የትምህርት ሚኒስቴር ቴሌቭዥን ማስተዋወቅ

የትምህርት ሚኒስቴር ቴሌቭዥን ማስተዋወቅ

የትምህርት ሚኒስቴር እንኳን ለአዲሱ የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያለ የትምህርትና ስልጠናውን ውጤታማነት በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ በሀገራችን በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቨዥን የሙከራ ስርጭት መጀመሩን ሲያበስር ላቅ ያለ ደስታ ይሰማዋል፡፡
ስርጭቱን ከዚህ ጽሁፍ ግርጌ በተገለጸው ባህሪያት መከታተል ትችላላችሁ፡፡
ተማሪዎች፣መምህራን፣ወላጆች፣የትምህርት ባለሙያዎችና አመራሮች እንዲሁም መላው ማህበረሰብ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዩኒቨርሲቲዎች የምዝገባ ጥሪ ማስታወቂያዎችን ጨምሮ ልዩ ልዩ ትምህርትና ስልጠና ነክ መረጃዎችን በሙከራ ላይ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን (MOE) በቀጥታ መከታተል የምትችሉ መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በደስታ ይገልፃል፡፡
ለበለጠ መረጀ:-
-
ስልክ ቁጥር 0111-56-55-36 /0111-56-55-29/
- facebook –
www.facebook.com/fdremoe.(Ministry of Education Ethiopia)
-
ድረገጽ - www.moe.gov.et ይጠቀሙ፡፡
መልካም የትምህርት ዘመን
የኢ.... ትምህርት ሚኒስቴር

 

No automatic alt text available.

 


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡