የተፋጠነ የትምህርት ቤት ዝግጁነት የትምህርት አቀራረብ ሥነ-ዘዴ እንደ አንድ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ማስፋፊያ አመራጭ ተወስዶ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንድተገበር የምመክር አውደ ጥናት ተካሄደ

የተፋጠነ የትምህርት ቤት ዝግጁነት የትምህርት አቀራረብ ሥነ-ዘዴ እንደ አንድ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ማስፋፊያ አመራጭ ተወስዶ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንድተገበር የምመክር አውደ ጥናት ተካሄደ

የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል 2007 . ክረምት ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተተገበረ ያለውን የተፋጠነ የትምህርት ቤት ዝግጁነት የቅድመ መደበኛ ትምህርት አቀራረብ ውጤታማነትን ለማስተዋወቅና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማስፋት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውጪ ከሁሉም ክልሎች፤ ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር፣ ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ እና ከህጻናት አድን ድርጅት እንዲሁም ከትምህርት ሚኒስቴር የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎችና የትምህርት ባለሙያዎች የተሳተፉበት አውደ ጥናት ሚያዚያ 2 እና 3/2009 .  በትምህርት ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አደራሽ ተካሄደ። ይህ ፕሮግራም ከአራቱ የቅድመ መደበኛ ትምህርት አሰጣጥ ሥነ-ዘዴ መካከል አንዱ ሲሆን በሦስቱም (መዋዕለ ህጻናት፤ ክፍልና ህጻን ለህጻን) የቅድመ መደበኛ ትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ተጠቅመው ለመደበኛ ትምህርት ቅድመ ዝግጅት ያላደረጉትን እድሜያቸው ስድስት ዓመትና ከዚያ  በላይ የሆኑ ህጻናትን በስምንት ሳምንታት  ውስጥ ለመደበኛ ትምህርት ዝግጁ ማድረግ ያሚያስችል ፕሮግራም ነው።

 

በኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት የቅድመ መደበኛ ትምህርት ባለሙያ የሆኑት አቶ ሰይፈ ወልዴየቅድመ መደበኛ ትምህርት አጠቃላይ ገጽታበሚል ርዕስ ባቀረቡት ጽሑፍ በአምስተኛው የትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ልማት ፕሮግራም የቅድመ መደበኛን ትምህርት አስመልክቶ ከተቀመጡት  ስትራቴጂክ ግቦች ውስጥ አንደኛው በዋነኛነት የኦ-ክፍል እና ሌሎች መደበኛ ያልሆኑ የቅድመ መደበኛ ትምህርት አሰጣጥ ዘዴዎችን ተግባራዊ በማድረግ 2012 ጥቅል ተሳትፎውን 80% ማድረስ የሚል ግብ አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ይሁን እንጂ 2008 . በወጣው የትምህርት ሚኒስቴር  አመታዊ ስታትስቲክስ መፅሃፍ መሠረት ሀገራዊ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ጥቅል ተሳትፎ 49.9 % እንደሆነ ገልጸዋል። በዚሁ መሠረት ከሀገር አቀፍ አማካይ አፈጻጸም አንጻር የቅድመ መደበኛ ትምህርት ጥቅል ተሳትፎ በሶማሌ ብሔራዊ ክልል፣በአፋር ብሔራዊ ክልል፣በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንዳሉ ጠቁመዋል።

 

በዩኒሴፍ ኢትዮጵያ  የቅድመ መደበኛ ትምህርት ባለሙያ የሆኑት / አማከለች ግደይ ጽሑፍ ያቀረቡ ሲሆን በጽሑፋቸው የሀገራችንን የቅድመ መደበኛ ትምህርት ሽፋን ለማሳደግ የተፋጠነ የትምህርት ቤት ዝግጁነት መርሀ ግብር እንደ አንድ አማራጭ ተወስዶ ተግባራዊ እንዲሆን ለማድረግ ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ፕሮግራሙን ለመነሻነት ያስተዋወቀ  መሆኑን እና በዚህ መልክ በተደረገው ጥረት በርካታ ሀገራት ካቀረቡት ቢጋር ውስጥ ኢትዮጵያ ከተመረጡት አምስት ሀገሮች አንዷ በመሆኗ ፕሮግራሙን በሙከራ ደረጃ ለመተግበር ድጋፍ መገኘቷን እና ይህንኑ መሠረት በማድረግ ከትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች እና ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ አመራሮች ጋር በተደረገው ውይይት መርሀ ግብሩ 2007 . ክረምት ወራት ጀምሮ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል በሙከራ እንዲተገበር ስምምነት ላይ በመደረሱ ተግባራዊ የተደረገ  መሆኑን  ገልጸዋል።

 

ለመጀመሪያ ጊዜ በክልላቸው የተሞከረውን የተፋጠነ የትምህርት ቤት ዝግጁነት ፕሮግራም አስመልክቶ አጠቃላይ ሂደቱን፣ የተከናወኑ ተግባራትን እና ያጋጠሙ ችግሮችን አስመልክቶ የክልሉ ሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ሥራ ሂደት ባለቤት ሰፋ ያለ ገለጻ አቅርበዋል። በገለጻውም በዋነኛነት በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጁትን የሥርዓተ ትምህርት ሰነዶች ክልሉ በማስተማሪያነት ወደሚጠቀምባቸው የበርታ፣ የጉሙዝ እና የሽናሻ ቋንቋዎች የመተርጎም፣መርሀ ግብሩ ተግባራዊ የሚደረግባቸውን ቦታዎች የመለየት፣የመምህራን ምልመላ፣ ለባለድርሻ አካላት ግንዛቤ መፍጠር ፣በመርሀ ግብሩ የሚሳተፉ ህፃናትን የመመዝገብና የመለየት፣የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ለመምህራን የተግባር ስልጠና መስጠት፣የድጋፍ እና  ክትትል ስራዎች፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና በመጨረሻ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮችን መቀመርን  የተመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮች ተካተዋል።

 

በመርሀ ግብሩ የሙከራ ትግበራ የተገኙ ዋና ዋና ውጤቶችን፣የአሰራር ልምዶችንና የተገኙ ውጤቶችን መሠረት በማድረግ በዩኒሴፍ ድጋፍ የተካሄደው የዳሰሳ ጥናት በክልሉ የቀረበ ሲሆን የጥናቱ ውጤትም በመርሀ ግብሩ ላይ የተሳተፉ ተማሪዎች በናሙናት በተወሰዱት /ቤቶች 92.9 % እስከ 1ኛው መንፈቀ አመት መቆየት የቻሉ መሆኑን እንዲሁም በክረምትና በበጋ ከተሳተፉት ተማሪዎች መካከል 80.1% 1 ክፍል ገብተው ትምህርታቸውን መቀጠል ያቻሉ መሆኑን አመላክቷል።

 

  ለሁለት ቀናት በተደረገው መርሀ ግብሩን የማስተዋወቅና የማስፋት ውይይት ላይ አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ እና የተቀመጠውን ግብ ከማሳካት አኳያ የተፋጠነ የትምህርት ቤት ዝግጁነት መርሀ ግብርን እንደ አራተኛ የትምህርት አሰጣጥ መንገድ በመጠቀም የቅድመ መደበኛ ትምህርትን ተደራሽነትን እና ሽፋንን ማሳደግ የሚቻል መሆኑ ላይ ግንዛቤ ተፈጥሯል።

 

የአውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች  በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተሞከረውና አሁን በመስፋት ላይ ያለው የተፋጠነ የትምህርት ቤት ዝግጁነት  ፕሮግራም የቅድመ መደበኛ ትምህርት ሽፋንን በማሳደግ  እና ህፃናትን ለአንደኛ ክፍል ዝግጁ በማድረግ ረገድ ያለው  ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን መገንዘባቸውን ለማረገጋገጥ ተችሏል። ከዚህ በተጨማሪ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል በዩኒሴፍ በሚታገዙና ከዛ ውጭ ባሉ በድምሩ  32 ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ የተመረጡ /ቤቶች ላይ ቀደም ብሎ 2008 . ጀምሮ መርሀ ግብሩ ተግባራዊ በመደረግ ላይ እንደ ሆነ እና በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦች ህዝቦች ክልል መርሀ ግብሩን 2009 . ክረምት ወቅት ጀምሮ ተግባራዊ ለማድረግ  የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ከወዲሁ እየተሠሩ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

 

መርሀ ግብሩን የማስፋት ስራ እየተሰራ መሆኑን አስመልክቶ ግንዛቤ ተይዟል። በመሆኑም መርሀ ግብሩ ጠቃሚ መሆኑን እና በሙከራ ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን ፕሮግራሙን የማስፋት ስራ የሚያከናውኑ ክልሎች እንደ ትምህርት በመውሰድ የማስፋት ስራው እንዲከናወን ያለምንም የሀሳብ ልዩነት ስምምነታቸውን ገልጸዋል።

 

በመጨረሻም በኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ያሳቡ ብርቅነህ ከፕሮግራሙ አንጻር ክትትል ሊደረግባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን በዝርዝር ለተሳታፊዎች በማሳሰቢያ መልክ አቅርበው አውደ ጥናቱ  ፍጻሜውን ሊያገኝ  ችሏል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡