የትምህርትና ሥልጠና ጉባዔ ተሳታፊዎች ለውጤታማነት አሰራር ተፈጻሚነት እንደሚረባረቡ ገለጹ

የትምህርትና ሥልጠና ጉባዔ ተሳታፊዎች ለውጤታማነት አሰራር ተፈጻሚነት እንደሚረባረቡ ገለጹ

የውጤታማነት የትግበራ ሥርዓትን በመተግበር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ለተቀመጡ ግቦች ስኬታማነት እንደሚረባረቡ 27ኛው የትምህርትና ስልጠና ጉባዔ ተሳታፊዎች አስታወቁ፡፡

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የገቡትን ቃል በማደስ የመልካም አስተዳደርን ለማስፈን የድርሻቸውን እንደሚወጡም ገልጸዋል፡፡

በጉባዔው በአፈጻጸማቸው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ተቋማት ዕውቅና ተበርክቶላቸዋል፡፡
27ኛው የትምህርትና ስልጠና ጉባዔ ተሳታፊዎች በአሶሳ ከተማ ላለፉት ሁለት ቀናት ያካሄዱትን ጉባዔ ሲያጠናቅቁ ባወጡት ባለ 14 ነጥብ የአቋም መግለጫ እንዳስታወቁት የውጤታማነት የትግበራ ስርዓትን ስኬታማ በማድረግ የትምህርት ጥራትና ተገቢነትን ለማረጋገጥ ተዘጋጅተዋል፡፡

በውጤታማነት የትግበራ ሥርዓት በአጠቃላይ ትምህርት፣በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና እና በከፍተኛ ትምህርት ዘርፎች ለተቀመጡ ግቦች ውጤታማነት በትኩረት እንደሚረባረቡ የጉባዔው ተሳታፊዎች በአቋም መግለጫቸው አረጋግጠዋል፡፡

በጥልቅ ተሀድሶ መድረኮች በትምህርትና ስልጠና ዘርፉ የተነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችና አስተያየቶችን በአጭር፣በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ዕቅዶቻቸው በማካተት ልማታዊ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን መዘጋጀታቸውን ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል ፡፡

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግ እና የትምህርት ፍትሀዊነት በሴቶች ፣በአካል ጉዳተኞች፣በአርብቶ አደርና በታዳጊ ክልሎች በተሻለ ደረጃ እንዲረጋገጥ ጠንክረው እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
የስነ ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርትን በማጠናከር በኢትዮጵያዊነት እሴቶች ላይ የተመሠረተ መልካም ስብዕና ያለው ትውልድ እንዲገነባ እንዲሁም የትምህርትና የቴክኖሎጂ ልማት ሠራዊት ግንባታን ወደተመጣጠነ ደረጃ በማድረስ ተልዕኳቸውን በውጤታማነት ለመፈፀም እንደሚተጉ አመለክተዋል፡፡

በህዝብ ተሳትፎ ምቹ ፣የተረጋጋና ሠላማዊ የትምህርትና ስልጠና በትምህርት ተቋማት ለማስፈን፣ መልካም ስብዕና የተላበሱ ዜጎችን ለማፍራት፣ የውስጥ ብቃትን በማሳደግና ትስስርና አጋርነትን በማስፋትና ችግር ፈቺ የጥናት፣ምርምር፣ የማህበረሰብ አገልግሎትና የቴክኖሎጂ ሽግግርን በላቀ ደረጃ በማከናወን የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰሩ አስረድተዋል፡፡

በትምህርትና ስልጠና የባለ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን በመፈጸም፣ የመንግስትና የህዝብ ሀብትን በአግባቡ በመጠበቅና የትምህርት ተደራሽነትን በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና፣ በብቃት ማረጋገጫ ማዕከላት፣በ2 ደረጃ፣በቅድመ መደበኛ፣በተቀናጀ መደበኛ ያልሆነ ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት በማስፋፋት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነትን ለማስፋት እንደሚረባረቡ በአቋም መግለጫቸው አረጋግጠዋል፡፡

ከአንደኛ እስከ ሦስተኛው ትውልድ /ጀኔሬሽን / ያሉ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች፣የሁሉም ክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የትምህርት ቢሮና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ኃላፊዎች በውጤታማነት አሠራር / Deliverology የትምህርት ጥራትና ተገቢነትን ለማረጋገጥ የተቀመጡ ግቦችን ተፈጻሚ ለማድረግ በዚሁ ጉባኤ ላይ ከክቡር ሚኒስትሩ ጋር ተፈራርመዋል፡፡

በጉባዔው 2009 የትምህርት ዘመን የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና. ተቋማት 1ኛደረጃ /ቤቶች፣ 2 ደረጃ /ቤቶች እንዲሁም የወረዳ ትምህርት /ቤቶች ፣የህዝብ ክንፍ አካላትና አጋር ድርጅቶች ለዋንጫና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በጉባዔው ማጠቃለያም 27ኛው የትምህርትና ስልጠና ጉባዔ አስተናጋጅ የሆነው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ 28ኛው የትምህርትና ስልጠና ጉባዔ አስተናጋጅ ለሆነው የኢትጵያ ሱማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ የአስተናጋጅነቱን አርማ ማስረከቡን የትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዘግቧል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡