማዕረግ በቅቷል፣ አሁንም እድሉ በእጃችን ነው ይላሉ፡፡ የትኛውም የትምህርት ቤቱ ስራና እንቅስቃሴ በዕቅድና በውይይት ብቻ በመተባበር ነው የሚፈጸመው ያሉት ደግሞ የቀድሞው የትምህርት ቤቱ ርዕሠ መምህር የአሁኑ የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዑመር አሊይ ናቸው፡፡ አቶ ዑመር አክለውም ከላይ በውይይት የዳበረው የስራ ዕቅድ በበሳል አካሄድ እስከ ታችኛው ፈጻሚ አካል መውረዱ ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት የያገባኛል መንፈስን እና ይቻላልን በውስጣቸው በመሰነቅ ለዚህ ደረጃ እንዲንበቃ ተረባርቧል ይላሉ፡፡
በትምህርት ቤቱ ጠንካራ የትምህርት ልማት አደረጃጀት መገንባቱ ለመማር ማስተማር ስራ ውጤታማነት አበርክቷል፣ የሁሉን ባለድርሻ አካላት፤ የተማሪዎች፣ የወ... የመምህራን፣ የድጋፍ ሰጭ ሠራተኞች ተነሳሽነትና በመናበብ እንደሚሰሩ እያንዳንዳቸው በግልጽ ከሚያደርጉት ገለጻና ካሳዩን የስራ አፈጻጸም ተረድተናል፡፡ አሁንም ዋንጫውን ላለመልቀቅ የበለጠ በርትተው እንደሚሠሩ ሲገልጹልን እምቅ ሃይል እንዳላቸው በመረዳት ለካስ ከተባበሩት እጆች በስተጀርባ እምርት ውጤት ይገኛል፣ ሶስተኛውን ዋንጫ በማስቀረት ታሪክ ስሩ በማለት እኛም አርቦዬዎች በርቱ ተበራቱ ብለናቸዋል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡