በሙያ ፍቃድ የምዘና ውጤት ትንተናና በመምህራን ትምህርት ኮሌጆች እውቅና አሰጣጥ ስታንዳርዶች ዙሪያ ምክክር መድረክ ተካሄደ

በሙያ ፍቃድ የምዘና ውጤት ትንተናና በመምህራን ትምህርት ኮሌጆች እውቅና አሰጣጥ ስታንዳርዶች ዙሪያ ምክክር መድረክ ተካሄደ

ሀገራችን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥና እድሳት ስርዓት በመዘርጋት የመምራን፣ የርዕሰ መምህራንና የሱፐርቫይሮች ሙያዊ ብቃት ምዘና ሂደትን በወጥነት ለመተግበርና በሙያ ፍቃድ አሰጣጥ የአደረጃጀቶችን ሚናና የፈጻሚ ባለድርሻ አካለላትን ተግባርና ኃላፊነት ለይቶ ለማሳወቅና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚየስችል የአሰራር ስርዓት ዘርግታ እየሰራች ትገኛለች፡፡

 

በሙያ ፍቃድ አሰጣጥ ስርዓት ውስጥ ሶስት የሙያ ፍቃድ አይነቶች አሉ፡፡ እነዚህም፦ አንደኛው የመጀመሪያ ሙያ ፍቃድ ለጀማሪ መምህራንና በትምህርት ተቋማት አመራርነት ሰልጥነው ወደሙያው ለሚገቡ  እንዲሁም  ለደረጃው የብቃት መመዘኛ ላሟሉ የሚሰጥ ሁለተኛው ሙሉ የሙያ ፍቃድ፥ ለአምስት አመት የሚያገለግል ሆኖ የመጀመሪያ ሙያ ፍቃድ በማግኘት ሲሠሩ ቆይተው ላጠናቀቁ የሚሰጥ ሲሆን የሦሥተኛው  ደግሞ ቋሚ የሙያ ፍቃድ ነው፡፡ ይህ ፍቃድ ሙሉ የሙያ ፍቃድ ከያዙ በኋላ  ለደረጃው የሚመጥን አገልግሎት አጠናቀው የሙያ ፍቃድ ብቃት መመዘኛ ላሟሉ መምህራን፣ ለርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የሚሰጥና በየአምስት አመት የሚታደስ  ቋሚ የሙያ ፍቃድ ነው፡፡

 

በኢ... ትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር / ጥላዬ ጌቴ የመምህራን የትምህርት ቤት አመራሮች እና ሱፐርቫይዘሮች ሙያ ፍቃድ አሰጣጥና እድሳትን አስመልክቶ ንግግር ባደረጉበት ወቅት  ሀገራችንትምህርት ለሁሉምግቦችን በማሳካት እምርታዊ ውጤት ማስመዝገቧን በመጥቀስ በትምህርት ጥራትና ፍትሐዊነት ዙሪያ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት ለዘርፉ ስኬትና ውጤት የሚያሳልጡ  መመሪዎች፣ደንቦች፣እቅዶችና መርሃ ግብሮችን ነድፋ እየተንቀሳቀሰች መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

 

እንደ ክቡር ሚኒስትሩ  ገለጻ መንግስት የሀገሪቱን ትምህርት ዘርፍ ልማት እንቅስቃሴዎችን በመፈተሽ በግብዓት፣ በሂደትና በውጤት ዙሪያ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የትምህርት ምዘናን መሰረት በማድረግ  የተማሪዎችን ንባብ ክህሎት ለማዳበር መምህራን በዝቅተኛ ትምህርት ክፍል (1-4) በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲሰለጥኑና እንዲያስተምሩ የማድረግ ተግባር፣ የአጠቃላይ ትምህርት እንስፔክሽን መርሃ ግብር በመተግበር የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማውጣትና  ትምህርት ቤቶችንም የመደገፍ እንዲሁም መምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች በማሰልጠን ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

 

በሚኒስቴር /ቤቱ የመምህራንና ትምህርት አመራሮች ሙያ የፍቃድ አሰጣጥና እድሳት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር / ካሳነሽ አለሙ ምክክር መድረኩን  በንግግር በከፈቱበት ወቅት  የብቃት ምዘናዎችን በአግባቡ ለማስፈጸምና የተመዛኞች ክፍተት ላይ በማተኮር ቀጣይነት ባለው ሁኔታ የክፍተት መሙያ ሙያዊ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በየደረጃው ባሉ የትምህርት ተቋማት ለመስጠት  ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና የኮሌጆች  ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

እንደ ዳይሬክተሯ ንግግር በዘርፉ የተጀመሩ ስራዎችን  ውጤታማ ለማድረግ የመምህራን፣ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች አጠቃላይ የብቃት ደረጃዎች(Generic Standards) ለሁለተኛ ደረጃ መምህራን የምዘና ውጤት ትንተናና ለኮሌጆች እውቅና ለመስጠት የሚያስችል መነሻ ማስተግበሪያ ሰነድ ላይ  ለባለድስሻ አካላት ጋር በመወያየት ለወደፊት ቀሪ ስራዎች የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው ብለዋል፡፡

 

እስካሁን በተደረገው የሙያ ብቃት ምዘና 172, 455 ለሚሆኑ መምህራን፣ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ፈተና የወሰዱ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 38,034 ማለትም 22 ከመቶ ለቀጣይ የምዘና አይነት ማለትም ለማህደር-ተግባር ምዘና ዝግጁ እንደሆኑ  / ካሳነሽ ገልጸዋል፡፡

 

ተሳታፊዎች በበኩላቸው የመምህራን፣ የርዕሰ መምህራንና የሱፐርቫይሮች ሙያዊ ብቃት ምዘና ሂደትን በወጥነት መተግበር በትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ሂደት ወሳኝ ሚና መጫወቱን  በመጥቀስ  ተመዛኞች ስለሙያ ፍቃድ አሰጣጥ አሰራር እንዲገነዘቡ ለማድረግ  በቂ የግብዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መሰራት እንደሚገባም አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

 

በአዲስ አበባ ከተማ ከሚያዝያ 17-18 . በተዘጋጀው ምክክር መድረክ  ከሚኒስተር /ቤቱ፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ከትምህርት ኮሌጆችና ከክልል  እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮች  እንዲሁም ከሙያ ማህበራት የተውጣጡ ኃላፊችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡

 


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡