የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በአዲስ ዓመት አቀባበል የንቅናቄ እቅድ ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በአዲስ ዓመት አቀባበል የንቅናቄ እቅድ ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡

የሚኒስቴር መስሪያቤቱ መላው ሰራተኛ ፣መካከለኛና ከፍተኛ አመራሩ በተገኙበት በአዲስ አመት አቀባበል የንቅናቄ እቅድ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
የንቅናቄ ዕቅዱን መነሻ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኮሙዩኒኬሽ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት / ሀረጓ ማሞ ያቀረቡ ሲሆን የዚህ እቅድ ዋነኛ ግብ የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር የተለያዩ ተግባራት በማከናወን አንድነትን በሚገነባ መንፈስ አዲሱን ዓመት ለመቀበል መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የዚህ የህዝብ ንቅናቄ አስፈላጊነት መጪው ዘመን በብሔር ብሔረሰቦች መካከል የነበረንን መከባበር ፣መቻቻል፣የአንድነት እሴቶችን በማጠናከር በትምህርትና ስልጠና ዘርፉ የበለጠ የመነቃቃት ስሜት እንዲፈጠር ለማድረግ ነው፡፡ 2010. የትምህርት ዘመን ምቹና ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲቀጥልና ያለምንም እንከን ዘመኑ በውጤት እንዲጠናቀቅ እንዲሁም ተማሪዎች ካለፈው ትምህርት ዘመን በላቀ ደረጃ ለውጤት የበለጠ እንዲተጉ ለማድረግ፣ተማሪዎች ከመጪው የትምህርት ዘመን ብሩህ ተስፋ ሰንቀው ያለ አንዳች መንጠባጠብ በነቂስ እንዲመዘገቡና እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናትም ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመጡ ለማድረግ በንቅናቄ ወደ ተግባር መግባት አስፈልጓል ብለዋል፡፡
አቅራቢዋ አክለውም የእቅዱ ዋና ዋና ተግባራት ያሉትን ዘርዘር አድርገው ያቀረቡ ሲሆን እነሱም የአረንጓዴ ልማትን ለማጠናከር የችግኝ ተከላ ማከናወንና ቀደም ብለው የተተከሉትንም ችግኞች መንከባከብ፣ለአቅመ ደካማ አረጋውያን፣ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናትና እነዲሁም ጎዳና ተዳዳሪዎችን መንከባከብና ድጋፍ ማድረግ ፣ለመጭው የትምህርት ዘመን በወጣው የትምህርት ጊዜ ሰሌዳ መሰረት የትምህርት ምዝገባ ማካሄድና ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ መስራት፣የሚኒስቴር መስሪያቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች አካባቢያቸውን ማጽዳትና መንከባከብ፣የተቋማት ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች የደም ልገሳ ማካሄድ፣ብሔራዊ ሙዚየምን ጨምሮ ሀገራዊና ታሪካዊ ቅርሶችን መጎብኘትና የመልካም ምኞት መግለጫ ፖስት ካርድ በማዘጋጀት ናቸው ብለዋል፡፡
ይህንን ስራ ለመስራት አብይ ኮሚቴና የተለያዩ ንዑሳን ኮሚቴዎች የተዋቀሩ ሲሆን የተዋቀረው ኮሚቴም ከተሰጠው ተልዕኮ አንፃር የራሱን እቅድ በማውጣት ወደ ተግባር እንዲገባ እንዲሁም የየኮሚቴ አፈፃፀሙ በየሁለት ቀኑ የሚገመገምበት አቅጣጫ መቀመጡን አመላክተው እያንዳዱ ተግባር መቼ መቼ ይፈፀማል የሚለውን በዕቅዱ የተቀመጠውን ድረጊት መርሃ ግብር ለውይይት አቅርበዋል፡፡
የቀረበውን ዕቅድ መነሻ በማድረግ ሰራተኞች የተለያዩ ጥያቄዎችንና አሰተያየቶችን አንስተዋል፡፡ ከተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች መካከል የትምህርት ጥራትን ስለ ማስጠበቅ፣ስለተማሪዎች ስነ ምግባር ኩረጃን በተመለከተ እዲሁም የበጎ አድራጎት ዘላቂነትን የተመለከቱና የመሳሰሉት ጉዳዮች ተነስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በእለቱ በንቅናቄ እቅዱ አስፈላጊነት ላይ እንዲሁም ከሰራተኛው ለተነሱት ጥያቄና አሰተያየት ላይ ሀሳብ የሰጡት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር የተከበሩ / ጥላዬ ጌቴ ኢትዮጵያ ሀገራችን ቀደምት ታሪክ ያላት፣የብሔርና ብሔረሰቦች እና የሀይማኖት መቻቻል ያለባት፣ለጥቁር አፍሪካውያን የነፃነት ፋናወጊ በቅኝ ግዛት ያልተገዛች፣በአሁኑ ወቅትም በአለም በከፍተኛ ፍጥነት እያደጉ ካሉ ጥቂት ሀገራት መካከል አንዷ ሀገር መሆኗን ገልጸው ለዚህ የንቅናቄ ስራ በብሔራዊ ደረጃ ኮሚቴ ተዋቅሮ የሚከናወን መሆኑ ጠቁመው አዲሱን ዓመት በተነቃቃና በአንድነት መንፈስ ለመቀበል ሁሉም ሰራተኛ በበጎ አድራጎት ተግባር ሊሳተፍ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ለተነሱ ሀሳቦች ምላሽ ሲሰጡ የትምህርት ጥራትን ማስጠበቀ መደበኛ ሥራችን መሆኑንና ካለፉት ጊዜያት የበለጠ አጠናክረን የምንሠራበት ዋነኛ አጀንዳችን ሲሆን ንቅናቄው ለዚህ ዓለማ ስኬት መሠረትና መነሻ በመሆን ህዝቡን ከጎናችን በማሰለፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጸው የመደበኛ ሥራውን አስመልክቶ ራሱን ችሎ ውይይት የሚደረግበት እንደሚሆን ግጸዋል' ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም ለዚህም ቅድመዝግጅ እየተደረገ እንደሚገኝና በትምህርትና ሥልጠና ዘመኑ መጀመሪያ ላይ ከፌዴራል እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የሚወርድ ውይይት የሚደረግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በመጨረሻም የተዋቀረው ኮሚቴ ኃላፊነቱን በሚገባ እንዲወጣና ሰራተኞች የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በንቃት እንዲሳተፍና ይህ የበጎ አድራጎትና ፍቃደኝነት ተግባራት ከመደበኛ ስራ ጎን ለጎን አመቱን ሙሉ በዘላቂነት ማስቀጠል እንደሚገባ በማሳሰብ ውይይት መድረኩን አጠቃለዋል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡