የትምህርትና ስልጠና አካላት የውጤታማነት አሰራር ስነ ዘዴን በመተግበር የተሰጠ ግንዛቤ

የትምህርትና ስልጠና አካላት የውጤታማነት አሰራር ስነ ዘዴን በመተግበር የተሰጠ ግንዛቤ

በየደረጃው የሚገኙ የትምህርትና ስልጠና አካላት የውጤታማነት አሰራር ስነ ዘዴን በመተግበር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና የሥራ ዕድል ተጠቃሚነትን ለማስፋት ለተቀመጠው ግብ ተፈጻሚነት መረባረብ እንደሚጠበቅባቸው የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው /ማርያም አስገነዘቡ፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው / ማርያም በአዳማ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የውጤታማነት አሰራር/DELIVEROLOGY/ አውደጥናት እንዳስገነዘቡት ሁሉም የትምህርት ሥራ ባለድርሻዎች በውጤታማነት አሰራር/ DELIVEROLOGY/ ስነ ዘዴ በመጠቀም በትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የተቀመጠው ግብ እንዲሳካ ተባብረውና ተቀናጅተው ሊሰሩ ይገባል፡፡
በአጠቃላይ ትምህርት፣በቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍና በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ የሥራ ዕድልን ለማስፋት የሚቻለው በዘርፉ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን በመፍታትና የመፈጸምና የማስፈጸም አቅምን በማሳደግ መሆኑን ዶክተር ሽፈራው ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም በየደረጃው የሚገኙ የትምህርትና ስልጠና አካላት ዕቅዶቻቸውን በውጤታማነት በመፈጸም ተማሪዎች በህይወት ዘመን ክህሎት በየተሰማሩበት የትምህርት እርከን በቅተው በኢኮኖሚው የድርሻቸውን እንዲያበረክቱ የማስቻል የጋራ ኃላፊነት እንዳለባቸው ሚኒስትር አስታውቀዋል፡፡
ሁሉም የትምህርትና ስልጠና አካላት እንደተጨባጭ ሁኔታቸው የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ ኢኮኖሚው የሚፈልገውን የበቃ የሰው ኃይል ለማፍራት የውጤታማነትን አሰራር/ DELIVEROLOGY/ ዘዴን ተከትሎ መሥራትና የሚፈለገውን ውጤት በአጭር ጊዜ ማስመዝገብ እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡
መንግስት በየዓመቱ እስከ 25 በመቶ በጀት ለትምህርት ሥራ ውጤታማነት በመመደብ ለዘርፉ እድገት ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን የጠቆሙት ሚኒስትሩ በዘርፉ እየተመዘገበ የሚገኘው ውጤት ወደላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር ማስቻል እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡
በትምህርትና ስልጠና ዘርፉ የውጤታማነት አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ የሚመዘገበው ውጤት የትምህርትና ስልጠና ዘርፉን ውጤታማነት ከማረጋገጥ ባሻገር በአገር ደረጃም ዘርፈ ብዙ የማስፈጸም አቅም ምላሽ መስጠት እንደሚያስችል ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው አስረድተዋል፡፡
በየደረጃው የሚገኙ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት የውጤታማነት አሰራር ስነ ዘዴን የዕቅዳቸው አካል በማድረግ በመደጋገፍና በመተሳሰብ መሥራትና የሚፈለገውን ውጤት ማምጣረ እንዳለባቸው ሚኒስትሩ በአጽንኦት አስገንዝበዋል፡፡
በውጤታማነት አሰራር ስነ ዘዴ ላይ አትኩሮ እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ አውደጥናት በየደረጃው የሚገኙ የትምህርትና ስልጠና ባለድርሻዎች ተሳታፊ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዘግቧል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡