News News

የ2010 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አዲስ ገቢ ተማሪዎች ምደባ ድልድል ይፋ ሆነ፡፡

2009 . የመሰናዶ ትምህርታቸውን በመከታተል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች ምደባ ድልድል ይፋ ሆነ፡፡ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ ዛሬ ከቀኑ 800 ሠዓት ላይ በኤጀንሲው ድረ ገፅ እንደሚለቀቅ ገልጿል፡፡

ምደባው የተማሪዎችን የትምህርት መስክ ምርጫ፣ የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች የክልል ስብጥር ባመላከተ መልኩ የተከናወነ ከመሆኑም በተጨማሪ ተማሪዎች ባስመዘገቡት ውጤት መሰረት እንደተደለደለ አቶ አርአያ ገልፀዋል፡፡ አቶ አርአያ አያይዘውም የጤና ችግር ኖሮባቸው የጤና ማስረጃ ያቀረቡ 137 የእንቅስቃሴ ችግር ያለባቸው 34 የሚያጠቡ እናቶች 25 መስማት የተሳናቸው 63 ተመሳሳይ ፆታ ያላቸው መንትዮች 37 እንዲሁም የአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር 40 መሰናዶ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ ድልድል መደረጉን ገልፀዋል፡፡

በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ከሚገቡት መካከል 94,195 ወንዶች፣ 42,941 ሴቶች በድምሩ 137,136 18 የትምህርት መስኮች መመደባቸውን አቶ አርአያ ገልፀዋል፡፡ 56.77/43.23 የወንድ ሴት ጥምርታ፣ 68.69 / 31.31 የተፈጥሮ ሳይንስ እና የህብረተሰብ ሳይንስ ጥምርታ እንዲሁም ኢንጂነሪንግ ከሌሎች ትምህርቶች ጋር ሲመዘን 30.48 ጥምርታ እንዳለው ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም አቶ አርአያ አያይዘውም የተማሪዎች የምደባ ውጤት በድህረ ገፅ www.app.neaea.gov.et እንዲሁም የየዩኒቨርሲቲዎች የምዝገባ ፕሮግራም በትምህርት ሚኒስቴር ቴሌቪዥን Frequency 11512 – Symbol rate 27500 – Polarization Vertical የሚገነውን እንዲከታተሉ አስገንዝበው ተማሪዎች ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች በወቅቱ እንዲገኙ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የኤጀንሲው ዳይሬክተር አቶ አርአያ /እግዚአብሄር የተማሪዎች ውጤት አወሳሰን፣ ሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድና አምስተኛውን የትምህርት ዘርፍ ልማት ፕሮግራም፣ የመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመቀበል አቅም፣ በትምህርትና ስልጠና መስክ የግል ሴክተሩ የሚጫወተውን ሚናና የዜጎች የመማር ዕድል መስፋት፣ የሴቶች ተማሪዎችን ቁጥር በማበራከት የትምህርት ፍትሃዊነትን ማረጋገጥ፣ የታዳጊ ክልልና የአርብቶ አደር ተወላጅ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተሳትፎ ማጠናከር እንዲሁም የአገራችንን ፈጣን ዕድገት ቀጣይ ለማድረግና ተፈላጊውን የሰው ኃይል ግንባታ ለማስቀጠል መሰረት ያደረገ እንደነበር አብራርተዋል፡፡No comments yet. Be the first.
News

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚካሄዱ የትምህርትና ሥልጠና ሥራዎች ውጤታማነት ተማሪዎች፣ መምህራን ፣ወላጆችና ህብረተሰቡ ኃላፊነታቸውን በላቀ ደረጃ ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚካሄዱ የትምህርትና ሥልጠና ሥራዎች ውጤታማነት ተማሪዎች፣ መምህራን ፣ወላጆችና ህብረተሰቡ ኃላፊነታቸውን በላቀ ደረጃ ሊወጡ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ አስታወቁ፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ህብረ-ብሔራዊነትና ኢትዮጵያዊነት የሚገነባባቸው ተቋማት እንጂ ተግባራቸው በጥቂት ችግር ፈጣሪዎች የሚስተጓጎል አለመሆኑንም ገለጹ 141ሺህ አዲስ ተማሪዎችን ጨምሮ ከ700 ሺህ በላይ ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመማር ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ከ2011 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የቅድመ ምረቃ ትምህርት መስኮች የብቃት መለኪያ አጠቃላይ ምዘና (የመውጫ ፈተና) ልተገበር ነው

ከ2011 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የቅድመ ምርቃ ትምህርት መስኮች ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት የብቃት መለኪያ አጠቃላይ ምዘና (የመውጫ ፈተና) ወስደው አጥጋቢና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚጠበቅባቸው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን በተለይም የምሩቃንን ብቃትና ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ አጠቃላይ ምዘና ወይም የመውጫ ፈተና መስጠት የምሩቃንን ዕውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ለመመዘን የላቀ ሚና ከመጫወቱም በተጨማሪ የተመራቂ ተማሪዎች በራስ መተማመን ያጎለብታል፡፡

የምርምርና የፈጠራ ስራ ውድድር ኤግዚቪሽን ተካሄደ

የሂሳብና ሣይንስ ትምህርቶች ማሻሻያ ማዕከል ከስቴምስ ሲነርጂ ፣ከዩኔስኮ እና ከኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ ጋር በመተባበር "በሣይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ የበለፀገ ህብረተሰብ ለዘላቂ ሠላምና ልማት "በሚል መሪ ቃል አገር አቀፍ የምርምርና ፈጠራ ስራ ውድድር ኤግዚቪሽን በኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ ተካሄደ፡፡ የምርምርና የፈጠራ ስራ አውደ- ርዕይ መከፈቱን አስመልክቶ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ የኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ የኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ የኢትዮጵያን ሣይንስ ለማበልፀግ የተቋቋመ መሆኑን አስታውሰው ይህ ማዕከል የህብረተሰቡን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ እንዲሁም ቴክኖሎጂን የመጠቀም አቅሙን ለማጎልበት ለማስተማርና የሣይንስ ፖርሽን ለመፍጠር የተሰራ ሲሆን ቋሚ የሳይንስ ማዕከል ለመፍጠር ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፡፡ በመሆኑም በቅርቡም የሳይንስ ማዕከሉ ወደ ስራ ይገባል በዚህም ወጣቱ ወደ ሣይንስ በሄደ ቁጥር የሀገራችን ተስፋ እየለመለመ ይሄዳል ብለዋል፡፡

የሥርዓተ-ፆታ ማካተትና ተቋማዊ ማድረግ መከታተያ፣ መመዘኛና በደረጃ የመለያ ማዕቀፍ ላይ ስልጠና ተሰጠ

የትምህርት ሚኒስቴር ሥርዓተ ፆታ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሁሉም የሥራ ክፍሎች እና ከተጠሪ ተቋማት ለተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች እየተሰጠ ባለው ስልጠና የሁለተኛ ቀን ውሎ በሥርዓተ-ፆታ ማካተትና ተቋማዊ ማድረግ መከታተያ፣ መመዘኛና በደረጃ የመለያ ማዕቀፍ ላይ ስልጠና ሰጠ ፡፡ ስልጠናውን የሰጡት በዳይሬክቶሬቱ የስርዓተ ፆታ ክትትልና ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ብርሃኑ አረጋ ሲሆኑ የዚህ ስልጠና ዋና አላማ በሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ያሉ የስራ ክፍሎች የሥርዓተ ፆታ እኩልነትና ሴቶችን ማብቃት ተቋማዊ ለማድረግ የሚያከናውኑትን ተግባራት በመመዘንና ተከታታይ ድጋፍ በመስጠት የሥርዓተ ፆታ እኩልነት በሁሉም ዘርፍ ለማረጋገጥ ብሎም የሀገራችንን የልማት ራዕይ ለማሳካት ነው ብለዋል፡፡

የመንግስታዊና ግብረሰናይ ድርጅቶች የጋራ ፎረም ውይይት ተካሄደ፡፡

ዛሬ ጥቅምት 20/2010 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር አዳራሽ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በትምህርት ስልጠና ዘርፍ የ2010 ዓ.ም ዋና ዋና ዕቅዶች ላይ ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል፡፡ በምክክር መድረኩ ተገኝተው የመድረኩን አላማ የገለጹት በትምህርት ሚኒስቴር የእቅድ ዝግጅትና ሃብት ማፈላለግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ግርማ የመድረኩ ዋና አላማ የትምህርት ሴክተሩ እቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት ማድረግ ነው ብለዋል፡፡