የትምህርት ሚኒስቴር ሥርዓተ ፆታ ዳይሬክቶሬት የኢትዮጵያ ሴቶች የልማትና የለውጥ ፓኬጅና ስትራቴጂ ላይ የምክክር መድረክ አካሄደ

የትምህርት ሚኒስቴር ሥርዓተ ፆታ ዳይሬክቶሬት የኢትዮጵያ ሴቶች የልማትና የለውጥ ፓኬጅና ስትራቴጂ ላይ የምክክር መድረክ አካሄደ

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስርዓተ ፆታ ዳይሬክቶሬት 06/12/09 . ቢሾፍቱ ከተማ ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የስርዓተ ፆታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት / ኤልሳቤጥ ገሰሰ ናቸው፡፡ የዚህ መድረክ ዋነኛ አላማ በኢ... ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር አማካኝነት በተዘጋጀው የኢትዮጵያ ሴቶች የልማትና የለውጥ ፓኬጅና ስትራቴጂ ላይ ውይይት ማድረግ ሲሆን በተለይም የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ረገድ እስካሁን የተሰራው ሥራ እንደተጠበቀ ሆኖ ተግዳሮቶችን በመለየት ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ዳይሬክተሯ አክለውም ይህንን ሰነድ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ሲያዘጋጅ ከየመስሪያ ቤቱ የተውጣጡ ባለሙያዎች የተሳተፉበት መሆኑን ገልፀው እንደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ያሉ መካከለኛ አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች በዚህ ፓኬጅና ስትራቴጅ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲይዙ ያስችላቸዋል በማለት የውይይት መድረኩን ከፍተዋል፡፡
በእለቱ በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የኢ... ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች ጉዳይ ግንዛቤ ባለሙያ የሆኑት አቶ ምንያምር ይታይህ ስትራቴጅውን መሰረት ያደረገ ሰነድ ለውይይት አቅርበዋል፡፡
ባለሙያው እንዳሉት የዚህ ስትራቴጂ ዋነኛ ዓላማ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ፣ፖለቲካዊና ማህበራዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ለሀገራችን ሁሉንተናዊ ልማትና እድገት የበኩላቸውን እንዲወጡ ማድረግ መሆኑን አመላክተው መንግስት ያከናወናቸውን ተግባራት ለማሳየት በሰነዱ በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች የተገኙ ውጤቶችንና ተግዳሮቶችን የሁኔታ ዳሰሳ ዘርዘር አድርገው አቅርበዋል፡፡ በፖለቲካው ረገድ ሴቶች ያላቸው ተሳትፎ 38.8% በህዝብ ተወካች ምክር ቤት፣ 20.6 በህግ ተርጓሚ፣ 13.3% በአስፈፃሚ አካላት ከፍተኛ አመራር፣ 22% በመካከለኛ አመራር እንዲሁም በክልሎች 40.3% በህግ አውጪ፣ 14.8% በአስፈፃሚ፣ 17.9% በህግ ተርጓሚ መድረሱን ጠቁመዋል፡፡ በኢኮኖሚውም ከድህነት ወለል በታች ያሉ ሴቶች ቁጥር በአንጻራዊነት የቀነሰ ሲሆን በተመሳሳይ የከተማ ስራ አጥ ምጣኔ 2002 . ከነበረበት 27.4% 2005 . ወደ 23% ዝቅ ማለቱ ተገልጿል፡፡ በተለይም በማህበራዊ ዘርፍ ከትምህርት አንፃር የተገኙ ውጤቶች ብለው ያነሷቸው ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ መሰናዶ ትምህርት ያለው ተሳትፎ ምጥጥኑ የተሻለ መሆኑ በመጀመሪያ ደረጃ የሴት መምህራን ቁጥር በመምህራን ትምህርት ኮሌጆችና በቴክኒክን ሙያ ተቋማት የሴቶች ተሳትፎና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከቅድመ እስከ ድህረ ምረቃ ተሳትፏቸው እያደገ መምጣቱን አንስተዋል፡፡ ባለሙያው አሁንም ያልተሻገርናቸው ችግሮች ያሏቸው፣ በሴቶች ትምህርት ዙሪያ ያለው አመለካከት ሙሉ ለሙሉ አለመቀየሩ፣ የሴቶች ትምህርት ማቋረጥና መድገም፣ የትምህርት ውጤታማነት የሚፈለገው ደረጃ ላይ አለመድረስ፣ ተፎካካሪነት፣ የጎልማሳ ትምህርት ተሳትፎ፣ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የሚሰጡ ስልጠናዎች የሴቶችን ፍላጎት ያማከሉ አለመሆን በቀጣይ ልዩ ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ናቸው ነው ብለዋል፡፡
የሰነዱ አቅራቢ የሴቶች የልማትና የለውጥ ስትራቴጂ ዋና ዋና ጉዳዮች እና ሁሉም አመራርና ባለሙያ ሊተገብራቸው የሚገቡ አራት ስትራቴጅክ ጉዳዮች አሉ ያሉ ሲሆን እነዚህም የአመለካከት ለውጥ ማምጣት፣ የሴቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፣ ልዩ ትኩርት የሚሹ ሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እና የአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደሮች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ላይ መስራት ይጠበቃል በማለት ከነማስፈፀሚያ ስልታቸው ሲያቀርቡ ተሳታፊዎችም የቀረበውን ሰነድ መነሻ በማድረግ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡
በመጨረሻም የትምህርት ሚኒስቴር ሥርዓተ ፆታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር / ኤልሳቤጥ ከፖሊሲውና ስትራቴጅው በመነሳት መካከለኛ አመራሩና ባለሙያው በጋራ የነበሩ መልካም አፈፃፀሞችንና ተግዳሮቶችን በሚገባ በመገምገም ትርጉም ባለው መልኩ 2010. እቅድ ውስጥ በማስገባት እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ በማውረድ በተጠያቂነት መንፈስ ኃላፊነታችንን እንወጣ የሚል መልክት አስተላልፈዋል፡፡
በውይይቱ የትምህርት ሚኒስቴር መካከለኛ አመራሮችና ከየዳይሬክቶሬቱ የተመረጡ ከፍተኛ ባለ ሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡