የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የአመራርና የአስተዳደር ክህሎት ለማሳደግ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የአመራርና የአስተዳደር ክህሎት ለማሳደግ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው

ከፍተኛ የመንግስት አመራሮችን  ያሳተፈ  በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት በአሁኑ ወቅት ያለበትን ሁኔታ  ላይ በማተኮር ምሁራን በዘርፉ እምርታዊ ዕድገት ለማስመዝገብ  በሀገራችን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአመራር ሚናና አሰራር ምን መምሰል እንደሚገባ ጥናቶችን መሰረት ያደረገ  መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

 በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር / ሳሙኤል ክፍሌ  መድረኩን በንግግር በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት ለከፍተኛ ትምህርት አመራሮች በተለያዩ ጊዜያት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በአመት ሦሥት  ማለትም የአጭር የመካከለኛና የረጅም ጊዜ የግንኙነት እቅድና የአፈጻጸም ሪፖርት  መድረክ መኖሩን ጠቁመዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ጥራት በሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ፣ በቂና ተወዳዳሪ የሰው ሃይል የማፍራት ተልዕኮን አጠናክረው ለማስቀጠል በዘርፉ የከፍተኛ አመራሮች አቅም ግንባታ ቀዳሚ አጄንዳ መሆኑንም ዶክተሩ ተናግረዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚመረቁ ምሩቃን ብቃትና የጥናት ምርምር መርሃ ግብር ተግባራዊነት ወደ ተሸለ ደረጃ ለማድረስ  የዩኒቨርሲቲ አማራሮች ሚና የላቀ መሆኑን ክቡር ሚኒስትሩ አክለው ገልጸዋል፡፡

እንደ / ሳሙኤል ገለጻ የከፍተኛ ትምህርት ጥራት በሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን  አምሰተኛውን የትምህርት ዘርፍ ልማት መርሃ ግብርና ሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን አቅድ እንዲሁም  የልማት ግቦች ማለትም መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት ተርታ ሀገራችን ለመሰለፍ የዩኒቨርሲቲ  አመራሮች  ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

በአፍሪካ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት አለም አቀፍ ኔትዎርክና  በደቡብ አፍሪካ ከዋዙሉ ናታል ዩኒቨርሲቲ የከፍተኛ ትምህርት ስልጠና ልማት መሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ዳምጤው ተፈራ  የአፍሪካ ከፍተኛ ትምህርት ተግዳሮቶች ወሳኝ ዝንባለን አስመልክቶ የምርምር ውጤታቸውን ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት የዩኒቨርሲቲ አመራሮች የዓላማ፣ የስልጣን፣ የልምድና የስኬት ተጠራጣሪነት ወደኋላ በመተው እውቀት፣ ክህሎትና ልምድን በማቀናጀት የተቋማቸውንና የሀገራቸውን ተልዕኮ ማሳካት በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር  ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ከከዋዙሉ ናታል ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ከሚያዚያ 09-13/2009 . ለሦሥት ቀናት የሚቆይ መድረክ እያካሄዱ ነው፡፡

በመድረኩም  ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከአፍሪካ ህብረት የተውጣጡ የመንግስት ሃላፊዎችና ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም የዘርፉ ምሁራን ተሳትፈዋል፡፡


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡